TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው..."

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ቦርደዴ ወረዳ ጉምቢ በተባለ ቦታ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን #የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ኮምዩንኬሽን ቢሮ ጥቃቱ መፈጸሙን በፌስቡክ ገጹ ባወጣው አጭር መረጃ አረጋግጧል።

#የአፋር እና #የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑበት አካባቢ በምትገኘው ጉምቢ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱ ሰዎች መካከል አንዲት እንስት እንደሚገኙበት እና ሌሎች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ የሆኑስት ሲስተር ሐይማኖት ተስፋዬ አስረድተዋል። ሲስተር ሐይማኖት «ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው። ሰባት ሰው ሞቷል። አሁን ሰባት እሬሳ አለ። እየተፈለጉም ያሉ አሉ» ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል የኮምዩንኬሽን ቢሮ ከአንድ ሰዓት ገደማ በፊት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ በቦርደዴ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

ሲስተር ሐይማኖት ከሞቱት ሰባት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ሁለት ሴቶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። «ሁለት የቆሰሉ ሴቶች ነበሩ። ወደ አሰቦት ሆስፒታል ልከናቸዋል» ብለዋል።

ሲስተር ሐይማኖት እንዳሉት ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የገቡበት ያልታወቀ ሰዎች በመኖራቸው #ፍለጋ እየተካሔደ ይገኛል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር እና ድሬዳዋ የሚወስደው መንገድ ለረዥም ሰዓታት ተዘግቷል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia