TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሲዳማ ዞን ከተሞች እንዴት ዋሉ? የዛሬው ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? #ሀዋሳ #ይርጋለም #ወንዶገነት #ለኩ #ሀገረሰላም

ከ20 ደቂቃ በኃላ እመለሳለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለኩ

የቀድሞ እንቅስቃሴዋ ባይኖርም የፀጥታው ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል። አልፎ አልፎ ከሚታዩ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ውጭ ከተማዋ ጭር ብላ ውላለች። የፀጥታ አስከባሪዎች ከተማውን ሲቃኙ ነበር።

#ሀገረሰላም

ከትላንት በስቲያ እና ትላንት ከፍተኝ ውጥረት እና የሰላም መደፍረስ የነበር ሲሆን ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እና ሰላም ታይቷል። የተኩስ ድምፅም ሳይሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ነግረውናል።

🏷በአጠቃላል በሁሉም ከተሞች ካለፉት ቀናት የተሻለ መረጋጋት እየታየ መጥቷል። ውሃ ተመረዘ የተባለውም በሁሉም ከተሞች የሚገኙ ዜጎችን ለማሸበር ነበር። ወሬም ውሸት ሆኖ ነው የተገኘው።

📎በየከተሞቹ በተፈጠረው ግጭት ስለጠፋው የሰው ህይወት ቁጥር እና ስለደረሱት ጉዳቶች በዞኑ ከሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ከመንግስት ሰዎችን እንዲሁም ከተለያዩ የዜና አውታሮች የምናገኘውን መረጃ በቀጣይ እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲአን #ሲዳማ_ዞን #ሞረቾ #ወተረሬሳ #ሀገረሰላም

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ በሞሮቾ ሶስት እና በሀገረሰላም ደግሞ ሁለት ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስረድተዋል።

በሐዋሳ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በግጭቱ የተጠረጠሩ 150 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከንቲባው ጠቁመዋል። ግጭቱን ተከትሎ የክልል እና የፌደራል አካላት ባደረጉት የማረጋጋት ስራ በሐዋሳ ከተማ እና በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን አቶ ስኳሬ ገልፀዋል። በሐዋሳ በዛሬው ዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደታየና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸው ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግን አሁንም ዝግ ናቸው።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል። በከተማይቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ ነው። ካለፉት ቀናት በእጅጉ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላም በከተማዋ መስፈኑን በስልክ ያነጋገርናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

#ወንዶገነት

በወንዶ ገነት ከተማ አርብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሚታወስ ሲሆን ትናንት ቅዳሜም በወንዶ ገነት ውጥረት ነግሶ ነው የዋለው። ይሁን እንጂ ዛሬ እሑድ በከተማው መረጋጋት እንደሚታይ አንድ የአይን እማኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል “የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። ሱቆችም ከሞላ ጎደል ተከፍተዋል። የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች በስፋት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነው የዋሉት።
/BBC/

#ይጋለም

ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቀስቃሴ አልተመለሰችም፤ ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ #መረጋጋት አለ። ዛሬ ላይም ቢሆን በይርጋለም ከተማ የደህንነት ስጋት መኖሩን ለBBC የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪ፤ በዚሁ ምክንያት በርካታ የንግድ ተቋሟት በራቸውን ዝግ አድርገው እንደዋሉ ገልፀዋል።

#ሀገረሰላም

በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ዛሬ ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እንደታየ ገልፀዋል፤ ስጋቶች ግን አሁንም አሉ ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት በከተማው ይገኛል በየቦታውም ቅኝት ሲያሰርግ ውሏል ሲሉ የዛሬውን ሁኔታ አስረድተዋል።

#አለታወንዶ

የዛሬው ዉሎ ከትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ከነበረው እጅጉ የተሻለ እና መረጋጋት የታየበት እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሲዳማ ዞን የኢንተርኔት አገልግሎት አልተጀመረም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀገረሰላም

በሲዳማ ዞን ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የሁላ ሀገረሰላም ወረዳ ነዋሪዎች በአዲስአበባና ሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች 200 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡ የአካባቢው ተወላጆች በወረዳው አስተዳደር ቅጥር ግቢ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን በመጎብኘት 20 ኩንታል ዱቄትና አልባሳት አበርክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia