🏷የ12ኛ ክፍል የፈተና #ዉጤት አስመልክቶ በተለያዩ ማህበረዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ መረጃዎች #ሀሰት መሆናቸውን የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀዉ የ12ኛ ክፍል ዉጤት #በቅርቡ ይለቃቃል የሚለዉ መረጃ መሰረተ ቢስ ነዉ ብሏል። የኤጀንሲዉ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ረዲ ሺፋ ለኢትዮኤፍኤም እንዳረጋገጡት ኤጀንሲዉ የፈተናዎቹ ዉጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን አልወሰነም ብለዋል፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ዉጤቱ ተለቋል በዚህ ቀን ይለቀቃልና ሌሎች መሰል መረጃዎች ሀሰት እንደሆኑ አቶ ረዲ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹም ሆነ ህብረተሰቡ ከተሳሳተ መረጃ እራሱን እንዲጠብቅ ሃላፊዉ ጠይቀዋል፡፡ በቀጣይ ኤጀንሲዉ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የፈተና ዉጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን ለመገናኛ ብዙሃን በይፋ ያሳውቃል ብለዋል፡፡
Via #ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia