TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ሰላማዊ ሰልፍ መፍቀድና መከልከል የሚባል ነገር የለም ፤ ማሳወቅ ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው ። የሚካሄድበት ቦታ መምረጥ የመንግስት ስራ ነው " ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ መጪው አዲስ ዓመት 2016 ዓ.ም በማስመልከት ለሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት " ሰልፍ እንዳይካሄድ ተብሎ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ ነገ ሰልፍ ለማካሄድ…
" እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መንግሥትን እና ፓርቲን ለመለየት ወስኖ እየሰራ ነው ብለዋል።

ይህን አዲስ ያሉትን የአሰራር ሂደት በ " ፀረ-ህወሓት " እንቅስቃሴ የፈረጁ የፓርቲው አመራሮች እንዳሉ ተናግረዋል።

አንዳንድ የክልሉ ወረዳዎች የጊዜያዊ አስተዳደር አካል እንዳልሆኑ በመግለፅም አዲስ ማዕተም ለመጠቀም ፍቃደኛ እንዳልሆኑ አስረድተዋል። ይህ መዋቅር እንዳይዘረጋ የማደናቀፍ ተግባር ነው ብለውታል።

አቶ ጌታቸው " በተደራጀ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ አለ፤ በዞን እና በወረዳዎች ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እንዳይኖረው የሚሰሩ አሉ ፤ በዚህም ዋናው የሚጎዳው ህዝቡ ነው። ጠቃሚው ነገር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ጨርሰን ከፌዴራል መንግሥት ጋርም ከነልዩነታችን መተማመናችንን ወደላቀ ደረጃ በማሳደግ በህዝብ የተመረጠ መንግሥት የሆነው ይሁን ፓርቲ ስልጣን የሚይዝበት ሁኔታ መፍጠር ነው። በዚህ ሂደት ግለሰቦች በተደራጀ መልኩ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ ፤ እንደ ፓርቲ ጉዳዩ እንቅፋት መሆኑን አንስተን ወደ ግምገማ እንገባለን " ብለዋል።

በጀት መድበው የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ለማደናቀፍ የሚሰሩ አካላት አሉ ያለቱ አቶ ጌታቸው እነዚህን አደናቃፊ ሲሉ የገለጿቸውን አካላት ማን እንደሆኑ በስም ጠቅሰው በግልፅ አልተናገሩም።

አቶ ጌታቸው ፤ የትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይገባ ሁሉም አይነት ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ እንሰራለን ያሉ ሲሆን " በአማራ ክልል ሆነው የትግራይን ህዝብ ማጥፋት የሚፈልጉ አካላትን ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር አደጋ መፍጠር ወደማይችሉበት ደረጃ ለማውረድ ያለ ጥርጥር እንሰራለን " ብለዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው በፕሪቶሪያ ስምምነት እና በሀገሪቱ ህገመንግስት መሰረት የትግራይ ክልል አስተዳደር ወደ ቀድሞው የመመለስ እና ተፈናቃዮችን ወደቄያቸው የመመለስ ሂደትን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመርህ ደረጃ #ተስማምተናል ብለዋል።

ይህ ሂደት በመጓተቱ በነዋሪው ህዝብ እና ተፈናቃዮች ላይ ችግሩ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው በመግለጫቸው ፥ በክልሉ መንግሥት የማያውቃቸው #እስር_ቤቶች መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።

" መንግሥት የማያውቃቸው እስር ቤቶች አሉ። ይሄን ጉዳይ የፈፀሙና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙትን ማሰር ጀምረናል። በዘመቻ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንይዛቸዋለን። ሰዎችን በመጥለፍ ገንዘብ የሚቀበሉ አሉ ፤ ኤርትራውያንን በመያዝ ብር እየተቀበሉ ናቸው። እነሱን ብቻ ሳይሆን የክልሉ ተወላጆች #ሀብታም ቤተሰብ ያላቸውን እየያዙ ናቸው ፤ እነዚህ በመንግሥት መዋቅር ስም የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፤ ሰላዮች ነን የሚሉ፣ በተለያዩ አደረጃጀቶች ስም የሚሰሩ ናቸው። ለማጣራት ረጅም ጊዜ ወስዶብናል ከዛሬ ጀምሮ ግን በሚቀጥሉት ቀናት ፍርድ የሚያገኙበት ስራ እንሰራለን የራሳቸው እስር ቤት አቋቁመው ሰዎችን እየደበደቡ ገንዘብ እየተቀበሉ የሚሰሩ በስም የምናውቃቸው ሰዎች አሉ። " ብለዋል።

በትግራይ ያለው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ መሆኑን ያሳወቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ወጥቶ መግባት ቅንጦት ሆኗል ብለዋል።

" እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም ፤ ይሄን ለማስተካከል ከስራ ውጭ የነበሩ የፀጥታ አካላትን ወደ ስራ የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈው ህዝቡን በማስተባበር ፀጥታ ለማስፈን ጥረት እንደሚደረግ ገልጸው ከምንም በላይ የሁሉም ችግር ምንጭ ፖለቲካዊ ነው ብለዋል።

ከእርዳት ምዝበራ ጋር በተያያዘ እስካሁን 482 እርዳታ መዝብረዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የገለፁት አቶ ጌታቸው እስካሁን እርዳታ ባለመጀመሩ ተፈናቃዮች በተለየ መንገድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር በተያያዘም ሰልፍ እየወጡ ያሉት መንግሥት በአግባቡ ስራውን ባለመስራቱና የክልሉ የበጀት አቅም አነስተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥረትው ስለነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንዳለና ፈንጂዎችም በብዛት መገኘታቸውን ገልጸዋል።

ሰልፍ ማድረግ መብት ቢሆንም ለህዝብ ደህንነት ሲባል የሚካሄደው ሰልፍ ጊዜው እና ቦታው እንዲቀየር ከሰልፍ መሪዎች ጋር እንነጋገራለን ብለዋል።

" መንግሥት የፀጥታ ኃይል ማሰማራት እችላለሁ በሚልበት ሰዓት እና ቦታው ሰልፍ ማካሄድ የተለመደ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አሁን ገና ተነጋረን አልጨረስንም ፤ ስለ አካሄዱ የምንነጋገርበት ነገር አለ፤ የፀጥታ ችግር አለ ፤ ከፍተኛ የሆነ የፈንጂዎች መሰባሰብ እንዳለ ደርሰንበታል ከጎረቤት አካባቢ የመጡ ናቸው የፀጥታ አካላት የሚያጣሩት ነው ፤ ሰልፍ የጠሩት አካላት ረብሻ ይፈጥራሉ ሳይሆን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው ረብሻ በመፍጠር ትግራይን ዳግም ወደ ሁከት ለማስገባት ያቀዱ ኃይሎች አሉ " ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

መረጃው የተዘጋጀው በቪኦኤ ሬድዮ ጋዜጠኛ ሙልጌታ አፅብሃ ነው።
ፅሁፍ ፦ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ።

@tikvahethiopia