TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ናቸው ተብለው የፈረሱ ቤቶች ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ትናንት ምሽት ድረስ 3,800 ቤቶች ፈርሰዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ቤቶቹ #በሕገወጥ መንገድ የተሰሩ በመሆናቸው የወሰድኩት #እርምጃ ሕግን የማስከበር ሥራ ነው ብሏል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው ከ10 እስከ 19 ዓመት ቤት ገንብተው መኖራቸውን የአፈር ግብር ለመንግሥት እንደሚከፍሉና ውሃና መብራትን ጨምሮ መሰረተ ልማት የከተማ አስተዳደሩ እንዳሟላላቸው ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወቃል፡፡ ነዋሪዎች ቤታችን በመፍረሱ ጎዳና ላይ ወድቀናል የሚል #እሮሮ እያሰሙ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊውን ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ሸገር 102.1 ራድዮ በጉዳዩ ዙሪየ አነጋግሯቸዋል።

Via Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ነው ያለውና ቤተክርስቲያንን ያሳዘነው ፤ ምዕመኑንም ያስደናገጠው የ " ጳጳሳት " ሹሙት ምንድነበር ?

ትላንት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት ተፈፅሞ ጳጳሳትን የመሾም ተግባር መከናወኑን መግለጿ ይታወሳል።

ይኸው ሲመተ ጳጳሳት ፤ #ከቅዱስ_ሲኖዶስ እውቅና ውጭ #በሕገወጥ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ነው ቤተክርስቲያን ያሳወቀችው።

ድርጊቱ በርካታ ምእመናንንም ያስደነገጠ ነበር።

ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት በተፈፀመበት መልኩ ተከናውኗል ያለችውን ሹመት ማነው ያካሄደው ?

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-23-2
" በየቤቱ የቁም እንስሳት ማረድ / በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል አልተከለከለም " - የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ #ሐሰተኛ ነው ሲል አሳወቀ።

ከዚህም ጋር በተያያዘ #ምንም_ዓይነት_ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጧል።

ነገር ግን በየአካባቢው #በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia