TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በከፋ ችግር ውስጥ ያሉ የቡለን ወረዳ ተፈናቃዮች ! በቡለን ወረዳ "በኩጂ ቀበሌ" በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቻችን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ እየተናገሩ ነው። የቡለን ወረዳ አስተዳደር ለዜጎቻችን አስቸኳይ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ በማድረግ ወገንን እንታደግ ሲል ጥሪ አቅርቧል። እስካሁን ለተፈናቃዮች ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች ምንም የተላከ የምግብ ድጋፍ የለም። መንግስትም…
#Metekel

በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው።

• ስንዴ 875 ኩንታል፣
• ዱቄት 1751 ኩንታል ፣
• ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት 7 የሚደርሱ መኪናዎች ድጋፉን ጭነው ወደ ቦታው አቅንተዋል።

ከሰሞኑ በቡለን ወረዳ በተፈፀመው የንፁሃን ጥቃት 35 ሺህ ዜጎቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በቡለን ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።

በአጠቃላይ በመተከል ዞን 56ሺ የሚደርሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

[በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን]
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው። • ስንዴ 875 ኩንታል፣ • ዱቄት 1751 ኩንታል ፣ • ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።…
#Metekel

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የፌዴራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ያደረገው ድጋፍ አየተሠራጨ ይገኛል።

ድጋፉ በቡለን ወረዳ ተፈናቅለው ቡለን ወረዳ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሠራጨ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ከ2 ሺህ 180 ኩንታል በላይ የስንዴ ፣ የበቆሎ ፣ የፋፋ ዱቄት በቡለን ወረዳ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በመድረስ ላይ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

ሌፍተናንት ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በጠ/ሚሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን አስታውቀዋል።

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፣ የንጹሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት እና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሌፍተናንት ጄኔራሉ ተናግረዋል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Metekel

በመተከል ዞን ከ97 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ከ58 ሺ በላይ ዜጎች ግልገል በለሰ ከተማ ይገኛሉ ፤ 39 ሺህ 679 ተፈናቃዮች በአማራ ክልል አዊ ብሔርስብ አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ።

ዜጎች ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ ያተደረገ ድጋፍ ፦

• በግልገል በለሰ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ33 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ ፣ 4 ሺ 38 ኩንታል ዓልሚ ምግብ እና 187 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

• አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ሺህ 404 ኩንታል ስንዴ እና 10 ሺህ 316 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ለአብመድ አሳውቋል። #MinistryOfPeace

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Metekel

በድባጤ 'ዚጊ ቀበሌ' ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ንፁሃን ሲገደሉ አንድ ሰው ቆስሏል።

ጥቃቱ በትላንትናው ዕለት ማለዳ ላይ እንደተፈፀመ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።

የሟቾች የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ አንደኛው ባለትዳር እና 5 ልጆች አባት እንደሆኑ ወንድማቸው ትላንት ምሽት በተሰራጨ መደበኛው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ሲናግሩ ተደምጠዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ ጥቃቱን አረጋግጠዋል ፥ እሳቸውም በድባጤ ወረዳ በዚጊ ቀበሌ ወደ ማሳቸው በሚሄዱ 3 ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ 2ቱ መገደላቸውን አንደኛው መቁሰሉን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ትላንት የመተከል ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር በዞኑ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Metekel

በመተከል ዞን "ሽፍቶች" ተቆጣጥረውት የነበረ ቦታ እንደነበር እና ቡድኑ ላይ በተወሰደ እርምጃ ቦታዎቹን ማስለቀቅ እንደተቻለ ተሰማ።

በዞኑ በሽፍቶች ቁጥጥር ስር የነበሩት ቦታዎች የትኞቹ እንደነበሩ ግን በግልፅ አልተብራራም።

ይህ መረጃ ይፋ የሆነው ዛሬ በዶ/ር ዐቢይ ተቋቁሞ የመተከል ዞንን የፀጥታ እና የሕግ ማስከበር ሥራ የተረከበው ግብረ-ኃይል የሁለት ሳምንት ስራውን መገምገም በጀመረበት ወቅት ነው።

ግብረ-ኃይሉ በመተከል ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የወረዳ እና ቀበሌ የሥራ ኃላፊዎች እንዲነሱ፣ ወንጀል ያለባቸውም በሕግ እንዲጠየቁ እየተደረገ ነው ብሏል።

አዲስ የሚመረጡ የሥራ ኃላፊዎች ሕዝብ መምራት የሚችሉት በሕዝብ ፊት ቀርበው ተቀባይነት ሲያገኙ ብቻ ነው ተብሏል።

ትምህርት ቤቶችን የመማር ማስተማር ማስጀመር፣ የጤና ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ የቀጣዮቹ ሁለት (2) ሣምንታት ሥራ እንደሚሆንም ተግልጿል።

በጠ/ሚሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የፀጥታ እና የሕግ ማስከበር ሥራውን በ1 ወር ጊዜ አጠናቅቆ ለአስተዳደሩ ለማስረከብ ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በዚህ ጉዳይ ያሰራጨው መረጃ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው፥ንብረትም እየወደመ ነው።

• አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ታኅሳስ 26 በጭላንቆ ቀበሌ 7 ንፁሃን ዜጎች እና 4 የመከላከያ አባላት ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን በቅዳሜው እትሙ አስነብቧል።

• በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ቦታ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

• ጉባ ወረዳ ትናንት በደረሰ ጥቃት 11 ሰዎች ተገድለዋል።

• ትላንት ለሊት ድባጤ ወረዳ 'ቆርቃ ቀበሌ' በታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት ከ60 በላይ ንፁሃን መገደላቸውን የአይን እማኞች እና ከጥቃቱ ያመለጡ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ዘግቧል።

ከ25 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ንብረት እንደወደመ ተነገሯል።

ቪኦኤ ሬድዮ ፥አንድ የአካባቢው የኮማንድ ፖስት አባል ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጠዋል ብሏል። ነገር ግን የደረሰውን ጉዳት መጠን አልገለፁም፤አላረጋገጡም፣ መረጃም አልሰጡም።

የአካባቢው የቲክቫህ አባላት በተፈፀመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከመቶ በላይ ነው ብለዋል።

• ትላንት እንዲሁም ዛሬ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ በሚሄዱ መኪናዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ሁለት ሰው ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል። ትላንት 1 ሰው ዛሬ 1 ሰው ተገድሏል።

አጠቃላይ ከላይ የተሰባሰቡት መረጃዎች የአይን እማኞችና ነዋሪዎች የሰጧቸው ሲሆኑ በመንግስት በኩል የተብራራ ዝርዝር መረጃ እስካሁን አልተሰጠም።

አሁንም አካባቢው ከፍተኛ የስጋት ቀጠና መሆኑን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው።

ምንጭ፦ቢቢሲ፣ቪኦኤ፣አዲስማለዳ፣ዶቼ ቨለ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው፥ንብረትም እየወደመ ነው። • አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ታኅሳስ 26 በጭላንቆ ቀበሌ 7 ንፁሃን ዜጎች እና 4 የመከላከያ አባላት ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን በቅዳሜው እትሙ አስነብቧል። • በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ቦታ…
#Metekel

1ኛ. ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ "ዳለቺ" ጥር 4/ 2013 ዓ/ም ከ80 ሰዎች በላይ መገደላቸውን አረጋግጧል።

ኮሚሽኑ ለቢቢሲ በሰጠው መረጃ ህይወታቸው የተቀጠፈው እድሜያቸው ከ2-45 ነው ብልሏል።

2ኛ. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ብሏል።

በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ጥር 4 ቀን ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ በተፈፀመው ጥቃት 82 ሰዎች መገደላቸውን አንድ አይን እማኝ አሳውቋል።

እንደ ኢሰመጉ በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ከ100 ሊበልጥ እንደሚችልና በአብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው ብሏል።

ከ24 ሰዎች በላይ ቆስለው ጋሊሳ ጤና ጣቢያ ቡለን ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው።

በተጨማሪ ፦ ከጥር 2-3 በቡለን ጉባ ወረዳዎች፣ ኦሜላ እና አይነሽመስ በተባሉ ቦታዎች በታጣቂ ኃይሎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 ሰዎች ተገድለዋል፤ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። (ሙሉ መግለጫቅ ከላይ ተያይዟል)

3ኛ. የቲክቫህ መተከል ዞን አባላት ከትላንት በስቲያ በድባጤ ወረዳው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከ100 እንደሚበልጡ ጥቃቱ በተፈፀመበት ዕለት ተናገረዋል።

ምንም የማያውቁ ንፁሃን ህፃናት እና እናቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ከጥቃቱ በኃላ የነበረውን ሁኔታ በፎቶ እንዲሁም በቪድዮ ቀርፀው ለማስረጃነትም አቅርበዋል።

⚠️ ይህ የመተከል ዞን አሁንም ከስጋት ቀጠናነት ያልተላቀቀ መሆኑን ነዋሪዎች እያሳወቁ ይገኛል ፤ የሚጨመር ኃይል ተጨምሮ አካባቢው ከስጋት እናቶች እና ህፃናትን ከሞት መታደግ እንደሚገባ እያስገነዘቡ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀው ግብረ ሃይል አባል ብ/ጄነራል ኣለማየሁ ወልዴ ከ2 ቀን በፊት በመተከል 74 ንፁሃን መገደላቸውን አሳውቀወል።

ግድያውን "ኦነግ ሸኔ እና የህወሃት ተላላኪ ታጣቂ ቡድን አባላት" ነው የፈጸሙት ብለዋል።

የታጣቂውን የሽፍታ ቡድን እንቅስቃሴ በመከታተል የተቀናጀ የህግ ማስከበር እርምጃ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

በዚህም በርካታ የታጣቂ ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውን ጠቅሰዋል።

በታጣቂ ሃይሉ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ባልተገባ መንገድ የሚገልጹ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Metekel

በመተከል ዞን የሽፍታ እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ የሚበሉ' የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው ሲል በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አሳሰበ።

ማሰበቢያው የተሰጠው በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ለሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት ስልጠና እየሰጠ ባለበት ወቅት ነው።

ግብረ-ሃይሉ በዞኑ ከሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት በዞኑ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ላይ አንዳንድ የጸጥታ ሃይል አባላት እጃቸው እንዳለበት መገንዘቡን አስታውቋል።

በዞኑ የሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት እንዲገመገሙና ሥልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑንም አሳውቋል።

ከጋንታ መሪ እስከ ብርጌድ አዛዥ የነበሩ 109 ፀረ-ሽምቅ፣ ልዩ ጥበቃና አድማ ብተና ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ 37 የፖሊስ አመራሮች ስልጠናውን መውሰድ ጀምረዋል።

የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የግብረ-ሃይሉ አባል ብ/ጄነራል ዓለማየሁ ወልዴ፤ የጸጥታ ኃይሉ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በእኩልነትና በተዓማኒነት የማገልግል ሃላፊነት አለበት ብለዋል።

ከዚህ በተቃራኒ የሚደረጉ ማናቸውንም አይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ በፍጥነት መቆም እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።

"የህዝብ አገልጋይ መስለው የሽፍታውን እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ ለመብላት' ሲነቀሳቀሱ የነበሩ የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው" ብለዋል።

"ማንኛውም የጸጥታ ኃይል ከህዝብ እና አገር በታች መሆኑን አስገንዝበው ፤ የተዘበራረቀ አስተሳሰብ የሚያራምዱ የጸጥታ መዋቅር አባላት ቆም ብለው መስመራቸውን ሊያጠሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Metekel : በሀገር መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ ስልጠና የተሰጣቸው 265 ሚሊሻዎች ዛሬ ተመረቁ።

ዛሬ የተመረቁት ሚሊሻዎች የመተከልን ሰላም ለመመለስ ሲስለጥኑ የቆዩ እንደሆኑ ተገልጿል።

በአካባቢው የሚገኛው ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮ/ል መልካሙ በየነ ፥ መከላከያ ሰራዊት እና በፌዴራል ፖሊስ አማካኝነት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከል እና ፀረ ሰላም ሃይሎችን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ አስፈላጊው ወታደራዊ ስልጠና ተሰጥቷል ማለታቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይፋ ባደረገው መረጃ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ በአሶሳ በጀመረው 23ኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።፡

በዚሁ መድረክ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ እንደተናገሩት ፤ በመተከል ግጭት ትምህርት ቤቶቹ የተጎዱት በ2013 ዓ.ም ሲሆን እነዚህም የመጀመሪያ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ናቸው ብለዋል።

በፀጥታ ችግር ከተጎዱ 194 ትምህርት ቤቶች ፥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፈራረሳቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቶቹ 69 ሺህ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደነበሩ ገልፀዋል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ፥ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #BenishangulGumuz , #Kamashi📍 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ፤ ትጥቃቸውን በሚፈቱበት አካሄድ ላይ ከተወካዮቻቸው ጋር ውይይት ሊደረግ መሆኑ ታውቋል። የክልሉ መንግስት የተሃድሶ ስልጠና ሃሳቡን ያቀረበው፤ ከጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ታጣቂዎች ጋር ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2014 በይፋ ዕርቅ መፈጸሙን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። በጉሙዝ…
#Metekel

