TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የድሬዳዋ ቤተሰቦቻችን እንኳን በደህና መጣችሁልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለህ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

©ጥቤ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.

4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ🔝

#የድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ በሕክምና ሙያና በኪነ ሕንጻ ትምህርቶች በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን 53 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኪነ ሕንጻ በመደበኛ የትምህርት መርሃግብር ለ5 ዓመታት አስተምሮ ካስመረቃቸው 36 የኪነ ሕንጻ ተማሪዎች መካከል 12ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ከኪነ ሕንጻ ተመራቂዎች በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው ለ3ተኛ ጊዜ በሕክምና ዘርፍ ያስተማራቸውን 17 ተማሪዎችንም በሕክምና ዶክተር አስመርቋል፡፡

Via ENA
ፎቶ፦ ena & flagot(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️

የቀድሞ #የድሬዳዋ_ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ግርማ_ጎሮ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። የዶ/ር ግርማን ህልፈት ተከትሎ የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት የመታሰቢያ ፕሮግራም በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀጋብ ኤሬ የሚመለከተው አካል #መላ እንዲለን ድምፃችንን አሰማልን። #የድሬዳዋ_ዩኒቨርስቲ ነገር መላ ቅጡ ጠፍቷል። ትናንት ተማሪዎቹ ገብተው ሰላም ሰፈነ ስንል ይሄው ዛሬ ማታ አገርሽቶበታል። ኡፍፍፍ በጣም ነዉ የሚጨንቀዉ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት አሊ መሐመድ ቢራ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበረከተ! #ድሬዳዋ_ዩኒስቨርሲቲ #DireDawaUniversity

🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት #የድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ አረጋዊያንን በመደገፍና በመጦር ተግባር ለተሰማሩት ለወ/ሮ አሰገደች አስፋው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክቷል።

🗞ቀን ሰኔ 30/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert አቶ አህመድ ቡህ #የድሬዳዋ_ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አህመድ ቡህን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾመ።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ የስራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል። ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው ካለፈው መጋቢት ወር 2011 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በከንቲባነት ያገለገሉትን የአቶ መሐዲ ጊሬን መልቀቂያ ተቀብሏል። በምትካቸውም አቶ አህመድ ቡህን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሹሟል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባዔው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ አብደላ አህመድን መልቀቂያ መቀበሉም ተገልጿል። በምትካቸውም ወይዘሮ ፈጡም ሙስጣፋን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia