TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አብዴፓ‼️

ኢንጂነር #አይሻ_መሃመድ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አብዴፓ/ ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አብዴፓ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አወል_አርባ ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አብዴፓ የፓርቲውን ስራ አስፈፃሚዎች ኮሚቴ አባላት ምርጫንም አካሂዷል። በዚህም መሰረት፦

1.ኢ/ር አይሻ መሃመድ
2.አቶ አወል አርባ
3.አቶ ኢብራሂም ዑመድ
4.አቶ አህመድ ሱልጣን
5.ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ
6.አቶ መሃመድ ሃሠን
7.አቶ መሃመድ ጠይብ
8.አቶ ጣሃ አህመድ
9.አቶ ዓሊ ሁሴን ዌኢሳ
10.አቶ ኤላማ አቡበከር
11.አሊ ሁሴን ዑመር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

ከህዳር 23 ጀምሮ በሰመራ ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ 7ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔም ባለፉት አመታት በክልሉ በነበረው አፈፃፀም እና በወደፊት የልማት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

አቶ #አወል_አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው #ተሾሙ። የክልሉ ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ምክር ቤቱ በቀጣይም የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ በመምረጥ በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የካቢኔ አባላትን ሹመት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በተዘጋጀ አዋጅ ላይም ውይይት ያደርጋል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኩሪፍቱ በሰመራ🔝

አፍሮ ፅዮን ኮንስትራክሽን ኩባንያ በአፋር ክልል ርዕሰ ከተማ #ሰመራ በኩሪፍቱ ሪዞርት ሥር የሚተዳደረውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ 90 በመቶ በማጠናቀቅ ሥራ አስጀምሯል፡፡

#ኩሪፍቱ_ሪዞርት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ሆቴል ቅዳሜ የካቲት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ #አወል_አርባ በተገኙበት የተመረቀ ሲሆን፣ የሆቴሉ ሥራ መጀመር ለክልሉ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል፡፡

148 የመኝታ ክፍሎች ያሉትና ሌሎች ደረጃቸውን የጠበቁ የሆቴል አገልግሎቶችን ያካተተው ሆቴል፣ እስካሁን 500 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት ሲገለጽ፣ ለቀሪ ሥራዎች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች #አዋሳኝ አካባቢዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ ርዕሰ መሰተዳደሮች ገለፁ፡፡

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ #አወል_አርባ ዛሬ በአዲስ አበባ በሁለቱ ክልሎች የፀጥታ ችግር መፍትሄ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች አንድም ሰው እንዳይሞት እና ግጭት እንዳይከሰት የማድረግ ሰራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታው አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን እንዲቋቋምና ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ እደሚገባው ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ጉዳይ ላይም በህዝብ ለህዝብ #ውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ክልሎቹ #ከማንነት እና #ከወሰን ጋር ያሉ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia