#update አዲስ አበባ⬆️
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ የውጭ #ምንዛሬ ግብይት ሲካሄድባቸው የነበሩ በርካታ የንግድ ቤቶች መታሸጋቸው ተሰማ።
የንግድ ቤቶቹ የታሸጉት በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሚመራ ግብረ ሀይል ሲሆን፥ ፖሊስ ከትናንት ጀምሮ ባካሄደው ድንገተኛ ክትትል እና ፍተሻ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
የንግድ ቤቶቹ የታሸጉበት ምክንያት፦
📌በህጋዊ የንግድ ፍቃድ ህገ ወጥ ተግባር በመፈፀማቸው ነው። ተግባሩም ህገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሬ በህገ ወጥ መንገድ የውጭ ሀገራት ገንዘብን #መግዛት እና #መሸጥ ድርጊት ነው።
በዚም በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለከተማ ጋንዲ ሆስፒታል፣ ኢትዮጵያ ሆቴል እና ቴሌ ባር አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች ታሽገዋል።
እንዲሁም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ጊቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት አካባቢዎች ላይ የሚገኙ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ናቸው በተደረገው ፍተሻ ተለይተው ታሽገዋል።
📌በፍተሻው ወቅት በርካታ የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ ገንዘቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
©fbc ፎቶ(ካፒታል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ኢትዮ ቴሌኮም⬆️
ኢትዮ ቴሌኮም አለም አቀፍ የሞባይል አየር ሰአት የመሙላት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
አዲሱ #ኤሌክትሮኒክስ የሞባይል አየር ሰአት መሙያ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ እና የጥምር ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በውጭ ሀገር የሚገኙ ዘመድ ወዳጆቻቸው ወደ ሞባይል ቁጥራቸው የአየር ሰአት #እንዲልኩላቸው የሚያስችል ነው።
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዘመድ ወዳጆቻቸው የሞባይል አየር ሰአት በመሙላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶችን እንዲለዋወጡም ያግዛቸዋል።
ተጠቃሚዎች ይህን የኤሌክትሮኒክ የአየር ሰአት መሙላት አገልግሎት በመጠቀም ከ25 ብር ጀምሮ ወደ ሀገር ቤት ለሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ዘመዶቻቸው የአየር ሰአት #መግዛት እና #መላክ ያስችላቸዋል።
አገልግሎቱ በመላው አለም ተደራሽነት ባላቸው ሀገሮች በቀን 24 ሰአት እና የበአል ቀኖችን ጨምሮ በሁሉም ቀናት የሚሰጥ በመሆኑ ዜጎች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው የአየር ሰአት እንዲገዙ እና በስጦታም እንዲልኩ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ይህ በኤሌክትሮኒክ አየር ሰአት የመግዛት አገልግሎት ለ2G፣ 3G እና 4G የሞባይል አገልግሎት አይነቶች በመቅረቡ ሁሉም የቅድመ ክፍያ እና የጥምር አገልግሎት ሞባይል ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ደንበኞች www.senditoo.com እንዲሁም www.worldremit.com በመጠቀም የአየር ሰአት መግዛት እና ወደዘመድ ወዳቾቻችው መላክ የሚችሉ ሲሆን ሞባይላቸው ላይ ሂሳብ መሞላቱን የሚያረጋግጥ አጭር የፅሁፍ መልእክት ከ994 ይደርሳቸዋል።
መልእክቱ የተገዛውን የአየር ሰአት መጠን በብር እና የሞሉትን የገንዘብ መጠን የሚያበቃበትን ቀን የሚያመለክት ይሆናል።
አገልግሎቱ በገበያ ላይ የዋለ ሲሆን ዜጎች ከላይ የተጠቀሱትን አድራሻዎች በመጠቀም የኤሌክትሮኒክ የአየር ሰአት የመሙላት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
©etv