TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሣኔ የምርጫ ምልክት ይፋ ተደርጓል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር በጋራ የሚከናወነው ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክት ዛሬ በይፋ አሳውቋል።
- የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን ፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን ከደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመስረታቸውን እንደግፋለሁ - የባለ 6 እጆች ጥምረት ምልክት።
- የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን ፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አካል ሆነው መቀጠላቸው እደግፋለሁ - የጎጆ ቤት ምልክት።
@tikvahethiopia

የአብን እጩ ተገደሉ።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበሩት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) አባል አቶ በሪሁን አስፈራው በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ እንደተፈፀመባቸው ፓርቲው አስታውቋል።
አቶ በሪሁን ግድያ የተፈፀመባቸው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያሉ ልዩ ቦታው "ካርባር" በሚባል ቦታ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ፓርቲው በተፈፀመው ግድያ መሪር ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።
አብን ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ላይ፥ ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ማድረጋቸውን ነገር ግን በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን መቻሉን አስታውሷል።
በተጨማሪም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎች ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቹ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ መኩራ መደረጉን አስታውሷል።
አብን የእጩ ተወዳዳሪ አቶ በሪሁን ግድያ ፖለቲካዊ መሰረት ያለው እና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ "ሆነ ተብሎ" የተደረገ እንደሆነ እንደሚያምን ገልጿል።
ፓርቲው መንግስት በምርጫ እጩ አባሉ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቋል።
ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ አስገንዝቧል።
* አብን ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ዶ/ር አይናለም አብርሃ በኮቪድ-19 ህይወታቸው አለፈ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመምህርነት እና በካንሰር ሕክምና ዘርፍ ያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አይናለም አብርሃ በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የዶክተር አይናለም አብርሃ ሕልፈት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ለሀገሪቱ ትልቅ ጉዳት ነው ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው የሃዘን መግለጫ።
ዶክተር አይናለም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በጥቁር አንበሳ ስፕሺያላይዝድ ሆስፒታል በካንሰር ሕክምና ከፍተኛ ባለሙያነት እንዲሁም በአአዩ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የካንሰር ሕክምና ማእከል ሐላፊ በመሆን ለበርካታ አመታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የጤና ሚኒስቴር በዶ/ር አይናለም አብርሃ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።

#Update የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦ - በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። - በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (#MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ…
#ማስተካከያ
ትላንት ይፋ በተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመቁረጫ ነጥብ ላይ የተደረገ ማስተካከያ (መስማት ለተሳናቸው እና ለአይነስውራን) እንደሚከተለው ቀርቧል።
ተፈጥሮ ሳይንስ ፦
- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 275 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ
- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ
ማህበራዊ ሳይንስ ፦
- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ
- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 265 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ
- ለአይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 240 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ
- ለአይነስውራን ሴት ተማሪዎች 235 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ
መረጀውን ያገኘነው ከ #MoSHE ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደሪ ታስረዋል ?
በተለያዩ አካላት ግለሰቦች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ አቶ ባይነሳኝ ዘሪሁን "ታስረዋል" እየተባለ የሚናፈሰው አሉባልታ ከዕውነት የራቀና ፍፁም ውሸት ነው ሲል የአዊ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
አስተዳዳሪው አሁንም በመደበኛ የመንግስት ስራ ላይ ያሉ እና ባለጉዳዮቻቸውን በተለመደው አግባብ እያስተናገዱ ነው ብሏል ቢሮው።
እንደዚህ ባለው አጀንዳ ላይ የተሰማሩ አካላት ተግባራቸው ለህዝብም ሆነ ለሀገር ፋይዳ እንደሌለው ተረድተው ከተግባራቸውን እንዲታቀቡ ሲል የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አሳስቧል።

#ሀሰተኛ_ዜና
"በአባቴ ህይወት ላይ አታሟርቱ፤ አባቴ አልሞተም" - ጃጋማ ዋሚ
በኖሩበት የምድር ህይወት ፣ እያንዳንዱን ያደረጉትን ተግባር ፣ በቀን ፣ በአመተ ምህረት ፣ በሰዓት ሳያዛንፉ የሚናገሩት ጀግናዉ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የተባለዉ ዉሸት ነዉ።
እባካቹህ መረጃ ሳታረጋግጡ ሰዉን አታሳስቱ።
Via መኳንንት በርሄ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"በአባቴ ህይወት ላይ አታሟርቱ፤ አባቴ አልሞተም" - ጃጋማ ዋሚ
በኖሩበት የምድር ህይወት ፣ እያንዳንዱን ያደረጉትን ተግባር ፣ በቀን ፣ በአመተ ምህረት ፣ በሰዓት ሳያዛንፉ የሚናገሩት ጀግናዉ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የተባለዉ ዉሸት ነዉ።
እባካቹህ መረጃ ሳታረጋግጡ ሰዉን አታሳስቱ።
Via መኳንንት በርሄ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አትሌት ዋሚ ቢራቱ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ !
ማህበራዊ ሚዲያዎች ስለተሰራጨው የአትሌት ዋሚ ቢራቱ ሀሰተኛ ህልፈት ዜና በተመለከተ ልጃቸው ጃጋማ ዋሚ ቢራቱ እንዲሁም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጵያ ቼክ ከተናግሩት ፦
"አባቴ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ሞተ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ስራ በሚሰሩ ሰዎች በጣም አዝናለሁ። አባቴ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል ፣ ዛሬ ጠዋት ራሱ በስልክ አውርተናል። ህብረተሰቡ የሀሰተኛ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ ሊያረግ ይገባል። ይህንን የሚፅፉ ሁሉ ሀላፊነት ሊሰማቸው ይገባል። ለነገሩ እኛ እንዲህ ተብሎ እንደተወራ ለአባታችን አንነግረውም፣ ሲጀምር እሱ ለወሬ ቦታ የለውም" - ጃገማ ዋሚ ቢራቱ
.
.
"ውሸት ነው ፤ ከቤተሰብም ሆነ ከጓደኞች አረጋግጫለሁ" - ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ

#Attention😷
ባለፉት 24 ሰዓት 33 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 7,487 የላብራቶሪ ምርመራ 1,851 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,193 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 225,516 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,111 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 167,945 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 895 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose

#GERD🇪🇹
የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት ለምታከናውነው የውሃ ሙሌት ሀገራቱ የግድብ ባለሙያዎችን ኢንዲመድቡ በይፋ ጋብዘዋል።
ሚኒስትሩ ለሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለግብፅ ውሃ ሚኒስቴር በላኩት ድባዳቤ ነው ሁለቱ ሀገራት የፊታችን ሐምሌ እና ነሃሴ ወር ላይ የሚከናወነውን የውሃ ሙሌት በተመለከተ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ባለሙያን እንዲመድቡ የጋበዘዋቸዋል።
በሚኒስትሩ ደብዳቤ መሠረት ግብዣው የ3ቱ ሀገራት ብሄራዊ ገለልተኛ የሳይንስ ምርምር ቡድን (NISRG) ባቀረበው የሙሌት የጊዜ ሰሌዳ ላይ በተደረሰው መግባባት ላይ በመመርኮዝ የቀረበ መሆኑ እና በዚህም መሰረት ሙሌቱ በሐምሌ እና ነሐሴ ወር ውስጥ እንደሚከናወን ፤ በወቀቱ በሚኖር የውሃ መጠን ላይ በመመርኮዝ እስከ መስከረም ወር ሊራዘም እንደሚችል ተመላክቷል።
የግድቡ ግንባታ የደረሰበትን ሁኔታና የዝናብ ወቅት መድረሱን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ተግባራዊና አስፈላጊ የሆነ የንግግር መድረክ ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
መረጃ የሚለዋወጥ ሰው መመደብ ትክክለኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ያፋጥናል፤ በአፍሪካ ህብረት ስር የሚደረገው የግድቡ ድርድር እስከሚጠናቀቅ ድረስ በሶስቱ ሀገራት መካከል መተማማን ይፈጥራል ብሏል መግለጫው፡፡
መግልጫው እንደጠቀሰው ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ካርቱም ውስጥ በፈረንጆቹ 2015 በሱዳን በሶስቱ ሀገራት በተፈረመው “የመርሆች ስምምነት መሰረት” በመጀመሪያው የግድቡ ሙሌት ህጎችና መመሪያዎች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን መረጃ የሚለዋወጡ ሰዎቸ ስብሰባ ለማካሄድ ፍላጎት አላት ብለዋል፡፡ [Al AIN News]

"ሮሃ ግሩፕ" የተሰኘ በጤና ዘርፍ የተሰማራ የአሜሪካ ኩባንያ በራሱ ወጪ የሚያስገነባው "ሮሃ የህክምና ማዕከል" ሜጋ ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የኢትዮጵያ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ናቸው።
የ "ሮሃ ህክምና ማዕከል" ሜጋ ፕሮጄክት ግንባታው በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 "አድዋ ፓርክ" አካባቢ በ300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ነው የሚገነባው።
የፕሮጀክቱ ግንባታ በ5 ዓመት ይጠናቀቃል ተብሏል።
የሕክምና ማዕከሉ በውስጡ 5 ሆስፒታሎች እንደሚኖሩት ተገልጿል።
በግንባታው በየዓመቱ አንድ ሆስፒታል አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ መታቀዱ ነው የተሰማው።
ሮሃ የሕክምና ማዕከል በውስጡ የነርቭና የጀርባ ፣ የህጻናትና እናቶችና የልብ ሕክምና ሆስፒታሎች ፣ የሕክምና ትምህርት ቤት እንዲሁም የጥናትና ፈጠራ እና የማገገሚያ ማዕከላት እንደሚኖሩት ተገልጿል።
ማዕከሉ 4 ሺ 200 የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ለ7 ሺህ 200 ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
#ENA

ለ22 ዓመት ጅቡቲን የመሩት ፕሬዜዳንት ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እየተወዳደሩ ነው ! የጂቡቲ ህዝብ ለፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ዛሬ ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛል። የጅቡቲው ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዜዳንትነት እየተወዳደሩ ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድምፃቸውን ሰተዋል። ከ200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች የተሳተፉበት ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡…
ግዜያዊ ውጤት : ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከ98% በላይ ድምፅ አገኝተዋል።
ጊዜያዊ ውጤቶች እንዳመለከቱት ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከ98% በላይ ድምፅ አግኝተው ለ5ኛ ጊዜ የጅቡቲን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አሸንፈዋል።
ዋነኛዎቹ ተፎካካሪዎች ምርጫው "ነፃ እና ፍትሃዊ" አይደለም ብለው እራሳቸውን ባገለሉበት የጅቡቲ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ከ21 ዓመት በላይ በሥልጣን ላይ የሚገኙት የ73 ዓመቱ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከ98% በላይ ድምፅ አግኝተዋል ተብሏል።
ይህ ጊዜያዊ ውጤት የተገለፀው ትላንት ለሊት ነው።

አፍሪካ : ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የሚገኙ/እያገለገሉ ያሉ መሪዎች ፦
[official data & AFP bureaux]
- ቴዎዶሮ ኦቢአንግ ነጉኤማ (ኢኳቶሪያል ጊኒ) 41 ዓመታት በስልጣን
- ፖውል ቢያ (ካሜሩን) 38 ዓመታት
- ዴኒስ ሳሱ ንጉሶ (ኮንጎ) 37 ዓመታት
- ዩዌሪ ሙሴቬኒ (ዩጋንዳ) 35 ዓመታት
- ምዋስቲ III (ስዋቲኒ) 34 ዓመታት
- ኢድሪስ ዴቢ (ቻድ) 30 ዓመታት
- ሌቲስ III (ሌሴቶ) 29 ዓመታት
- ኢሳያስ አፈወርቂ (ኤርትራ) 27 ዓመታት
- ኢስማኤል ኡማር ጌሌ (ጅቡቲ) ከ21 ዓመታት በላይ
- መሀመድ VI (ሞሮኮ) 21 ዓመታት
- ፖል ካጋሜ (ሩዋንዳ) 21 ዓመታት
- ፋውሬ ግናሲንግቤ (ቶጎ) 15 ዓመታት

#HawassaUniversity
ዛሬ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 270 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል 48ቱ በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም የሰለጠኑ ናቸው።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶክተሮችን ሲያስመርቅ የዛሬው ለ12ኛ ጊዜ ነው።
በሌላ በኩል ፦ ከ12ኛ ዙር ተመራቂዎች መካከል ዶክተር ዮናስ ንጉሴ 3 ነጥብ 87 ውጤት በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሻላሚ መሆን ችሏል።
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ክፍል እስካሁን ከተመዘገቡ ውጤቶች ውስጥ ከፍተኛው በመሆንም ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።
ምንጭ፦ SRTA