TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የሰላም ንግግር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙን ሮይተርስ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ቀጠሮ የተያዘለት የሰላም ንግግር መራዘሙ ከሎጂስቲክስ ዝግጅት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸው እስካሁን አዲስ ቀን እንዳልተቆረጠ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በአፍሪካ…
#PeaceTalks

ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከ4 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ቀን እንደተቆረጠለት ተሰምቷል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የነበረውና በሎጅስቲክስ ዝግጅት ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከዛሬ 4 ቀናት በኃላ (ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም) በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ መሆኑ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን  ለማድረግ ለጥቅምት 14/2015 ዓ/ም ቀን መቁረጡን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ " በዚሁ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናችንን በድጋሚ አረጋግጠናል " ብለዋል። " ነገር ግን መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል ርምጃ ለማጠልሸት የሃሰት ከስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካካት ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልፃል።" ሲሉ አክለዋል።

አፍሪካ ህብረት በህብረቱ የሚመራና በደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለህወሓት ግብዣ አቅርቦ እንደነበርና በሁለቱም በኩል ግብዣው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።

የሰላም ንግግሩ ፤ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ እንደሚመራም መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU የ " ኢትዮጵያ መንግስት " እና የ " ህወሓት " ን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫው ምን አሉ ? - የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል። - በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)…
#PeaceTalks

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህበረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

እስካሁን የንግግሮቹን ይዘት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም። በዛው ያሉ ሚዲያዎችም ስለ ሰላም ንግግሩ እና ስለሂደቱ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እንዳይኖር ተደርጓል።

የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ እንደሚቀጥል ነው የሚጠበቀው።

የደቡብ አፍሪካ/ፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ አመቻችነት ነው እየተመራ የሚገኘው።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN)፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ደግሞ በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

በሌላ በኩል፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ለስራ ጉብኝት ወደ ካናዳ (ኦታዋ) በሄዱበት ወቅት በዛው ከነበሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ውይይት እንዳካሄዱ ገልፀዋል።

ፋኪ በውይይቱ ፤ ለአፍሪካ ሰላም የፖለቲካ ሂደትን በተመለከተ እንዲሁም በታህሳስ ወር ለሚካሄደው የአፍሪካ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

የደ/አፍሪካው ሰላም ንግግርም "ወደ ተኩስ አቁም ይመራል " የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሊቀመንበሩ (ሙሳ ፋኪ መሀመት) እና የአፍሪካ ህብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን #ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ፎቶ ፦ ሮይተርስ/AU

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PeaceTalks የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህበረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል። እስካሁን የንግግሮቹን ይዘት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም። በዛው ያሉ ሚዲያዎችም ስለ ሰላም ንግግሩ እና ስለሂደቱ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እንዳይኖር ተደርጓል።…
#PeaceTalks

ትላንት እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ሰኞም እንደሚቀጥል ተሰምቷል።

ኤፒ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የሰላም ንግግሩ ዛሬም ይቀጥላል።

ከኤፒ በተጨማሪም " SA FM RADIO " የሰላም ንግግሩ ዛሬ እንደሚቀጥል ዘግቧል።

የሰላም ንግግሩን ይዘትና አጠቃላይ አሁን ላይ የደረሰበትን ሂደት በተመለከተ ምንም ይፋዊ መረጃ የለም። የሰላም ንግግሩ ሚዲያዎች መረጃ ሊያገኙበት በማይችል ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

ለሰላም ንግግሩ ቅርብ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ንግግሩ ምን እድገት እንዳሳየ ሲጠየቁ፤ " እሱን ጊዜ ብቻ ነው የሚነግረን " ሲሉ መልሰዋል።

ሌሎች ምንጮች ደግሞ የሰላም ንግግሩ ዝግ እያለ እየሄደ ቢሆንም በአካል ተገናኝቶ ፊት ለፊት መነጋገሩ ተቀባይነትን እንዳገኘ አመላክተዋል።

በግጭት ማቆም፣ በሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት እና በወሳኝ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንደገና መጀመር ላይ በተደረገ ንግግር "ትልቅ እድገት" ታይቷል ሲሉ እነዚህ ምንጮች ገልፀዋል።

የሰላም ንግግሩ " ወደ ተኩስ አቁም ይመራል " የሚል ተስፋ እንዳላቸው ሙሳ ፋኪ መሀመት ከቀናት በፊት ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

እስካሁን ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች/ አዘጋጆች በኩል በቀጥታ የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም፤ የሰላም ንግግሩ አዘጋጆች የንግግሮችን ይዘትና ሂደት በተመለከተ ከሚዲያዎች ርቀው ዝግ በሆነ መንገድ ነው እያስኬዱ የሚገኙት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከላይ ያነበባችሁት መረጃ የተሰባሰበው፦ ከ "The Star kenya" ጋዜጠኛው ኢሊዩድ ኪቢ፣ SA FM RADIO/SABC፣ ከDaily Maveric/South Africa/ እንዲሁም ከኤፒ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PeaceTalks ትላንት እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ሰኞም እንደሚቀጥል ተሰምቷል። ኤፒ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የሰላም ንግግሩ ዛሬም ይቀጥላል። ከኤፒ በተጨማሪም " SA FM RADIO " የሰላም ንግግሩ ዛሬ እንደሚቀጥል ዘግቧል። የሰላም ንግግሩን…
#PeaceTalks

2 ዓመት ሊደፍን የተቃረበውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው የሰላም ንግግር ነገ ማክሰኞም ይቀጥላል ተብሏል።

ትላንት ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ይኸው የሰላም ንግግር ተራዝሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉና ነገም እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

ከዚሁ የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ ፤ የአፍሪካ ህብረት ንግግሩ የሚጠናቀቅበት ቀነ ገደብ እንዳልተቀመጠ ለኤኤፍፒ በሰጠው ቃል ገልጿል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ቃል አቀባይ ኤባ ካሎንዶ ፤ " በንግግሩ (በሰላም ንግግሩ) ላይ ቀነ ገደብ አልተቀመጠም " ብለዋል።

አሁን ድረስ የንግግሩን ይዘት ፣ ስላለበት ደረጃ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከተ ምንም አይነት ይፋዊ መረጃ ያልወጣና ሚዲያዎችንም የሰላም ንግግሩን በተመለከተ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ ዝግ የተደረገ ሲሆን አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማት የሰላም ንግግሩ አስተባባሪዎች ንግግሩን በጥብቅ ሚስጥር እንደያዙት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia