TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.3K photos
1.58K videos
216 files
4.33K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19Vaccine

ዛሬ መጋቢት 30 በኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ጀምረዋል።

ክትባቱን ለሁሉም የኃይማኖት አባቶች ለመስጠት ፕሮግራም እንደተያዘ ታውቋል።

PHOTO : EOTC TV & EBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Vaccine : የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆታጠር ከ54 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከአጠቃላይ ሕዝባቸው 10 % የሚሆነውን በመክተብ የዓለም ጤና ድርጅትን ግብ ያሳኩት 14ቱ ብቻ መሆናቸው ተገለፀ።

የዓለም ጤና ድርጅት አገራት ከሕዝባቸው ቢያንስ 10 በመቶውን እንዲከትቡ ያስቀመጠው ጊዜ በፈረንጆቹ የመስከረም ወር መጨረሻ ነው።

ለዚህ ግብ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያቱ በአብዛኛው ክትባቱን ለድሃ አገራት ለማሰራጨት የተቋቋመው ኮቫክስ በበቂ መጠን ክትባት ማግኘት ባለመቻሉ ነው።

ከአፍሪካ ሀገራት ሲሸልስ፣ ሞሪሺየስ እና ሞሮኮ ከ40 በመቶ በላይ ሕዝባቸውን በመክተብ በአህጉሪቱ ውስጥ ከፍተኛውን የክትባት መጠን አሳክተዋል።

እነዚህ ሀገራት ክትባቱን በተሳካ ሁኔታ ያስኬዱት ጠንካራ የክትባት መርሃ ግብር ስላላቸው፣ የቆዳ ስፋት እና የሕዝባቸው ብዛት ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

ለመሆኑ 10% የሚሆነውን ህዝባቸውን የኮቪድ-19 ክትባት በመክተብ የዓለም ጤና ድርጅትን ግብ ያሳኩት 14ቱ ሀገራት እነማን ናቸው ? ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።

Credit : BBC

@tikvahethiopia