TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዓመታትን የፈጀው መንገድ . . .

" የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ " - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

ግንባታው ከተጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረው የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት አሁን ወደ መጠናቀቁ መድረሱ ተነግሯል።

ይህ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በደቡብ የአዲስ አበባ ክፍል እየገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው መንገድ ፤ ከደቡብና ከምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለመግባትና ለመውጣት፣ ለረጅም ዓመታት ብቸኛው የወጪና ገቢ መተላለፊያ መስመር ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

መንገዱን ያለውን የትራፊክ  እንቅስቃሴ በአግባቡ ማስተናገድ እንዲችል በሚል ግንባታ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን እንደሚለው ፤ ከመንገድ ፕሮጄክቱ አጠቃላይ ግንባታ ሂደት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተፈፅሞ በከፊል አገልግሎት መስጠት ችሏል።

ነገር ግን፦
- #ከፋይናንስ
- #ከወሰን_ማስከበር ጋር በተያያዘ በገጠሙ ችግሮች ምክንያት ቀሪው የግንባታ ሥራ በተፈለገው ልክ ሳይፈፀም መቆየቱን አመልክቷል።

ለችግሮቹ በተሰጠ መፍትሄ የፕሮጀክቱ ግንባታ ቀጥሎ አሁን ላይ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መሸጋገሩን አሳውቋል።

መ/ቤቱ በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ክረምት በጭቃ፣ በጋውን በአቧራ ሲፈተን እንደነበር ገልጿል።

በዚህ መንገድ ምክንያት የትራፊክ እንቅስቃሴው እንደ ኤሊ ጉዞ እያዘገመ ይጓዝ እንደነበረም ገልጾ አሁን ግን ወደመጠናቀቁ መድረሱን አሳውቋል።

አሁን ላይ ቀደም ሲል ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ በቆየው የመንገዱ የቀኝ ክፍል ተደራቢ አስፋልት የማንጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የእግረኛ እና የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መስመርና ቀሪ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ብሏል።

ቃሊቲ ማሰልጠኛ የቀለበት መንገድ መሸጋገሪያ ላይ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ ማገጣጠሚያ ግንባታ ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃሉ ብሏል።

አሸከርካሪዎች በግንባታው ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ችግሮች እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia