TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate ሳምንታዊ የመንግስት መግለጫ⬇️

በኢትዮጵያ #የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ።

የአገሪቷን ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው ሳምንታዊ የመንግስት አቋም መግለጫው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ለህዝቦቿ ተስፋ ሰጪ ከመሆኑ በላይ ከአገር አልፎ ለአጎራባች የአፍሪካ አገሮች ጭምር ተምሳሌት መሆኑን የታወቁ የዓለም ፖለቲካ ተንታኞችና ተቋማት እየመሰከሩለት መሆኑን ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይደግፉ ቡድኖች አንዳንድ አደናቃፊ ተግባራትን ሲፈፅሙ እንደሚስተዋል አመልክቷል።

እነዚህ አካላት ከሰሞኑ በቡራዩ እና በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ባስነሱት ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ “የዜጎች ጥሪትም ወድሟል” ሲል አመልክቷል።

“የንፁሃን ዜጎችን ደም ማፍሰስ፣ አካል ማጉደል እና ለዓመታት ለፍተውና ደክመው ያፈሩትን ሃብት በመዝረፍና በማውደም፤ ሁሉም የሚረባረብለትን የለውጥ ጉዞ ለማጠልሸት መስራት ለማንም ትርፍ አያስገኝም” በማለትም አስገንዝቧል።

በመሆኑም በደረሰው ጉዳት ህዝብ እና መንግስት አዝነዋል ያለው የመንግስት መግለጫ “ድርጊቱ የየትኛውንም ብሄር የማይወክል እና ክስተቱ ለውጡን የሚያፋጥን እንጂ ሊያደበዝዝ አይችልም” ብሏል።

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ማሸነፍና ሥልጣን መያዝ የሚቻለው የተሻለ ሃሳብ በማቅረብ ተወዳድሮ በማሸነፍ እንጂ #በአመጽና በኃይል ሊሆን እንደማይችልም በመግለጫው ተመልክቷል።

የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት ሁኔታ የአገሪቷን #ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ መንግስት ኃላፊነቱን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህግ የበላይነት #መከበር በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia