#update CNN⬆️
ዓለም አቀፉ ብዙኃን መገናኛ ሲኤን ኤን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዐብይ አህመድን
በተመለከተ ሰፊ ትንታኔ አስነብቧል፡፡
#ወጣቱ፣ #ዲሞክራቱ እና #ሰላምን ሰባኪዉ መሪ ኢትዮጵያዉያን ለዘመናት ሲመኙት የነበረ አይነት መሪ መሆኑ በዘገባዉ ተገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን በመምጣታቸዉ ኢትዮጵያን ከእርስ በርስ ግጭት እና መበታተን ታድገዋል፡፡
በአስተዳደር ቆይታቸዉም እስረኞች ተለቀዋል፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላም ፈጥረዋል፣ የሚዲያ ነፃነትን አዉጀዋል፣ አስቸኳይ አዋጁን አንስተዋል፣ ኢኮኖያዊ ለዉጦችን የተመለከቱ ዉሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡ ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያዉያንን ተስፋ አለምልመዋል ብሏል ዘገባዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተወዳጅነታቸዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሶ በሃገሪቱ መዲና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምስሎች እና እሳቸዉን የሚደግፉ መልዕክቶች መኪኖች ላይ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ማየት የተለመደ ነዉ ብሏል፡፡ ምስላቸዉን የያዙ ቲሸርቶችም ይሸጣሉ ሲል ገልጿል፡፡
ዶ.ር ዐብይ ከሳቸው በፊት ከነበሩት መሪዎች ልዩ ናቸው ያለዉ #ዘገባዉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በፍቅር ይቀበላሉ፣ ከአድናቂዎቻቸው ጋር #ፎቶግራፍ ይነሳሉ፣ ፈገግታቸውም ለካሜራ ሳይሆን #ከልብ ነው ሲል አስፍሯል፡፡
ቶም ጋርድነር የተሰኘ እንግሊዛዊ ጋዜጠኛን ዋቢ አድርጎ ዘገባዉ እንዳሰፈረዉ ዶር. ዐብይ ከፈጣሪ የተላኩ መሪ ተደርገዉ እንደሚቆጠሩ ገልጿል፡፡
የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ነብይ እንደሆኑ ያምናሉም ብሏል፡፡ ዶር. ዐብይ የመበታተን ስጋት ተጋርጦባት የነበረችዉን ሀገር መታደግ ችለዋል ፡፡
መሪዉ #በወታደራዊ አስተዳደር በቂ ልምድ ማካበታቸዉን እና ይህም እንደጠቀማቸዉ አስነብቧል።
ሲኤን ኤን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የመንጋ ፍትህ እንዲሁም ሁከቶች ጥንቃቄ ያሻችዋል ብሏል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ዶር. ዐብይን የመሰሉ ሰዎች ከሚሊየን አንድ ናቸዉ ያለዉ ዘገባዉ አፍሪካ ካፈራቻቸዉ ጥቂት ታላቅ መሪዎች አንዱ ሊሆኑ ይችላሉ ሲል ትንታኔዉን ደምድሟል፡፡
ምንጭ፦ ሲኤን ኤን (በአመብድ ወደ አማርኛ ተቀየረ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia