TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC “ አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም ” - ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በምክክሩ እንደማይሳተው ገልጾ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አሁንም እየተሳተፈ እንዳልሆነ፣ ኮሚሽኑ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ እንደሌለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ፓርቲው ከዚህ ቀደም በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፍ ቢጋበዝም በምክክሩ እንዳልተገኘ አስታውሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣…
" በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀርባለሁ " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ አጀንዳዎች እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል። 

ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎች አጀንዳ እንዳሰባሰበ፣ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ግን አጀንዳቸውን በማስረብ ፋንታ ከኮሚሽኑ እንዳገለሉ መግለጻቸው ይታወሳል።

የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፓርቲ ከሳምንታት በፊት በሰጠን ቃል፣ " አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም " ብሎ ነበር።

ፓርቲው ይህን ያለው ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም “ምክር ቤቱም በገዢው ፓርቲ የተሞላ ስለሆነ ገልተኛነቱ ያን ያክል አስተማማኝ አይደለም” በማለት ጭምርም ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ኮሚሽኑን ፓርቲዎችን ለማካተት ምን እየተሰራ እንደሆነ በወቅቱ ጠይቆ ምላሽ ማግኘት ሳይቻል የቆዬ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ አሁን ምላሽ ሰጥቷል።

ምን አለ ?

" ኮሚሽኑ ገለልተኛ ተቋም ነው። ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚሰሩ ሌሎች ፓርቲዎችም በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጓል። በምክክሩ አብዛኛዎቹ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፈቃደኛ ሆነው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ኦፌኮ እንደተባለው ሂደቱን ለመቀበል ፈቃኛ አይደለም። ኮሚሽኑ ፓርቲው ፈቃደኛ ያልሆነበትን ምክንያት በተደጋጋሚ ከኦፌኮ ጋር  በአካልም እንደገና በደብዳቤም እንነጋገር በሚል ጥረት አድርጓል።

 ፓርቲው ግን ፈፈቃደኛ መሆን አልቻለም። በዚህ ሂደት የኮሚሽኑ እይታ ፓርቲው በማንኛውም ሰዓት ሀሳቡን ለውጦ ለመመካከር ከመጣ ኮሚሽኑ በሩ ክፍት ነው።

ግን ኮሚሽኑ በራሱ መንገድ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆነውን አካል አስገድዶ ማሳተፍ አይችልም። ስለሆነሞ ኦፌኮ እንደ ኦሮሚያ በምክክሩ ባለመሳተፉ ኮሚሽኑ ያዝናል።

በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን። ምክክሩ ላይ ልዩነትን ይዞ እስከመጨረሻው መሄድ ይቻላል። 

የሀሳብ የበላይነት እንጂ የኃይል የበላይነት በምክክሩ ላይ  አይንጸባረቅም። በሀገራዊ ምክክሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎቻቸውን ለማህበረሰቡ ግልጽ ማድረግ ይችላሉ።

በሚስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ይስማማሉ በማይስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ደግሞ በልዩነት መሄድ ይችላሉ። ሀገራዊ ምክክሩ በባህሪው በትውልድ መካከል ከረጅም ጊዜ በኋላ የሚመጣ በመሆኑ ሂደቱን ከማበላሸት ይልቅ አሁንም ቢሳተፉ ይመረጣል።

ኮሚሽኑ አካታች ነው። ፈቃደኛ የሆኑትን አካቶ እየሰራ ነው። ፈቃደኛ ያልሆኑት እስከመጨረሻው እንዲመጡ በሩ ክፍት ነው፣ ይጠብቃል። ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖም እንደማይደርስባቸው ኮሚሽኑ ዋስትና ይሰጣል። ”

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ .pdf
“ የግል ትምህርት ቤቶችን መፈናፈኛ የሚያሳጣ፣ አለመፈለጋችንን በግልጽ ያስረዳ ረቂቅ ዐዋጅ ነው ” - የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኀበር

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ ቋሚ ኮሚቴ መራው የተባለው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ ዐዋጅ ላይ ብርቱ ተቃውሞ እንዳለው የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ገለጸ።

የማኀበሩ ፕሬዜዳንት አቶ አበራ ጣሰው፣ “ የግል ትምህርት ቤቶችን መፈናፈኛ የሚያሳጣ፣ አለመፈለጋችንን በግልጽ ያስረዳ ረቂቅ ዐዋጅ ነው ” ሲሉ ተችተውታል።

ፕሬዜዳንቱ በዝርዝም ምን አሉ ?

በረቂቁ ብዙ ነገሮች መሻሻል አለባቸው። አንኳር አንኮር የሆኑትን ለማንሳት፦ 

አንዱ ‘አንድ የግል ትምህርት ቤት ት/ቤት ሆኖ ለመቀጠል ‘የ6 ወራት የሰራተኞችን ደመወዝ በዝግ ሂሳብ ቁጥር ማስቀመጥ አለበት’ የሚለው ነው።

ይሄ ገንዘብ ከተቀመጠ በኋላ መቼ እንደሚወጣ አይታወቅም፣ Forever እንዲቀመጥ ነው እንድምታው። ምክንያቱም ገንዘቡ ከወጣ ፈቃድ ይነጠቃል።

አንደኛ የትምህርት ሥራ እንደንኛውም ድርጅት ንግድ ነው። በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በላሎች የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ነጋዴዎች ያለምንም ዋስትና ስራቸውን እያከናወኑ ነው ያሉት።

ዋስትና መሠረቱ ጥርጣሬ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች ሳይጠረጠሩ የትምህርት ሥራ ተጠርጣሪ ሆኖ ‘ዋስትና ካልያዝክ አትሰራም’ መባሉ አሳዛኝ ነው።

የገል ትምህርት ቤቶች ተርፏቸው የ6 ወራት ደመወዝ በአካውንት ማስቀመጥ አይችሉም። ስለዚህ ይሄ ረቂቅ ሕግ ሆኖ ከቀጠለ ትምህርት ቤቶች ሥራቸውን አይቀጥሉም።

ምናልባት ሌላ ንብረት ያላቸው ከባንክ ተበድረው በአካውንት ቢያስቀምጡ እንኳ 19% ወለድ ይከፍላሉ፣ ገንዘቡን በቶሎ መመለስ ስለሚያዳግት አመታት ይወስዳል። ወለዱም ዋናው ገንዘብም ተንገዳግደው ከፍለው እንኳ መቀጠል አይችሁም። ስለዚህ ይሄ ፈጽሞ የሚተገበር አይሆንም።

ሁለተኛ ማንም ሰራተኛ የትም ይስራ ዬት በአሰሪና ሠራተኛ ህግ ነው የሚዳኘው። ስለዚህ ረቂቅ ዐዋጁ ያለ ቦታው ነው የተቀመጠው። 

ሌላው የበላይ አካል ማነው? ከትምህርት ቤት ውጪ ያለ የመንግስት አካል ነው? ወይስ ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ የትምህርት አመራሮች ናቸው? የሚለው በረቂቁ ግልጽ አይደለም። 

ሕግ ይከበር እንላለን እዚህ አገር የሚያሳዝነው ነገር ግን በዬአካባቢው ራሳችን ሕግ አውጪ ሆነን ቁጭ እንላለን።

ሕግ ይከበር ስንል እኮ ሕግ የማውጣት ስልጣን ያለው አካል የሚያወጣውን ሕግ ለማክበር እንጂ እያንዳንዳችን እየፈበረክን የምንወጣባቸውን ሕጎች ለማክበር አይደለም።

ስለዚህ በሕግ አውጪው አካል የወጣው ህግ ‘ትምህርት ቤቶች እንደማንኛውም አይነት ንግድ ነጋዴዎች ናቸው’ ብሏል። ድርጅቶችምሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ናቸውና መጀመሪያ ይህንን ሲመሰርቱ እኮ በአገሪቱ የሚሰራ ሥራ አለ ብለውናል። 

የኢንቨስትመንት ፓሊሲው፣ ሕገ መንግስቱ የሚያሰራ ሆኖ ሳለ በመሃል እየመጡ እንደዚህ አይነት ችግር የሚፈጥሩ ከሆነ ያሉ ትምህርት ቤቶች አይቀጥሉም፤ ሌሎች ትምህርት ሊከፈቱ አይችሉም። ምክንያቱም በዬቦታው ያለው እንቅፋት ነው ”
ብለዋል።

ጉዳዩን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገ ይሻሻል የሚል ተስፋ እንዳለውም ማኀበሩ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“ የልብ ክፍተት ህመም ያለበት ልጄን አድኑልኝ ” - አባት

በሞጆ ከተማ የሚገኙ አቶ አማረ አለማየሁ የተባሉ አባት የአንድ አመት ጨቅላ ህፃን ልጃቸው በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃዬ በመሆኑ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ።

የህፃኑ አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

“ ህፃኑን ይዤ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተመላለስኩ። ‘የሚሆን ነገር አይደለም’ ብለው ወደ ህፃናት ልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል መርተውኝ ነበር።

በማዕከሉ ያለው ወረፋም የሚቻል አይደለም። ‘በአስቸኳይ መሰራት አለበት ክፍተቱ ከ7 ሚሊ ሜትር የበለጠ ነው’ አሉኝና ወደ ግል ሆስፒል መሩኝ።

ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ኢሉዜር ሆስፒታል ሄጄ ስጠይቅ ለማሳከሚያ 685 ሺሕ ብር ጠየቁኝ። በአካባቢዬ እርዳታ ብጠይቅም እስካሁን ምንም ገንዘብ አላገኘሁም።

የልጄ ህመም የተፈጥሮ የልብ ክፍተት ነው። ክፍተቱ በተፈጥሮ መዝጋት ነበረበት ሳይዘጋ ቀረ። ‘መደፈን ያለበት ደግሞ ግዴታ በህክምና ነው’ ተባለ።

ህመሙን ያወቅነው በ6 ወሩ ነው። አዳማ ኃይለማርያም ሆስፒታል ወሰድነወሰና የልብ ኬዝ እንዳለብ ነገሩን። ከዛም ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈር ፃፉልኝ። በሽታው እንዳይባባስበት በመድኃኒት እየተከታተለ ነው ያለው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ልበ ቀና ነው። በመረዳዳት የታወቅን ነን። ወገኖቼ አነሰ በዛ ሳትሉ በመተባበር ልጄን አድኑልኝ ”
ሲሉ ተማጽነዋል።

ለመርዳት 1000045518586 የአቶ አማረ አለማዬሁ ደስታ የኮፕራትቭ COOP ባንክ ሒሳብ ቁጥር ሲሆን 1000263542979 የንግድ ባንክ ነው።

ለመደወል እና ዝርዝር ማስረጃዎችንም ለመጠየቅ 0915846447 የእጅ ስልካቸው ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የጤናባለሙያዎችድምፅ " ከ15 ወራት በላይ የዱቲ ገንዘብ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃየን " - ጤና ባለሙያዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ15 ቀናት የዘመቻ አበልና ከአንድ አመት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመፈጸሙ ችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎቹ ዝርዝር ቅሬታ ምንድን ነው…
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

🔵 " ቸግሮናልጠምቶናል፣ ርቦናል፣ ሰልችቶናል፣ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ የዱቲ ሳይከፈለን ለ17 ወራት ስንሰራ ከመንግስት አካል ማንም ያሰበን የለም " - ጤና ባለሞያዎች

🔴 " ምንም ምላሽ የለንም። ቢሮ መጥተው ይጠይቁን " - ወናጎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት

በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ያሉ ጤና ባለሙያዎች የወራት ያልተከፈለ የዱቲ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው በመጠየቃቸው ከደመወዛቸው እንዲቆረጥባቸው መወሰኑን በመግለጽ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" ዱቲ ስላልከፈሉን የሰራነውን ገንዘብ ስለጠየቅን ብቻ ከሦስት ወራት በላይ ደሞዛችን ከ960 ብር ጀምሮ በስኬል  እየተቆረጠ ይገኛል " ብለው፣ ደመወዛቸው እንዲቆረጥ የተወሰነው የዱቲ ሥራ በማቆማቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ ህዝቡም ችግር ላይ ስለሆነ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀው፣ " ካልሆነ ለሚፈጠር ችግር ተጠያቂ አንሆንም " ሲሉ አስጠይቅቀዋል።

በዞኑ ዲላ ዙሪያ ወረዳ ጪጩ ጤና ጣቢያ ያሉ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፣ የ17 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያማረራቸውን ቅሬታ በተመለከተ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የ17 ወራት የዱቲ ክፍያ ባለመከፈሉ የጪጩ ጤና ጣቢያ ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የዱቲ ሥራ በማቆም ሕዝቡ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል።

በተደጋጋሚ ለዞኑና ለወረዳው ቅሬታ ብናቀርብም ምላሽ በመስጠት ፈንታ ባለሞያዎችን ለእስር ሲዳርግ ቆይቷል። ለሦስት ዓመት ያክል በዱቲ ክፍያ እየተከራተተ የሚገኝ የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሞያ እስከ ዛሬ ተገቢ ምላሽ አላገኘም።

በጌዴኦ ዞን በወናጎ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሞያዎች የዱቲ ጥያቄ አቅርበው ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው መብታቸው ለማስከበር የዱቲ ሥራ በማቆማቸው በየወሩ ከደሞዛዝ እንዲቆረጥ ተወስኗል።

ዱቲ ስላልከፈሉን የሰራነውን ገንዘብ ስለጠየቅን ብቻ ከሦስት ወር በላይ ደሞዛችን ከ960 ብር ጀምሮ በየወሩ እየተቆረጠ ይገኛል። መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን።

ቸግሮናል፣ ጠምቶናል፣ ርቦናል ሰልችቶናል ሞራላችን ተነክቷል መውጫ ቀዳዳ አሳጥቶናል ከኑሮ ውድነት ጋር የዱቲ ሳይከፈለን ለ17 ወራት ስንሰራ ከመንግስት አካል ማንም ያሰበን የለም " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቀው የወናጎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ቀጥተኛ ማብራሪያ በመስጠት ፋንታ፣ " ምንም ምላሽ የለንም። ቢሮ መጥተው ይጠይቁን " ብሏል።

ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስልክ ለማሳት ፈቃደኛ ባይሆኑም የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ ከዚህ ቀደም ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡትን ምላሽ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸውልን ነበር።

"ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው" የሚል ቃል ነበር የሰጡን።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ ” - የአቶ ክርስቲያን ታደለ ቤተሰብ

ለ1 አመት ከ4 ወራት በእስር ላይ ሆነው ፍትህ እየተጠባበቁ የሚገኙት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አበል አቶ ክርስቲያን ታደለ ከባድ የጤና እከል ስለገጠማቸው በሕይወት እንዲቆዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲጎበኟቸው የቅርብ ቤተሰባቸው አሳሰቡ።

ከፍትህ በፊት በሕይወት መቆየታቸው እንደሚቀድም ገልጸው፣ “ የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ቦታ ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ ” ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስበዋል።

የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ የጤናው ሁኔታ አሁንም በጣም አሳሰቢ ነው። ሰርጀሪ ተደርጎለት በሰዓታት ልዩነት ነው ወደ ማረሚያ ቤት የተመለሰው። እዛም ሆኖ የደም መፍሰስ አለበት።

ሰኞ እለት ቀጠሮ ስለነበር ሂዶ ነበር የሚፈሰው ደም ምን እንደሆነ ለማወቅ ብለው ደም ወስደዋል። ባለፈው ከአንጀቱ ውስጥ በሰርጀሪ የወጣውንና የተወሰደውን ደም ውጤት ለማወቅ ለነገ ሐሙስ ተቀጥሯል።

ህመም አለው። ‘ከፍተኛ ህመም ነው የሚሰማኝ’ ነው የሚለው። ለጊዜው የሚያስታግስለትን መድኃኒት ነው የሚጠቀመው።

ከዚህ ቀደም አያመውም ነበር። አዋሽ አርባ ከሄደ በኋላ ነው የታመመው። አሁን ሲነግረን አሟቸው ከአዋሽ ወደ አዲስ አበባ አምጥተዋቸው ነበር። የዛኔም ምርመራና በቂ ህክምና አላደረገም። 

የዛኔ አብረዋቸው ከአዋሽ የመጡ አካላት ፕራይቬሲያቸውን በሚጥስ ሁኔታ ‘አብረን ገብተን እንመለከታለን ህክምናውን’ በሚል አለመግባባት ተፈጥሮ ህክምና ሳያገኙ ተመልሱ።

የዛኔ ቢታከም መታጠብ ነበር የሚጠበቅበት ለሰርጀሪም አይደርስም ነበር። ህመሙ በድርቀት የሚመጣ ሲሆን፣  አንጀቱ ውስጥ ሌላ የቋጠረ ነገር ነበር።

እሱንም አሁን ሀኪሞቹ ለማብራራት ቆርጠው ካወጡት በኋላ ለምርመራ ተወስዷል። ነገ ነው ውጤቱ የሚገለጸው።

የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ በሚገርም ሁኔታ በጣም ረጅም፣ ረጅም የሆነ ቀጠሮ ነው የሚሰጠው። አሁንም ገና ለጥር 13 ነው ቀጠሮ የተሰጣቸው።
 
እንደ ቤተሰብ ከምንናገረው በላይ እጅግ በጣም ከባድ ነው ያለንበት ሁኔታ። እሱ በነበረበት ወቅት ጥሩ በሚባል ሁኔታ ላይ ነው የነበርነው፣ አሁን ላይ እንደዛ አይደለም።

ፍትህ እንጠብቃለን። ተስፋ አንቆርጥም። ግን አሁን ያለው ሂደት በፍትህ ስርዓቱ ክርስቲያንንም ተስፋ እንዳቆረጠው ነው በተደጋጋሚ የሚነግረን፣ እኛም የምናየው።

የደም መፍሰሱ እንኳ አልቆመለትም በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ነው ያለው። የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ቦታ ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ።

በቂ የሆነ ህክምና እንዲያገኝ ያለበትን ሁኔታ ተረድተው የሰብዓዊ መብት አካላት እንዲጎበኙት እንፈልጋለን ”
ሲሉ ተማጽነዋል።

(የአቶ ዮሐንስ ቧ ያለው የቅርብ ቤተሰብ ለቲክቫህ ያቀረቡት እሮሮ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ ” - የአቶ ክርስቲያን ታደለ ቤተሰብ ለ1 አመት ከ4 ወራት በእስር ላይ ሆነው ፍትህ እየተጠባበቁ የሚገኙት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አበል አቶ ክርስቲያን ታደለ ከባድ የጤና እከል ስለገጠማቸው በሕይወት እንዲቆዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲጎበኟቸው የቅርብ ቤተሰባቸው አሳሰቡ። ከፍትህ በፊት በሕይወት መቆየታቸው…
“ አሁንም በጣም ከፍተኛ በሆነ ህመም ውስጥ ነው ያለው ” - የአቶ ዮሐንስ ቧያለው የቅርብ ቤተሰብ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ዮሐንስ ቧያለው መጀመሪያ ታስረውበት ከነበረው በአዋሽ አርባ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አብረዋቸው ካሉ እስረኞች ጋር ተዘዋውረው ፍትህ እየተጠባበቁ ቢገኙም የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የቅርብ ቤተሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

አቶ ዮሐንስ ከታሰሩ 1 አመት ከ5 ወራት አስቆጥረዋል።

ልጆቻቸውና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ሲተዳደሩ የነበረው በአቶ ዮሐንስ አማካኝነት እንደነበር የገለጹት የቅርብ ቤተሰባቸው “ በጣም ከፍተኛ ችግር ላይ ነን ” በማለት፣ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

እኝሁ የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

“ አሁንም በጣም ከፍተኛ በሆነ ህመም ውስጥ ነው ያለው። ደሙም ከመፍሰስ አልቆመም። ምክንያቱም አዋሽ አርባ እስር ቤት እያሉ በወቅቱ ስላልታከሙ ነው።

ህመሙ የጀመረው አዋሽ አርባ እስር ቤት እያለ ነው። እዛ እያለ ታመመ። በጣም እንደታመመ እዛ ላሉት አካላት ቢነግራቸውም በሰዓቱ ወደ ህክምና አልወሰዱትም ነበር።

በኋላ ላይ በጣም ሲታመምባቸው እሱንና አቶ ክርስቲያን ታደለን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በድብቅ ይዘዋቸው ገቡ። ከዚያ በኋላ ዶክተሮቹ ሊያክሙ ሲሉ አብረው የሄዱ ጥበቃዎች ‘የሚታከሙትን ነገር ገብተን እናያለን’ አሉ። ይሄ ደግሞ ፕራይቬሲን መጣስ ነው።

በመሆኑም ‘በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንታከምም ይቅርብን እንጂ’ ብለው እንደተመለሱ ነው አሁን ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ የነገረን። 

እንደገና ከአዋሽ አርባ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ሜክሲኮም ሲገቡ ሲጠይቁ ነበር ‘ውስጣችን ደኀና አይደለም መታከም አለብን’ እያሉ። ያኔም መልስ አልተሰጠውም።

ቃሊቲም እያለ ‘እባካችሁ አሳክሙኝ እየታመምኩ ነው፣ የምመገበው ምግብ እየተስማማኝ አይደለም’ እያለ ሲጠይቅ ነበር። ከቤቱ ነው ምግብ የሚሄድለት ግን ምንም አይነት ምግብ ውስጡ አይረጋም፣ ይታመም ነበር።

አሁን በብዙ መከራ ባለፈው ለህክምና ፈቅደውላቸው ሄዱ። በጣም በኃይለኛው ከመቆጣት አልፎ አንጀቱ አብጦ ነበር። ያ በአፋጣኝ በሰርጀሪ ተቆርጦ መውጣት ነበረበት። ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር በቼካፕ ቀን ነው ወዲያው ‘ሰርጀሪ መሰራት አለበት’ ተብሎ የነበረው።

ግን ሰርጀሪ ለመሰራት ሁለት ቀናት ምግብ ሳይመገብ መቆዬት ነበረበት። ለሁለት ቀን ምግብ አቁሞ በሦስተኛው ቀን ሰርጀሪ ተሰራ። ሰርጀሪም አድርጎ ወዲው ተመለሰ። አሁንም ገና ክትትል ያስፈልገዋል። ለነገ ቀጠሮ አለው።

ውስጡ ያለው ነገር ሰላም መሆኑን፣ ወደ ቦታው መመለሱን ነገ ነው የምናውቀው። በአንዴ የሚታወቅ ነገር አይደለም። ምክንያቱም ቶሎ ባለመታከሙ ውስጡ በጣም ተጎድቷል።

የፍርድ ቤቱ ሁኔታ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት ፍትህ አልተገኘም። ምንም አይነት መልስም እያገኘ አይደለም። እስካሁን ‘ምርመራ ላይ ነን’ ነው የሚሉት።

ምንም ያቀረቡት ነገር የለም መመላሰስ ብቻ ነው እንጂ አፋጣኝ ፍትህ አልተገኘም። 

ቤተሰቡ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው። ቤተሰብ እሱ በመያዙ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንድንገባ ተገደናል። ምክንያቱም ሙሉ ቤተሰቡን የሚያስተዳድረው እሱ ነበር።

ልጆችና ሌሎች በሱ ስር የሚተዳደሩ ቤተሰቦች አሉት። እሱ በመታሰሩ ያ ሁሉ ተበትኗል። በጣም ችግር ውስጥ ነን። ዴሞክራት ነኝ ከሚል መንግስት ፍትህ ይጠበቃል።

እሱም እያለ ያለው ‘ፍትህ ይሰጠኝ’ ነው። ስለእውነት ነው እያወራ ያለው፣ ስለእውነት ነው እየታገለ ያለው። ቤተሰብና ልጅ በቶኖ በጣም ኃይለኛ እንግልት ላይ ነን በእውነት ”
ብለዋል።

አቶ ክርክቲያን ታደለና አቶ ዮሐንክ ቧ ያለው አዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት  ህመም ሲጀምራቸው በወቅቱ ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት በሽታ ተዳርገው ሰሞኑን ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው፣ ነገም የሀኪም ቀጠሮ እንዳላቸው ቤተሰቦቻቸው ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አሁንም በርካታ ሰዎች ከኢትዮጲያ እየጎረፉ ይገኛሉ  !! " - በስፍራው የሚገኝ የአይን ምስክር በርካታ የሀገራችን ወጣቶች " ታይላንድ ስራ አለ " እየተባሉ ወደ ማይናማር ድንበር ቦታ ተወስደው ካምፕ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉና በዓለም አቀፍ የኦንላይ ማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እየተደርጉ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዬጵያ ለረጅም ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል። አሁንም በርካታ ወጣቶች እዛው ናቸው። ከአደገኛው…
#Update

🚨 “ ግብረሰዶም ወደ ሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል” -  በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ

➡️ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኑሮን ለማሻል በሚል ወደ ታይላንድ የሄዱና በኃላም ወደ ማይናማር የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን በጋንግስተሮች እጅ ወድቀው ከውላቸው ውጪ  ህገወጥ የዶላር ማጭበርበር ሥራ ለመስራት እንደተገደዱ ቤተሰቦቻቸው ጭምር መግለጻቸው ይታወሳል።

የታጋቾቹ ወላጆች ያቋቋሙት ኮሚቴም፣ “ ልጆቻቸን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርል ” ሲል በቅርቡ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ማሳሰቡ አይዘነጋም።

በወቅቱ ምላሽ የጠየቅነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ፣ ቶኪዮ ባለው ኤምባሲ አማካኝነት ንግግር እየተደገ መሆኑን ገልጾ፣ “ ልጆቹ የማይናማር መንግስት የሚቆጣጠረው ቦታ ላይ አይደለም ያሉት ለዛ ነው ችግሩ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ” ብሎ ነበር።

የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የኢትዮጵያዊያኑ ወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ግብረሰዶም ወደሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ገልጿል።

ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

“ ልጆቻችን ገና አልወጡም። ወደ ሦስት ሀገራት ዜጎቻቸውን አስወጥተዋል። የ18 የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ልጆች ናቸው እየተሰቃዩ ያሉት።

ሦስቱ ሀገራት ከእነዛ ጋንግስተር ቡድን ተነጋግረው አቅጣጫዎችን አስቀምጠው የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው ነው ልጆቻቸውን ያስወጧቸው። 

በአጋጣሚ ከወጡት ከፊሊፒን ዜጎች ወክሎ ሲንቀሳቀስ የነበረን ሰው አድራሻ አግኝተን (የታይላንድ ፓሊስ ኮማንደር ነው) በምን አይነት ሁኔታ ልጆቻቸውን እንዳስወጡ ኮንታክት እያደረግን ነበር። ያንን ኢንፎርሜሽን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመስጠት ሞክረናል።

ሌሎች ዜጎች ስለወጡ በአሁኑ ወቅት ልጆቻችን ብቻቸውን በግላጭ ስለቀሩ ስቃዩ በርትቷል። ጭራሽ እንዲያውም በግብረሰዶም ወደምታትታወቀው ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል። ፈጣሪ ይጠብቅልን እንጂ።

እጅ በእጅ ነው ልጆቹን አስተላልፈው የሚሸጡትና ይሄ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ስለሆነ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትኩረት በመስጠት ልጆቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሌሎችንም ሀገራት ወዳሉበት ቀርቦ በተለይ ከታይላንድ መንግስት ጋር ተነጋግሮ መፍትሄ ይስጠን።

ማይናማርን ማነጋገር እንዳለ ሆኖ የታንላንድን መንግስት ማነጋገር ለሁለት ነገር ይጠቅማል። ለክፍያ የሚጠይቁትን ገንዘብ በማስቀረት እንዳይታሰሩ ለማድረግና ካሉበት መከራ እንዲወጡ ለማድረግ።

ከጋንግስተሮቹ ጋር ቀረቤታ አለው ተብሎ ነው የሚታሰበው የታይላንድ መንግስት። ሌሎች ሀገራትም ይህንኑ ሲስተም ነው የተጠቀሙት የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን መንገድ ተጠቅሞ ልጆቹ የሚወጡበትን መንገድ እንዲያመቻች በአጽንኦት እንጠይቃለን”
ሲል አሳስቧል።

ወደ 111 ወላጆች ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለአንድ አመት ተመላልሰው መፍትሄ ባለማግኘታቸው ትላንት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባነር ይዘው ከሚኒስትሮች መፍሄ እንደጠየቁ፣ ሚኒስቴሩም ከኢትዮጵያ ሰዎችን ለመላክ እንደተወሰነና በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ቃል እንደገባ ኮሚቴው አስረድቷል።

ምን አዲስ ነገር አለ? ጉዳዩ ከምን ደረሰ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ “አዲስ መረጃ ካለ አጋራለሁ” ብሏል። (ጉዳዩን እስከመጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🚨“ አቶ ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ የሐኪም ቀጠሮ ነበራቸው ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” - ቤተሰቦቻቸው

🔴 “ በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ወይስ በሕይወት የመኖር መብት ነው የሚቀድመው ? ” - ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ

አዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ባደረባቸው የጤና እክል በወቅቱ ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት ህመም የተዳረጉት አቶ ክርስቲያን ታደለና አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ሰሞኑን የቀዶ ህክምና ተደርጎላቸው ወዲያው ወደ ማረሚያ ቤት በመመለሳቸው ደም እየፈሰሳቸው እንደሆነ፣ ዛሬም የሀኪም ቤት ቀጠሮ እንደነበራቸው ቤተሰቦቻቸው ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ለዛሬው ሀኪም ቤት ቀጠሯቸው ሄዱ ?

ሁሉቱም ዛሬ (ሐሙስ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ/ም) ለቸካፕ ቀጠሮ የነበራቸው ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ እንዳልወሰዳቸው ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። 

አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ተደጋጋሚ የደም መፍሰስ እያጋጠማቸው በመሆኑ ቁስላቸው ለኢንፌክሽን እንዳይጋለጥ ለቸካፕ ለዛሬ በመቅረዝ ሆስፒታል ቀጠሮ እንደነበራቸው አስረድተዋል።

ቀጠሮው ስለሰርጀሪው ፣ ለቅድመ ካንሰር ምርመራ ውጤቱ፣ ለቀጣይ ተከታታይ ህክምና የሚሰጣቸውን የቀጠሮ ቀን የሚውቁበት እንደነበር ገልጸው፣ “ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” ሲሉ ወቅሰዋል።

የእነ የአቶ ክርስቲያንና ዮሐንስ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ በበኩላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

በቀጠሮው አለመሄዳቸው ጉዳት ያመጣል። ለሁለት ነገር ነው በምርመራ ላይ ያሉት። አንደኛ በፊንጢጣ በኩል ኦፕራሲዮን ተደርገው ደም እየፈሰሳቸው ነው።

አዋሽ አርባ በነበሩበት ወቅት የአንጀት ድርቀት ገጥሟቸው ባለመታከማቸው በኋላ ላይም በሽብር ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ በብዙ ጭቅጭቅ ማረሚያ ቤቱ ወደ ሀኪም ቤት ቢሄዱም የሰርጀሪ ደሙ አልቆመም። 

ሆስፒታሉም ‘በዚህ ቀን ይዛችሁ ኑ’ ብሎ ፐርስክርፒሽን ሰጥቷል። ይሄ ህመም ነው የጤና ጉዳይ ነው። የዛሬ የሆስፒታል ቀጠሮ የሚፈሰውን ደምና የቁስሉን ምንነት ለማረጋጠጥ ነበር።

ሁለተኛ የአንጀታቸውን በተመለከተ ኦፕራሲዮን ለማድረግ የካንሰር ምርመራ አድርገዋል። ውጤት ለማወቅ ነበር ቀጠሮው። ግን ከቤተሰቦቻቸው የሰማሁት በቀጠሯቸው መመሠረት ሀኪም ቤት እንዳልወሰዷቸው ነው።

ማረሚያ ቤቱ ያቀረበው ምክንያት ‘እስረኞቹን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወርን በመሆኑ አጃቢና መኪና ስሌለ ነው’ በሚል ነው። ይሄን በተመለከተ ፍርድ ቤት ምስክር በምናሰማቸው በነ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ዐቃቢ ህግ ምስክር እያሰማ እዛው ውለናል ከትላንትና ትላንት ወዲያ።

‘እስረኛ እያዘዋወርን ስለሆነ አናመጣቸውም’ የሚል ወረቀት ቢያስገቡም ‘አይቻልም’ ብሎ ፍርድ ቤቱም ትዕዛዝ ስለሰጣቸው ትላንትናም አምጥተዋቸዋል። ትላንትም ምስክር ሰምተናል፣ ዛሬም ምስክር ሰምተናል።

ታዲያ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሆን ብቻ ነው እንዴ እነርሱ የሚያከብሩት ? በእርግጥ እስረኛ እያዘዋወሩ እንደሆነ ይታወቃል። ግን ምስክር ለመስማት ‘አምጡ’ ሲባሉ ነው ተገደው ማምጣት ያለባቸው ወይስ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ሲሆን ነው አፋጣኝ እርምጃ ወስደው ማምጣት ያለባቸው ?

መቼም የማረሚያ ቤት አስተዳደር ብዙ ጠባቂዎች አሉ። እንደምንም ተፈልጎም መኪናም ተከራይተውም ቢሆን የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ በቀጠሯቸው መሠረት አምጥተው ማሳከም ነበረባቸው። 

ስለዚህ ድርጊቱ አግባብ አይደለም። ይሄ በሕይወት የመኖር መብትንም የሚጣረስ ነው። እነዚህ ሰዎች አሁን ደም እየፈሰሳቸው ነው በቀጣይነት ደሙ ቢፈስስ? የቅድመ ካንሰር ምርመራ ሕይወት ወደማሰጣት ቢደርስስ ? 

በመሆኑም በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ነው ወይስ በሕይወት የመኖር መብት የሚቀድመው? በሕይወት የመኖር መብት ነው መቅድም ያለበት ”
ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ግብር

🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች

🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

" በ2015 ዓ/ም ነበር ጥናቱ የተጠናው ፤ ከዛ 'ተግባራዊ አይሁን፣ ትክክል አይደለም' ተብሎ የተቀመጠ ጥናት ነው አሁን መመሪያ ተደርጎ በትዕዛዝ የወረደው " ሲሉ ነው የተናገሩት።

አስመጪዎቹ ስለዝርዝር ቅሬታቸው ምን አሉ ?

" አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን አላስፈላጊ ግብር እየጠየቀን ነው። ይሄን የሚያደገው 'ሲስተም አዘጋጅቻለሁ' በሚል ነው።

አዲሱ ሲስተም የስሪት፣ የተመረተበትና የመጣበት አገር ይጠይቃል፣ በጥናት መልክ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን ብሎ በአዲስ አበባ በሁሉም ቅርንጫፎች ኤክስኤል ሰርቶ አውርዶ ሥሩ ብሏል።

'ከጉምሩክ ዴክላራሲዮን ላይ ሒሳቡ ሲሰላ ከ45 በመቶ በላይ የሆነ ትርፍ እያተረፋችሁ ነው’ በሚል ነው አዲስ አሰራር ያመጣው።

ይህ መመሪያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተለዬ፣ ፌደራልና ክልል ላይ የሌለ፣ በአዲስ አበባ ብቻ፣ የመኪና አስመጪዎችን ብቻ በተመለከተ የተዘጋጀ መመሪያ ነው።

በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠየቅነው ግብር አላስፈላጊ፣ ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ነው። ምክንያቱም ግብር በህግ ነው እንጂ በጥናት አይደለም የሚከፈለው። 