በካማሺ ዞን የተካሄደውን ባህላዊ እርቅ በመተከል ዞን ለመድገም ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው።

የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን ፤ በካማሺ ዞን የተካሄደውን ባህላዊ እርቅ በመተከል ዞን ለመድገም በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ አሻድሊ ፤ የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸም ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት በካማሺ ዞን የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህል መሰረት ያደረገ እርቅ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በዞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የተሠራው ሥራ በታጣቂ ቡድኑ እና በመንግስት መካከል ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ድርድር ከማድረግ ባሻገር የአካባቢውን ባህል መሠረት ያደረገ እርቅ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

በተካሄደው እርቅ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት አቶ አሻድሊ በጫካ ይኖሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደአካባቢያቸው በመግባት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህንንም ስኬት በመተከል ዞን እንዲደገም ለማድረግ የሁሉም ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአካባቢው ማኅበረሰብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይወናበድ ሠላም በማስፈኑ ሂደት ከክልሉ መንግስት ጎን እንዲሠለፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጀ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በካማሺ ዞን የተካሄደውን ባህላዊ እርቅ በመተከል ዞን ለመድገም ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ የተሰማው በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው። የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን ፤ በካማሺ ዞን የተካሄደውን ባህላዊ እርቅ በመተከል ዞን ለመድገም በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።…
#Metekel📍

ከዚህ ቀደም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ውስጥ እንደተደረገው ባህላዊ የእርቅ ስነስርዓት በመተከል ዞንም ተካሄደ።

ከጥቂት ቀናት በፊት ክልሉ በካማሺ የተካሄደውን እርቅ በመተከል ለመደገም ስራዎች እየተሰሩ ነበር ማለቱ አይዘነጋም።

ዛሬ በግልገል በለሰ ከተማ ፤ በመተከል ዞን የነበረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ለመፍታት እርቀ ሰላም ተካሂዷል ሲል ዞኑ አሳውቋል።

ዞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ፥ " የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ በርካታ የጉህዴን አባላት በግልገል በለስ ከተማ እርቀ ሰላም አካሂደዋል " ብሏል።

ተሃድሶ ሲወስዱ ነበሩ የተባሉት በርካታ ወጣቶች እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን ወደ ሰላም ለመመለስ ''ከልብ የመነጨ እርቅ ለዘላቂ ሰላም'' በሚል መርህ በድርጊታቸው በመጸጸት እርቀ ሰላሙ እውን እንዲሆን ይቅርታና ምህረትን አካሂደዋል ተብሏል።

በመተከል ዞን ትጥቅ በመፍታት የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ እርቀ ሰላም የፈጸሙ የጉህዴን አባላት ማንዱራ ፣ድባጢ፣ ቡለን፣ ወምበራና ዳንጉር ወረዳዎች ውስጥ የናበሩ እንደሆኑ ዞኑ ገልጿል።

የዛሬው የይቅርታና ምህረት ፕሮግራም የተካሄደው በጉሙዝ ብሄረሰብ ዘንድ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚታወቀው ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓት ክዋኔ መሰረት መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት በዚሁ መተከል ዞን የክልሉ መንግስት ከታጣቂዎች ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረምን ጨምሮ የተለያዩ የሰላም ጥረቶች ሲደረጉ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ትምህርት የማስጀመር ንቅናቄ በግልገል በለስ ከተማ ተካሄደ።

በንቅናቄው መድረኩ ከትምህርት ሁኔታው ጋር በተያያዘ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

በመተከል ዞን በ2014 የትምህርት ዘመን በነበረው ግጭት በርካታ ትምህርት ቤቶች የወደሙን ሲሆን በዚህም ቀላል የማይባሉ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል።

አሁን ላይ በዞኑ በእጅጉ የተሸሻለ ሰላም በመስፈኑ በ2015 የትምህርት ዘመን ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መላክና የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መልሶ ግንባታ ማካሄድ እንደሚገባ ተገልጿል።

የመተከል ዞን በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለትምህርት ስራ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቼ ሰራለሁ ብሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ነባር አዲስና ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማገባት በሚስራው ስራ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ማስገንዝቡን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ መተከል ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ ባጋጠመ ግጭት በርካታ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከተሉ ሆነዋል ፤ በዚህም ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ደርሶባቸዋል አሁን ላይ የተፈጠረው የተሻለ ሰላም ተማሪዎቹን ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ ትልቅ ተስፋን ያሳደረ ነው።

@tikvahethiopia