#EthiopianAirlines🇪🇹
" ... የድርጅቱን ምርታማነት እና የኢንደስትሪ ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ለመስራት ቁርጠኛ ነኝ " - አቶ መስፍን ጣሰው
ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰራታዊ የሰራተኞች ማህበር አዲስ ለተሾሙት የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የእንኳን ደህና መጡ መርሃ ግብር አከናውኖ ነበር።
በመርሃ ግብሩ ላይ የማህበሩ ፕሬዚደንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳ ፤ አዲስ የተሾሙትን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንኳን ደህና መጡ በማለት የሰራተኛ ማህበሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በማህበሩ የተገኙ ድሎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፣ የድርጅቱ ምርታማነት እና የኢንደስትሪ ሰላሙን በማስጠበቅ ሂደቱም የመሪነት ሚናውን በመጫወት እንደሚቀጥሉ እነታቸውን ገልፀዋል።
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው የተደረገላቸውን አቀባበል አድንቀው እንደቀድሞው ሁሉ ከቀዳማዊ ማህበሩ ጋር የሰራተኞችን ጥቅም፣ የድርጅቱን ምርታማነትና የኢንደስትሪ ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ለመስራት ቁርጠኝነት አስታውቀው ማህበሩም በዚህ ረገድ ከፍ ያለ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
የማህበሩ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ኪያ ለማና የአየር መንገዱ የሰው ሃብት ም/ፕሬዝዳንት በመርሃ ግብሩ መልዕክታቸውን አስተላለፈው " በህብረት ፣ በንግግርና በድርድር ብዙ ውጤት እንዳመጣን ሁሉ ይህንኑ አጠንክረን ብንቀጠል የምናልማቸውን ስኬቶች ማሳካት እንችላለን " ብለዋል።
Via Abdi Kuma (Tikvah Family)
@tikvahethiopia

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ " ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20 % ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን እኤአ ሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ38 ዓመታት ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ትላንት አዲሱን…
#EthiopianAirlines
በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት አቶ መስፍን ጣሰው አዲስ የማኔጅመንት ቡድን አዋቅረዋል፡፡
በተዋቀረው በአዲሱ ማኔጅመንት ቡድን ቀደም ሲል በተጠባባቂነት የሃላፊነት ቦታዎች ይዘው ሲያገለግሉ የነበሩ ሀላፊዎች ቦታው ፀድቆላቸዋል።
አንዳንድ ሀላፊዎች ደግሞ ከቦታቸው ተነስተው በሌሎች ባልደረቦቻቸው መተካታቸውን " ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ " ዘግቧል።
(ዝርዝሩ ከላይ በምስሉ ተያይዟል)

#EthiopianAirlines #EthioTelecom
" የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ እና ሳትንገላቱ የበረራ ትኬታችሁን በቴሌ ብር መግዛት ትችላላችሁ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ / ኢትዮ ቴሌኮም
ከዚህ በኃላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የበረራ ትኬታቸውን በ 'ቴሌ ብር ' አማካኝነት መግዛት ይችላሉ ተብሏል።
ዛሬ ኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋር ሊሰሩ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን የአየር መንገዱ ደምበኞች የበረራ ትኬት ክፍያ በቴሌ ብር አማካኝነት መፈፀም እንደሚችሉ ተገልጿል።
የተደረገው ስምምነት የአየር መንገዱ ደንበኞች የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው እና ሳይንገላቱ ባሉበት ሆነው በሞባይል ስልካቸው አማካኝነት ትኬት መግዛት እና ክፍያ ለመፈፀም እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፥ ለሀገር ውስጥ ሆነ ለውጭ ሀገር በረራ እስከ 30 ሺህ ብር የሚያወጡ የአየር መንገዱን ትኬቶች የትም መሄድ ሳያስፈልግ ካሉበት ሆኖ መግዛት ይቻላል ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ።
ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው።
ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023 በጀትና እቅድ ውይይትና ማጽደቅ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።
የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ውሎ ከድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውና ከፍተኛ የማኔጅሜንት አባላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሰራተኞች በተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ለተለያዩ የሰራተኛ ተወካዮች ፣ የተመሰገኑ የስራ መሪዎችን የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጠ ሲሆን ፤ የአየርመንገዱ ሰራተኞች የማህበሩን ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳን በማህበሩ ላስመዘገቡት ለውጥ ከፍተኛ ሽልማት እንዲሁም የአየር መንገዱን ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክቷል።
በሌላ በኩል ጉባኤው ታግዷል ፣ አልተካሄደም በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ውሸትና አሉባልታ ናቸው ያለው ማህበሩ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው ሲል ገልጿል።

#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።
አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

በአፍሪካ ግዙፉና በደህንነቱ አስተማማኝ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማት ተበረከተለት።
አየር መንገዱ " Global Travel Magazine " ከመንገደኞች ባሰባሰበው ድምፅ መሰረት " የ2022 ዓ.ም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ " ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ " SKYTRAX 2022 " የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ በ4 ዘርፎች ተሸለመ።
አየር መንገዱ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተገልጿል። ደረጃው በዓለም ዙሪያ ባሉ የአየር መንገድ ደንበኞች በተሰጠ ድምጽ ነው።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸለማቸው ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?
🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ፤
🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለ4 ተከታታይ ዓመታት
🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ ደረጃ ፤ ለ4 ተከታታይ ዓመታት
🇪🇹 በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን ሽልማት አሸንፏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካፒታሉን ወደ 300 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ማቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
አየር መንገዱ አሁን ያለውን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሳደግ ያቀረበው ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ ሲሆን ቦርዱ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን ያለንን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማሳደግ የፈለግንበት ምክንያት፣ ወሮታችን ከፍ እያለ በመምጣቱ ሲሆን፣ በቅርቡ ያፀድቁልናል ብለን እናስባለን " ሲሉ ተናግረዋል።
የአየር መንገዱ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ እንደሚገኝ ጋዜጣው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ማረጋገጡን አመልክቷል።
አቶ መስፍን የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄውን ምክንያት በተመለከተ፤ " የምናንቀሳቅሰው ገንዘብ እያደገ በመምጣቱና የካፒታል ማሻሻያ ከሌለ ትክክለኛ የፋይናንስ አያያዝ ለመፍጠር ስለሚያስቸግር " ነው ብለዋል።
" በተጨማሪም አሁንም አዳዲስ አውሮፕላኖች እያስመጣን ነው፡፡ በምናስመጣበት ወቅት የዕዳና ካፒታል ምጣኔ መመጣጠን አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፕላን የሚገዛው በብድር ስለሆነ አበዳሪዎቹ ጋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍ ያለ የሀብት መጠን መድረስ አለበት። ብለዋል፡፡
የዕዳ እና ካፒታል ምጣኔ ተቋሙ ካለው ካፒታል አንፃር ሲታይ ምክንያታዊ ካልሆነ አበዳሪዎቹ ለማመን እንደሚቸገሩ አቶ መስፍን መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚሊዮን ዶላር ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ የጭነት አገልግሎት ማዕከል እያስገነባ ሲሆን ይኸው ማዕከል በቅርቡ ስራ ይጀምራል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ ፤ አየር መንገዱ በካርጎ አገልግሎት ከአፍሪካ ትልቁና በዓለም ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ ዘመናዊ አሰራርን ይከተላል ብለዋል።
በዓለም ላይ የዲጂታል ግብይት እያደገ በመምጣቱ የመደበኛው ካርጎ አገልግሎት እየቀነሰ በአንጻሩ የኢ-ኮሜርስ የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣቱን አንስተዋል።
አዲሱን የካርጎ አገልግሎት ማዕከል እውን ለማድረግ እውቀትና የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተዘርግቶለት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
አሰራሩ ከዚህ ቀደም ከነበረው የካርጎ አገልግሎት በእጅጉ የሚለይ ነው ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ዕቃ ከውጭ ተጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ይወስድ የነበረውን እስከ 7 ቀን በአዲሱ አሰራር እንደሚቀረፍ ተናግረዌ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባ ያለው የኢ-ኮሜርስ ማዕከል በ15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይሆንበታል።
ማዕከሉ በመጪው የፈረንጆቹ 2023 አጋማሽ ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኢዜአ አየር መንገዱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።