TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰላም ድርድሩ መቼ ይጀመር ይሆን ?

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ድርድር እንዲቋጭ ከፍተኛ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል።

በፌዴራል መንግሥት እንዲሁም በህወሓት በኩል ለሰላም ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸው በርካቶች ሰላም ይሰፍናል የሚል ትልቅ ተስፋን አሳድሮባቸዋል።

በሁለቱም በኩል ተደራዳሪዎች መሰየማቸው ከተሰማ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን መቼ ድርድሩ ይጀምራል የሚለው ትክክለኛ መልስ አላገኘም።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሞሊ ፊ ግን የሰላም ንግግሩ በነሐሴ ወር ሊጀመር ይችላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ፊ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሽምግልና ለመፍታት ቁልፍ ሚና አላት ባሏት #ኬንያ ውስጥ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ድርድሩ እንደሚጀመር ጥንቃቄ የተሞላበትን ተስፋቸውን ለአገራቸው ም/ቤት ኮሚቴ መናገራቸውን AFP ፅፏል።

በኬንያ ሊካሄድ የተቃረበው ምርጫ በድርድሩ የጊዜ ሰሌዳ ላይ መዛባትን ሳይፈጥር እንዳልቀረ ገልጸዋል።

ኬንያ ነሐሴ 3/2014 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

በሌላ በኩል በተለያዩ አገራት ጉብኝታቸውን የጀመሩት አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር "ድርድሩ ወደፊት እንዲራመድ አሜሪካ ምን ማድረግ እንደምትችል ከሁለቱም ወገኖች ጋር ይወያያሉ" ሲሉ ሞሊ ፊ ለኮሚቴው ተናግረዋል።

በተጨማሪ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ #ከአጎዋ መታገድን እያጤነው መሆኑን ተናግረዋል።

የጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ አንጻር ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለማድረግ የተሻለ ሁኔታ መኖር አለመኖሩን " በቅርበት እያጤነ ነው " ሲሉ ፊ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ፦ telegra.ph/AFP-07-29

@tikvahethiopia