" 41 የጸጥታ አካላት ከኃላፊነታቸው #ተነስተዋል " - አቶ ሀሚድ አህመድ
ከሰሞኑን በሲዳማ ክልል ፤ የጸጥታ አካላት የግምገማ መድረክ ሲካሄድ መሰንበቱ ተነግሯል።
ይህን ተከትሎ " ለህዝብ ሳይሆን ለራሳቸዉ ቆመዋል " የተባሉ አመራሮች ከስልጣን መነሳታቸው ተገልጿል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የተጣለባቸውን የስራ ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡ በተለይ ህዝብን #ሲያማርሩ እና #ሲያሰቃዩ እንዲሁም የሀገርን ሀብት ሲዘርፉ የነበሩ 41 የፀጥታ አካላት ተነስተዋል " ብለዋል።
በቀጣይ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።
#በታችኛው_እርከን ላይ ያሉ የጸጥታ አመራሮች ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ይቀጥላል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ 291 ከፍተኛ አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉ ገልጸዋል።
ለመሆኑ እነማን ናቸው ከኃላፊነት የተነሱት ? በማለት ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ ዳይሬክተሩ ፤ " አሁን ላይ መግለጽ የምችለው ብዛታቸዉን ብቻ ነው። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
" በቀጣይ ቀናት ማንነታቸውን እናሳውቃችኋለን " ሲሉ ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia