TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የህንድ የጨርቃጨርቅ ማምረቻ ኩባንያዎች በኢትዮዽያ በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ በመሳብ በባንግላዴሽና በካምቦዲያ ያሏቸውን ፋብሪካዎች #በማንሳት ወደ ኢትዮዽያ እያመሩ መሆናቸውን ቢዝነስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ኬፒአር ሚል የተሰኘው ግዙፉ የህንድ የጨርቃጨርቅ አምራች በኢትዮዽያ ፋብሪካውን በመትከል ሰፊ የሰው ሃይል፣ ከቀረጥ ነፃና ወደ ዩኤስ አሜሪካና አውሮፓ ገበያ ቅርብ የሆነውን የመርከብ አገልግሎት ለመጠቀም መወሰኑን ገልጿል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

"ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ የሱማሌ ክልል #ባለስልጣናትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት #ተጠናቋል"- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
.
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ዛሬ ከሰዐት በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት #እንዲጠፋ፣ ህገመንግስታዊ ስርዐትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ንብረት እንዲወድምና በተያያዥ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሌሎቹ 40 ግን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተሸሽገዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ዝናቡ ገለፃ ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በሀገር ውስጥ የተደበቁትንም አፈላልጎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች #ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ መብታቸውን #በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት አቶ ዝናቡ ህዝቡ የተሸሸጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ አድርሱ~~8482👆

ህብረተሰቡ የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያ ቢልቦርዶች ሲመለከት #በ8482 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 1112/2011 የአልኮል ምርት በማንኛውም በብሮድካስትና ቢል ቦርድ ማስተዋወቅ የተከለከሉ ድንጋጌዎች መውጣቱን ተከትሎ አብዛኛው የአልኮል ምርት አምራቾች ህጉን ተከትሎ በአ/አ ስታዲየም ዙሪያና በተለያዩ ቦታዎች የተሰቀሉ ቢልቦርዶችን #በማንሳት ላይ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። ሆኖም በአንዳንድ ቦታዎች እስካሁን ድረስ የቢልቦርድ ማስታወቂያ ያልተነሱ መሆኑንና የአልኮል አምራች ድርጅትና የማስታወቂያ ሰሪ ድርጅቶች በየቦታው የተሰቀለውን ቢልቦርድ እንዲያነሱ አሳስቦ ህብረተሰቡም በየቦታው የተሰቀሉ ቢልቦርዶች ሲመለከት በ8482 በመደወል #ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል።

√√በህዝብ ተወካዬች ም/ቤት በቅርቡ በፀደቀውን የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ 1112 መሰረት ከዛሬ ግንቦት 21 ጀምሮ የአልኮል ማስታወቂያዎችን በብሮድካስት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ህግ ተግባራዊ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል ።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia