TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ ተሳደብ፣ ቀስቅስ፣ ሰዎችን አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው ተባላ ...ነገ ሀገር #ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ የምትበላው ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት #ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።
.
.
ዛሬማ ሰላም ነው #ፎክር እንጂ...የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ ህፃናት #ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ...የዛሬዋን ቀን #ትረግማታለህ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።

.
.
ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር...አቅራራ...ህዝብ ቀስቅስ...ተነሳ በለው፣ ግደለው በል!
.
.
የለኮስከው #እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን #ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ!

#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ ተሳደብ፣ ቀስቅስ፣ ሰዎችን አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው ተባላ ...ነገ ሀገር #ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ የምትበላው ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት #ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።
.
.
ዛሬማ ሰላም ነው #ፎክር እንጂ...የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ ህፃናት #ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ...የዛሬዋን ቀን #ትረግማታለህ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።

.
.
ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር...አቅራራ...ህዝብ ቀስቅስ...ተነሳ በለው፣ ግደለው በል!
.
.
የለኮስከው #እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን #ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ!

#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋጋ

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ያለአገልግሎት የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን መሸጫ የዋጋ ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር)  64.00

2. ካስት አይረን  - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.75

3. አልሙኒየም - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 120.00

4. ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ / ማሽነሪ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.25

5. ያገለገለ የተሽከርካሪ / ማሽነሪ መለዋወጫ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ  (በብር) 51.25

በዚህ መሰረት መሰሪያ ቤቶች ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን የማዕድን ሚኒስቴር ለሚመድብላቸው የብረታ ብረት አቅላጭ ኢንዱስትሪ/ለአምራች ኢንዱስትሪ #ብቻ በቀጥታ እንዲሸጡ ከሽያጭም የሚገኘውን ገንዘብ ወደ መንግስት ማዕከላዊ ግ/ቤት የባንክ አካውንት ገቢ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

(ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዙትን ደብዳቤዎች ይመልከቱ)

Credit : M. (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ የተናገሩት ፦ - ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ የሚያስጀምሩት በዋና መ/ቤት የሚገኙ ሰራተኞች በጊዜያዊነት በከተማዋ በማሰማራት ነው። በአሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት የሚሰሩ ሰራተኞችን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው። ለጊዜው ከዚህ ሰዎች እየሄዱ ይሰራሉ፤ ይመለሳሉ። እዚያም ጥቂት ሰዎች አግኝተናል።…
#Mekelle

መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ።

ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች።

ትላንት የበረራ ቴኬት ለማግኘት ብሞክርም አልተሳካልኝም፤ በቀጣይ ቀናትም ያሉት ከወዲሁ ተይዘዋል" ያለችው ሄርሞን አየር መንገዱ በየዕለቱ የሚያደርገድን በረራ እንዲያሳድ ጠይቃለች።

" የምወዳትን እናቴን ድምፅ ከሰማሁ ወራት ተቆጥረዋል፣ አባቴም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም፤ ቤተሰቦቼም ምን ገጥሟቸው እንደሆነ የማውቀው ነገር የለኝም፤ ወደ መቐለ ሄጄ ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ቸኩያለሁ፤ በረራው ቁጥሩ ጨምሮ ብሄድ ደስ ይለኛል ይሄ የኔ ብቻ ሳይሆን እጅግ የብዙ የትግራይ ተወላጆች ጥያቄ ነው " ስትል ገልፃለች።

ሌላው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ካህሳይ፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በረራ እንደሚጀምር መስማቱ በዛው ያሉትን ቤተሰቦቹን ለማያት ትልቅ ተስፋ እንዳሳደረበት ገልጿል።

ካህሳይ በመቐለ ያሉ ቤተሰቦቹን ሳያይና ድምፃቸውን ሳይሰማ ከዓመት በላይ እንደሆነው ገልጾ ወደመቐለ ለመጓዝ ትኬት ለመቁረጥ ቢሞክርም መሙላቱን አመልክቷል አየር መንገዱም ፤ የበረራ ቁጥር እንዲያሳድግ  ጠይቋል።

በተጨማሪ " በዚህ ወቅት በአውሮፕላን የሚኬደው አማራጭ መንገድ ባለመኖሩም ጭምር በመሆኑ የትኬት ዋጋ አስተያየት ይደረግበት " ብሏል።

በተመሳሳይ ሌሎችም በርካቶች የበረራ ቁጥር እንዲጨምርና የትኬት #ዋጋ ላይ አስተያየት እንዲደረግ እየጠየቁ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።

ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበት እንዲሁም ምእመናን በተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያንን የማይመጥንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ፦
° " #ግድሉ "
° " #ዘርህ_ይጥፋ "
° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " በማለት መናገራቸውን ገልጿል።

ይህ ንግግራቸው ፦
➡️ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል፣
➡️ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ፣
➡️ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል፣
➡️ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣
➡️ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ፣
➡️ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች በተለያየ ቦታ የሚያስተለልፏቸው መልዕክቶች ቤተክርስቲያንን ለትችት እየዳረገ እንዲሁም ዋጋ እያስከፈለ ነው ተብሏል።

በቀጣይ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ ገዢ ህገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል።

ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስብከት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia