TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ነገ ይፋ ይደረጋል። የ2013 ዓ/ም የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ 'መወሰኛ ነጥብ' ነገ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማምሻውን አስታውቋል። @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#MoSHE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ነጥብ :

በተፈጥሮ ሳይንስ ፦

- ለወንድ 380 ፤ ለሴት 368

- ለታዳጊ ክልሎች ደግሞ ለወንድ 368 ለሴት 358

- ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 350 ፤ ለሴት 345

- ለአርብቶ አደሮች አካባቢዎች 358

- በትግራይ እና መተከል ለወንድ 358 ፤ ለሴት 350

በማህበራዊ ሳይንስ ፦

- ለወንድ 370 ፤ ለሴት ደግሞ 358

- ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 358 ፤ ለሴት 348

- ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 340፤ ለሴት 335

- በትግራይና መተከል ለወንድ 348 ፤ ለሴት 340

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ባልሆነ ፕሮግራም ማለትም (በክረምት ፣ በማታ ፣ በሳምንት መጨረሻ ፣ የርቀት ፣ በበይነ መረብ) እና በግል ተቋማት በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ አማራጮች ለመማር አነስተስተኛው የመቁረጫ ነጥብ ፦ ለወንዶች 330 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 320 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE

በግል ተቋማት የህክምና መስኮችን ለመማር አነስተኛው የመቁረጫ ነጥብ (ከተፈጥሮ ሣይንስ መስክ ለሚመጡ ብቻ) ለሁለቱም ፆታ 450ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE

በ2013 ዓ/ም 147,640 (88,153 ወንድ ፤ 59,487 ሴት) ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ። እነዚህ ተማሪዎች በ46ቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ ይደረግላቸዋል።

በተጨማሪም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መቀየር እንደሚቻል MoSHE አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
"...አስቸጋሪ የሆነ መልክዓ ምድር ባለበት አካባቢ አገልግሎቱን (የ4G LTE) ለምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ተደራሽ ማድረግ በመቻላችን ደስተኛ ነን" - ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ

ኢትዮ-ቴሌኮም በምስራቅ ምስራቅ ሪጅን የ4G ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኢንተርኔት አገልግሎት በይፋ አስጀምሯል።

የሶማሌ ክልል ሰባት ከተሞችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው የ'4G ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት በጂግጂጋ ከተማ ለምረቃ በቅቷል።

አገልግሎቱ ፦

- ጅግጅጋ፣
- ጎዴ፣
- ቀብሪ ደሃር፣
- ቀብሪ በያህ፣
- ደገሃቡር፣
- ፊቅና ዋርዴር ከተሞች የሚገኙ 454 ሺህ ደንበኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ፥ የማስፋፊያ አገልግሎቱ በአንድ ወር ውስጥ ተደራሽ መደረጉን አሳውቀዋል።

የ4G ኢንተርኔት አገልግሎት ደንበኞች ዘመኑን የሚመጥን ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል።

በተጨማሪም አገልግሎቱ በአካባቢው ለሚገኙ ደንበኞች ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ማግኘት ያስችላል ነው ያሉት።

ኢትዮ-ቴሌኮም አስቸጋሪ በሆነ መልክዓ ምድር ባለበት አካባቢ አገልግሎቱን ለምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ተደራሽ በማድረጉ ደስተኛ ነው ብለዋል ወይዘሪት ፍሬህይወት። #EthioTelecom

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...ከመንግስታቱ አስቸኳይ መልስ እንፈልጋለን" - ጓንጓ ወረዳ

መተከል ዞን አዋስነው በሚገኙት የአማራ ክልል ወረዳዎች ጃዊ፣ ጓንጓ ፣ ዚገም እና ቻግኒ ከተማ ላይ ያንዣበበው ከፍተኛ ስጋት ንፁሃንን አጉል መሰዋትነት እያስከፈለ ነው ሲል የጓንጓ ወረዳ አስታወቀ።

ቀጠና ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበት በመሆኑ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩ ግልፅ ነው ብሏል የወረዳው ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ።

ወረዳው ፥ "ያለ ምክንያት እየተሰዋ ላለው ህዝባችን የ2ቱ ክልል መንግስታትና የፌዴራሉ መንግስት ዝምታ ባይገባንም አስቸኳይ የሰላም መፍትሔ የማይሰጥ ከሆነ ህዝባችን ላይ የሚደርሰው አደጋ የከፋ እንደሚሆን በተግባርም እየተመለከትን በመሆኑ ከሶስቱ መንግስታት አስቸኳይ መልስ እንፈልጋለን" ብሏል።

@tikvahethiopia
#COVID19Vaccine

ዛሬ መጋቢት 30 በኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ጀምረዋል።

ክትባቱን ለሁሉም የኃይማኖት አባቶች ለመስጠት ፕሮግራም እንደተያዘ ታውቋል።

PHOTO : EOTC TV & EBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Update

የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦

- በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

- በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (#MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ያንብቡ ፤ ለሌሎችም ያጋሩ።

@tikvahethiopia @TikvahUniversity
#ምርጫ2013

"...ከአገሪቱ የመክፈል አቅም አኳያ ክፍያው አነስተኛ አይደለም" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ

ለስድስተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ 200 ሺ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና ተከታትለው ወደ ሥራ ገብተዋል።

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከተሰማሩ አስፈጻሚዎች መካከል የተወሰኑት ''ክፍያው ያንሰናል'' በሚል ምክንያት በሥራ ገበታቸው ላይ እንዳልተገኙ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ አስፈጻሚዎች ከክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ስልጠና ተሰጥቷቸው በአ/አ ከተማ የምርጫ ጣቢያዎች ከተሰማሩት አስፈጻሚዎች መካከል የተወሰኑት ሥራ ባለመጀመራቸው የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች አገልግሎት ሳይሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ምርጫ ቦርድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሌሎች የምርጫ አስፈጻሚዎችን በመመልመል አገልግሎቱ በፍጥነት እንዲጀመር ማድረጉን ገልጸዋል።

ያልሰለጠኑ የምርጫ አስፈጻሚዎች ወደ ስለማይሰማሩ እንደ አዲስ ስልጠና በመስጠት የሰው ሃይል ማሰማራት ፈተና እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ይህም ቢሆን ግን የሰው ሃይል እጥረት ያለባቸው ቦታዎችን አዲስ የምርጫ አስፈጻሚዎችን በማሰልጠን የሰው ሃይሉ እንዲሟላ መደረጉን ተናግረዋል።

ለምርጫ አስፈጻሚዎች የሚመደበው ክፍያ ለምርጫው ከተያዘው በጀት ከፍተኛ መጠን እንደሚይዝ ገልፀው፤ ከአገሪቱ የመክፈል አቅም አኳያ ክፍያው አነስተኛ አለመሆኑን አይደለም ብለዋል።

"በመሆኑም የምርጫ አስፈጻሚዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአገራዊ የኃላፊነት መንፈስ ሊወጡ ይገባል" ብለዋል።

አስፈጻሚዎቹ ኃላፊነታቸውን በትክክል በመወጣት ለኢትዮጵያ መጻኢ እድል ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።~ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የስልክ ውይይት :

[Deutsche Welle , Reuters, www.whitehouse.gov]

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጃክ ሰሊቫን የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ፀጥታን ያናጋዉ ግጭት እና ጥቃት እንዳሳሰባቸዉ አስታውቀዋል።

ዋይት ሐዉስ፥ የፀጥታ አማካሪዉ ከም/ጠቅላይ ሚንስትር እና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት በስልክ ባደረጉት ዉይይት በተለይ ትግራይ ክልል ዉስጥ የሚደረገዉ ግጭት እንዳሳሰባቸዉ አስታዉቀዋል።

ሮይተርስ ዋይት ሐዉስን ዋቢ እንድርጎ እንደዘገበው፥ 2ቱ ባለስልጣናት ትግራይ ዉስጥ ለተቸገረዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ስለሚቀርብበት ፣ ግጭቱ ስለሚረግብበት ፣ የዉጪ ወታደሮች ስለሚወጡበትና የደረሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደል በገለልተኛ ወገን ስለሚጣራበት ሁኔታ ተነጋግረዋል።

ከትግራይ ክልል በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉት የጎሳ ግጭቶችና ጥቃቶች በዉይይቱ መነሳቱ ተጠቅሷል።

በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የገጠመችዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የሚደረገዉ አካባቢያዊ ዉይይት መቀጠል እንዳለበት መወያየታቸውን ኃይት ሐውስ አሳውቋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በይፋዊ የማህበራዊ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በትግራይ ያለው ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑንም በስልክ ውይይቱ ወቅት እንዳብራሩ ገልፀዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ታዛቢዎች በፍትሃዊነት እና በገለልተኝነት እንዲያገለግሉ በማሰብ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ድርድር ቁልፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈታ እንዳረጋገጡላቸው አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

#Purpose #Tikvah

- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 341 የላብራቶሪ ምርመራ 39 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 56 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓት ከተደረገው 40 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 87 የላብራቶሪ ምርመራ 54 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 197 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 3 አገግመዋል።

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 105 የላብራቶሪ ምርመራ 40 ሰዎች ላይ ቫይረዱ ተገኝቷል ፤ 16 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 809 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 244 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

* ያልተካተቱ ሪፖርቶች ይፋ የሚደረጉ ከሆነ ዘግየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ።

@tikvahethiopia
#Attention😷

ባለፉት 24 ሰዓት 20 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,757 የላብራቶሪ ምርመራ 2,121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 617 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 223,665 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,078 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 166,752 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 892 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በአፋር እና ሱማሊ ክልል መካከል ያለው ውጥረት ፦ የአፋር ክልል መንግስት ፦ - በክልሉ "ሀሩቃ" በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መቁሰላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። - በአርቡ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል። - የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በዚያኑ ዕለት ምሽት "ገዋኔ"…
#UPDATE

የሱማሌ ክልል እና አፋር ክልል መንግስታት ችግሮቻቸውን በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ተገልጿል።

የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን ዛሬ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ሰብሳቢነት ምክክር አድርጓል።

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠሩትን ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰላም ሚኒስቴር ማምሻውን አሳውቋል።

የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በተገኙበት የተከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ለማስቆምና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት አድርገዋል።

@tikvahethiopia