ግብር ሲከፈል ህግ ተረቆ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ነው። ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የግብር መመሪያ የሚያወጣው  ደግሞ ገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

ይሄን አዲስ መመሪያ ግን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በራሱ በደብዳቤ መልኩ ነው ወደታች ያወረደው ከአሰራር ውጪ በሆነ መልኩ


እስከዛሬ ጉምሩክ ባስቀመጠው መሠረት ከፍተኛው ጣራ 9% ተደርጎ እኛም 4ም፣ 5ም% አተረፍን ብለን አቅርበን ነበር የምንፈፍለው።

አሁን ግን ቢሮው ሌላ የራሱን ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይህንን መመሪያ አወረደ በትዕዛዝ መልክ። መመሪያው የወረደው ‘ከ45 በመቶ በላይ እያተረፋችሁ ነው የዚህን ግብር ክፈሉ’ በሚል ነው።

ከዚህ ቀደሙ ግብር ጋር ሲነጻጸር 5% አትርፌአለሁ ብለሸ አሳውቆ ግብር ሲከፍል የነበረን ሰው ‘45% ታተርፋለህ’ ማለት በጣም ብዙ እጥፍ ነው። የህግ አግባብ የለውም አሰራሩ። 

በፌደራል ደረጃ ንግድ ፈቃድ አስመጪዎች ያላቸው መኪና መሸጫ አላቸው። የእነርሱ በኖርማሉ ነው፣ እነርሱን አይመለከትም መመሪያው። ክልል ያሉትንም በተመሳሳይ አይመለከትም። 

አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ክፍለ ሀገርም ሆነው የክፍለ ሀገር ፈቃድ አውጥተው (ለምሳሌ የክልል፣ የፌደራል ፈቃድ ያላቸው) ከኛ ጋር ተመሳሳይ መኪና የሚሸጡ አሉ።

እነርሱን ግን ይሄ አዲሱ የግብር መመሪያ አይመለከትም። አንድ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ አይነት መኪና እየሸጡ እያሉ
ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው።

የፌደራል ገቢዎች የማያውቀውን ተመን እንዴት አንድ የከተማ አስተዳደር በራሱ ያወጣል? ይሄ አሰራር የህግ ግራውንድ የለውም። ቅሬታችን ይሰማልንና ትግበራው ይስተካከልልን”
ብለዋል።

አዲስ አበባ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጭዎች ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሰራር ወርዶ ከመጠን ያለፈ ግብር ተጠየቅን ለሚለው ቅሬታቸው ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥያቄ አቅርበናል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ?

" በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው።

የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለውም። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። ዋናው ዓላማ ግን ከፍተኛ የሆነ የታክስ ስወራ ስላለ ያን ለማስቀረት ነው።

ከተማው ማንኛውም መኪና የሚገዛ ሰው ስንት ብር ነው የገዛው? በትክክል በገዛውና በከፈለው ገንዘብ ልክ ደረሰኝ ተሰጥቶታል ወይ? በስት አካውንት ነው ገንዘብ እንዲያስገባ የሚጠየቀው? የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው። 

ስለዚህ የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

እዚህ ላይ ልዩነት አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መጥቶ ልንወያይ እንችላለን በራችን ክፍት ነው "
ብለዋል።

(ኃላፊው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ላቀረብንላቸው ጥያቄዎች የሰጡን ሙሉ ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብር 🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች 🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ…
#ግብር #ተሽከርካሪዎች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከተሽከርካሪ አስመጪዎች ለቀረበበት ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ሙሉ ምላሽ ምንድን ነው?

" አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ የታክስ ስወራ አለባቸው የሚባሉ ዘርፎች ተለይተው ጥናት ተደርጓል፡፡

አንዱ ከቋሚ ንብረት፣ ከቤት፣ ከሪልስቴት ጋር ሽያጭ ጋር፣ ሌላው ደግሞ ከመኪና ጋር የተገናኘ ጥናት ነው፡፡ 

እነዚህ ጥናቶች 2015 ዓ/ም ተጠንተው ተጠናቀው 2016 ዓ/ም ሚያዝያ ጀምረው ተግባራዊ እንዲደረጉ በከተማ አስተዳደሩ ተወስኖ ሰርኩላር ተላልፏል፡፡ 

የቤትና መኪና ሻጮችን በተመለከተ ማለት ነው፡፡ የቤት ወዲያውኑ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ከመኪናም ሽያጭ ጋር በተገናኘ የመኪና ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ሁለት ቢሮዎች ናቸው በዋናነት ግብር የሚሰበስቡት፡፡ 

አንዱ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ ያለው የከተማው የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡ 

በጥናት እንዲጠና የተደረገው  ከተማው የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች የሚሸጡበት ዋጋና ተሸጠዋል ተብሎ ለገቢወዎች ቢሮ በሚቀርበው የገንዘብ መጠን መካከል በጣም ሰፊ የዋጋ ልዩነት በመኖሩ ነው።

ጥናቱን ከፌደራልም ከአዲስ አበባም የተለያዩ ባለሙያዎች ናቸው ያጠኑት፡፡ በገበያው ዋጋና ለገቢዎች ቢሮ በሚቀርበው ሪፖርት መካከል በጣም ሰፊ ሆነ የዋጋ ልዩነት እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።

10 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ3 ሚሊዮን ብር፣ በ6 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ1 ሚሊየን ብር እየሆነ ያለው፡፡ በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡  

ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው። ጥናቱ በወቅቱ የነበረውንም የዋጋ ግሽበት ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተያያዘውንም ጉዳይ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። 

ስለዚህ ተግባራዊ መደረግ የነበረበት አምና ነው፡፡ 2016 ዓ/ም በዚሁ ነው መሰራት የነበረበት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት 2016 ዓ/ም ሳይተገበር ቆይቷል፡፡ 

ከተማ አስተዳደሩ ‘2016 አለመተግበሩ ትክክል አይደለም፡፡ በ2016 ዓ/ም የግብር ዘመን ላይ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ አሁን ግን የ2017 ዓ/ም ግብር በሚከፈልበት ጊዜ ህጉ መከበር አለበት’ የሚል አሰራር ስለተቀመጠ ያንን አሰራር ነው የተገበርነው፡፡ 

በተከታታይ አስመጭዎቹ ሰዎችን ወክለው የሂሳብ ባለሙያዎቹ ጭምር መጥተው በተሰራው ፎርሙላ ላይ ቁጭ ብለን አንድ በአንድ ተወያይተናል፡፡ ተግባብተናል ብዙ ልዩነት አልነበረም።

በውይይታችን በተለይ ቴክኒካል የሆነውን ነገር የሒሳብ ባለሙያዎቻቸው ባሉበት ተወያይተን እነሱን የሚያከስር እንዳልሆነ ነገር ግን የግብር ስወራውን ለመከላከል የተዘጋጀ ፎርሙላ እንደሆነ ከውጭ ምንዛሬ ጋር ያለውንም ችግር ግምት ውስጥ እንዳስገባ በመድረኩ ላይ ተግባብተናል፡፡ 

አንድ ሰው መኪና ሲገዛ ደረሰኙን ይዞ ታርጋ ለመውሰድ ወይም ለማዞር በሚሄድበት ጊዜ አምና ጭምር መኪና ሻጮቹ የሰጡትን ደረሰኝ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን ‘አልቀበልም’ እያለ በፎርሙላው መሰረት እየሰራ ትክክለኛውን እያሰላ ከመኪና ገዥዎቹ አስፈላጊውን ክፍያ ሲቀበል ነው የነበረው፡፡ 

ሻጮቹ የሸጡት የገንዘብ መጠን ገዢው ታርጋ ለመሸጥ በሚሄድበት ጊዜ ተቀባይነት እንዳላገኘ እዛ በትክክለኛው ዋጋ የስም ዝውውር እንደፈጸመ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ አምናም እነሱ ላይ አለመተግበሩ ካልሆነ በስተቀር አዲስ የመጣ ነገር አይደለም፡፡  

ምንም አስመጪዎቹን የሚጎዳ፣ የሚያከስር ነገር የለውም፡፡ በጣም መሠረታዊ ሚባሉ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ ያስገባ አሰራር ነው፡፡

እንደ ጉዳት እየወሰዱት ያለው አምና ስንከፍል በነበረው አይነት ብቻ እንክፈል ለምን ተጨማሪ ክፍያ እንከፍላለን? ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ጥያቄ ነው፡፡ 
ይሄ ደግሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ የታክስ ስወራን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚሰራውን ይህን ሁሉ ልማትና ህዝብ ጥያቄ የሚመልሰው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ ነው፡፡ 

እዚህ ገቢ ውስጥ የግብር ስወራውን የመከላከል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዋጋ ጥናትን በተመለከተ በግልጽ በታክስ አስዳደር አዋጁ ላይ ስልጣን ለገቢዎች ቢሮ ተሰጥቷል፡፡ ግልጽ ነው፡፡

አዋጁም ይሄ በዋናው የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ የሚባል አለ በሱ አዋጅ ላይ በግልጽ የተቀመጠ፣ አንቀጽ 3 ላይ ለገቢዎች ቢሮ ተሰጠ ስልጣን አለ "
ብሏል።

አንዱ የአስመጪዎቹ ቅሬታ መመሪያውን ማውረድ ያለበት የገቢዎች ሚኒስቴር ነው እንጂ ቢሮው አይደለም የሚል ነውና የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው ? ሲንል ለቢሮ ኃላፊው ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

ምን ምንላሽ ተሰጠ ?

" አይ አይልም። የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የተሰጠ ስልጣን በታክስ አስተዳደር ተቀምጧል። የፌደራል ግብር ከፋይ የሚባሉ አሉ። አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ አለ። 

በአዲስ አበባም ሆነ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ላይ PLC የሆኑ ግብር ከፋዮች ለፌዴራል መንግስት ነው ግብር የሚከፍሉት። እነሱን የተመለከተ አሰራር ሊያወርድ ይችላል ፌደራል መንግስት። 

የአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ አሰራር መዘርጋት፣ ዋጋ ማጥናት፣ በዋጋ ጥናቱ መሰረት ግብር እንዲሰበስቡ የማድረግ ስልጣን ደግሞ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ መሆኑ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጧል። "

" ግብር የሚከፈለው ህግ ወጥቶ በህግ ደረጃ ነው እንጂ ጥናት ተጠንቶ አይደለም፣ ይሄ ጥናት ደግሞ 2015 ዓ/ም ላይ ‘ተጠንቶ አይሆንም ትክክል አይደለም’ በሚል ነበር ቆይቶ የነበረው፣ አሁን ለአዲስ አበባ መኪና አስመጪዎች ብቻ በሚል ጥናትን መሰረት ተድርጎ የወጣ፣ ህግን መሰረት ያላደረገ ነው " የሚል ቅሬታም ቀርቧል። የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ትጥቷል።

ቢሮው በምላሹ ምን አለ ?

" በታክስ አስተዳደር አዋጁ ላይ በግልጽ የተቀመጠው በማንኛውም ምርት፣ አገልግሎት፣ ሽያጭ በሚከናወንበት በማንኛውም እቃ ላይ የገቢዎች ቢሮ ዋጋ ማጥናት፣ ዋጋን Set የማድረግ፣ በዚህ ዋጋን በመቀነስ የሚመጣን የግብር ስወራ ለመከላከል ዋጋ መተመን እና በዚያ መሰረት ግብር ማስከፈል እንደሚችል ተቀምጧል።  

ስለዚህ መመሪያም፣ ሌላ አዋጅም አያስፈልገውም አሰራር ብቻ ነው መዘርጋት የሚያስፈልገው። ይጠናል ያ የተጠናው ጥናት ወደ አሰራር ይቀየርና ተግባራዊ ይደረግ ተብሎ ለየቅርንጫፍ ይወርድና ነው ተግባራዊ የሚደረገው።  

ይሄ ነው አሰራሩ። ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለው። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። "

(ገቢዎች ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia