TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#LemmaMegersa #PP

"...አይሆንም ያልኩበት ምክንያት አንደኛ እኛ የኦሮሞ አመራር አባላት የኦሮሞ ህዝብ አምኖን ያቀረበልን ትላልቅ ጥያቄዎች አሉ፤ እነዚህ ጥያቄዎችን እንመልስላችኃለን ብለን ቃል ገብተናል። ህዝባችን ይህን ጥያቄ ያቀረበልን የትላንቱን #ኦህዴድ ስም ለውጠንለት #ኦዴፓ ካልን በኃላ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ጥያቄውን አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ብሎ የሰጠው ለሀገራዊ ፓርቲ ሳይሆን ለኦዴፓ ነው። ስለዚህ የህዝቡን ጥያቄ ሳንመልስ ይህን ማድረግ ትክክል አይደለም፤ እምነት ማጉደል ይሆናል እናም ጥያቄዎቹን ቆጥሮ እንደሰጠን መመለስ አለብን የሚል እምነት አለኝ።" አቶ ለማ መገርሳ

.
.
"...የመደመር ፍልስፍና የምንለው ለውጡ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ፤ እይታ ነው። በበፊቱ አግባብ መሄድ አንችልም። ጠንካራ ጎኖችን ከድሮ እናስቀጥላለን። ደካማ ጎኖችን ማረም አለብን። ይሄ ለውጡ በምን አይነት ፍኖተ ካርታ ይመራ የሚል የህዝብም የሊሂቃንም ጥያቄ ነበር። በምንድነው የምንመራው ? ፍኖተ ካርታ የለም የሚል አንድ አመት፣ አንድ አመት ተኩል ይሆናል ለውጡ ከተጀመረ በኃላ፤ የመደመር ዋነኛው አስፈላጊነት ለውጡ በምን ጎዳና ይመራል? ከዴሞክራሲ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከሰላም አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከኢኮኖሚ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከፖለቲካ አኳያ ቀጣይ እይታችን፣ ቀጣይ ሃሳባችን ፍኖተ ካርታው ባጠቃላይ ሚመራበት ምንድነው የሚለውን ሚመልስ ነው።" አቶ ፍቃዱ ተሰማ (የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ፅ/ቤት ኃላፊ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአቶ ለማ መገርሳ ቀጣይ የፖለቲካ ተሳትፎ ዕጣፈንታ...

#VOA #LemmaMegersa

ቪኦኤ : ኦቦ ለማ እንደሚያውቁት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ODP) ፈርሷል፤ የእርሶ የፖለቲካ ተሳትፎ ዕጣፈንታ ምን ይሆን?

ኦቦ ለማ : "ከዚህ ድርጅት ውጣልን ብለው እስካልወሰኑ ልዩነቴን ይዤ እሟገታለሁ። እኔ ብቻ ስላሆን ቅራኔ ያላቸው፣ የሚከራከሩ ብዙ አሉ። ከሆነልን እናስተካክላለን፤ ካልሆነ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተመካክረን የሚበጀንን እናደርጋለን።"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#LemmaMegersa

አሜሪካ - ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እያበረከተች ያለውን በጎ ሚና አደነቀች!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በዋሽንግተን ዲሲ የተወያዩ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም የሚታበረክተው በጎ ሚና እና በመከላከያ ዘርፍ የምታካሄደውን ማሻሻያ አድንቀዋል፡፡ የሁለቱ አገራት 9ኛው የሁለትዮሽ የመከላከያ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ በዋሽንግተን ከተማ ተካሂዷል።

በስብሰባው ሁለቱ አገራት በቀጣናው የጸጥታና ደህንነት፣ የመረጃ፣ ሰላም ማስከበር እና መከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ ገምቢ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም የአገራቱን በጸጥታና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ትብብር የበለጠ እንደሚያጎለብት ተገልጿል፡፡

አገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ እንዲጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹ ሲሆን፣ ባለፉት 18 ወራት በጸጥታው ዘርፍ እያደገ የመጣው ትብብርም ለዚህ ማሳያ እንደሆነ ነው የተገለጸው። የሁለትዮሽ የመከላከያ ኮሚቴ ስብሰባው ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን ጠንካራ ግንኙነት በማበልጸግ በጸረ ሽብር፣ በደህንነት መረጃ እና ሌሎች የትብብር ዘርፎችን በመለየት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ከአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#LemmaMegersa #GeneralAdemMohammed 

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ የተመራ ልዑክ ቢሾፍቱ የሚገኘውን የመከላከያ ኮንፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገበኘ። በጉብኝቱ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄነራል አደም መሃመድን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AbiyAhemed #LemmaMegersa

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ መካከል የነበረ አለመግባባት "በበሳል የድርጅታችን ስራ አስፈጻሚ አመራሮችና በቀድሞ የትግል ጓዶች" ተፈቷል ሲል የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል። ዶ/ር አብይ እና አቶ ለማ በጋራ ለመታገል ተስማምተዋል።

(እሸት በቀለ - ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AbiyAhemed #LemmaMegersa

አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት በአስተዳራዊ ስርዓት በተለይም እንደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታና አዳዲስ ሀሳቦችና የፓርቲ ሪፎርሞች በሚካሄዱበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች ሊኖሩ ቢችሉም የሀሳብ ልዩነት በራሱ ችግር እንዳልሆነ ገልጸው ትልቁ ጉዳይ ይህን የሀሳብ ልዩነት እንዴት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንፈታዋለን የሚለው ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

አቶ አዲሱ በቅርቡ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ ለመገናኛ ብዙሃን በመደመር ፍልስፍና እንዲሁም በፓርቲው ውህደት እንደማይስማሙ የገለጹትን ጠቅሰው ይህንን ጉዳይ በኦሮሞ ባህልና ስርዓት መሰረት የቀድሞ የኦዲፒ የስራ አመራሮች ሌሎችም ኃላፊዎች በተገኙበት የበሰለ ውይይት በማድረግና የነበሩ ልዩነቶችን በማጥበብ ከዚህ በኃላም አንድነትን አጠናክሮ አብሮ ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል፡፡

አቶ አዲሱ አክለውም ፓርቲያቸው በዲሞክራሲ ባህል እና በኦሮሞ ባህልና ስርዓት የውስጥ ችግሩን ለመፍታትና ህብረተሰቡ ያለውን ጥያቄ ሁሉ ለመፍታት የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia