TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለ1439ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

ሕብረተሰቡ በበዓሉ ላይ በአዲስ አበባ ስቴድየም እና በዙሪያው #ፍተሻ መኖሩን ተገንዝቦ ለፍተሻ እንዲተባበር፣ የእምነቱ ተከታዮች ለሶላት ሲመጡ የስለት መሳሪያዎችንና ሌሎች አዋኪ ነገሮችን ይዘው ባለመምጣት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ስቴድየም የሚደረገውን የሶላት ስነስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንምይፋ አድርጓል:-

➢ ከቦሌ- ኦሎምፒያ -ፍላሚንጎ ወደ መስቀል አደባባይ

➢ ከኡራኤል-ባምቢስ ወደ ምስቀል አደባባይ

➢ ከአራት ኪሎ - ብሔራዊ ቤተመንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያ

➢ ካሳንችስ -ብሔራዊ ቤተመንግስት -ፍልውሀ

➢ ከንግድ ማተሚያ ቤት -ኦርማ ጋራዥ- ፍል ውሃ -ሐራምቤ ሆቴል

➢ ከቴድሮስ አደባባይ -ኢምግሬሽን- ሀራምቤ ሆቴል - ስቴድየም

➢ ከጎማ ቁጠባ- ብሄራዊ ትያትር- ስቴድየም

➢ ከሰንጋ ተራ - በድሉ ህንጻ -ስቴድየም

➢ ከሰንጋ ተራ - በለጋሀር- ስቴድየም

➢ ከሜክሲኮ አደባባይ- በለገሀር -ስቴድየም

➢ በቂርቆስ አዲሱ መንገድ -በለገሀር -ስቴድየም

➢ በሀራምቤ ሆቴል -ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ

➢ ከጎተራ - በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ:-

ከቦሌ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች

➢ በኡራኤል -በካሳንችስ-አራት ኪሎ
ከመገናኛ ወደ ጦር ሀይሎች መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች

➢ በኡራኤል -ካሳንችስ -ታላቁ ቤተመንግስት -እሪበከንቱ -ቴዎድሮስ አደባባይ- ኤክስትሪም ሆቴል- ተክለሀይማኖት- ጦር ሀይሎች ከሳሪስ አቅጣጫ ወደ አራትኪሎ እና ፒያሳ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች

➢ ጎተራ -ወሎ ሰፈር - አትላስ ሆቴል - ኡራኤል - ካሳንችስ -አራት ኪሎ ያሉ መንገዶች በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከዛሬ ነሀሴ 14/2010 ማታ ጀምሮ የሶላት ስነስርዓቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በስታድየም ዙሪያ እና አከባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጹም #የተከለከለ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ሕብረትሰቡ ለጸጥታ #አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥሮች

• 011-5- 52-63-03
• 0115-5- 52- 40-77
• 011-5- 52- 63-02
• 011-1- 11-01-11 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

©EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

ሰሞኑን ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአዲስ አበባ ሰፋፊ ቦታዎች ዳግም በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይወረሩ #ጥበቃ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽህፈት ቤት ለቦታዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ለደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ትዕዛዝ አስተላልፏል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል...

በሕገ-ወጥ መንገድ #የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ አካላትን #በማጋለጥ ጥቆማ እንዲሰጥ የከተማው ነዋሪ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ ጥሪውን ያቀረበው የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤት ኖሯቸውም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የወሰዱ ካሉ፣ ነዋሪው እንዲጠቁመው ይፈልጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት በፌስቡክ ገጹ እንዳስረዳው፣ ታጥረው የቆዩ የከተማዋን መሬት ወደ መንግስት እንደመለሰው ሁሉ በጋራ መኖሪያ ቤቶችም ላይ ምርመራውን ቀጥሏል፡፡ የቤት ችግር ላለባቸው ነዋሪዎች ታስቦ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በህገ-ወጥ መንገድ በያዙት ላይ፣ በተደረገው #ፍተሻ የተገኘውን ውጤት እንደሚገለፅም ተጠቁሟል፡፡
እስከዚያው ነዋሪዎች፣ ሰው ሳይገባባቸው የቆዩ፣ በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን እንዲጠቁሙ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬇️

በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ #የጦር_መሳሪያዎች እና #ስለታም ነገሮችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የአድማ ብተና እና ልዩ ኃይል ዘርፍ ኃላፊ በምክትል ኮሚሽነር ማዕረግ መሳፍንት ሙሉጌታ እንደገለጹት በሀዋሳ ከተማ መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች በተደረገው #ፍተሻ 3 ስታር #ሽጉጥ የተለየዩ ስለታማ መሳሪያዎችና 834 ሺህ ብር መያዙን ገልፀዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለጻ የፀጥታ አካሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የከተማውን ሠላም ለማስጠበቅ በቋሚና ተንቀሳቃሽ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝና በዚህም አምስት ግለሰቦት የጦር መሳሪያዎችንና ስለታማ ጩቤዎችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ በድንገት በተደረገው ፍተሻ በጎድጓዳ፣ ጥቁር ውሃ እና ታቦር ክፍለ ከተማ እንደተያዙ አስረድተው ግለሰቦቹ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል ሲል የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሮክተሬት ዋና ሳጅን ደጀኔ አሰፋ አስረድተዋል።

©የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ⬇️

በአዲስ አበባ መስመር ወደ አዳማ ከተማ ሊገባ የነበረ 17 ሽጉጥና 45 ጥይት ዛሬ በተደረገ ድንገተኛ #ፍተሻ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ልዩ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ሳጅን #ወርቅነሽ_ገልሜቻ እንደገለፁት ዛሬ ከጠዋቱ 1፡30 አካባቢ በአሰላ መስመር ወደ አዳማ መግቢያ ልዩ ስሙ ሶደሬ መንገድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 2 ሹጉጦች ተይዘዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ከአዲስ አበባ ቃሊቲ መነሃሪያ የተነሳው ኮድ 3 – 42617 ኦሮ ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አዳማ ከተማ መግቢያ ላይ ልዩ ስሙ መልከአዳማ በተባለው ስፍራ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ደግሞ 15 ሽጉጦችና 45 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

የጦር መሳሪያው ባለቤት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ጥርጣሬ የሚያጭሩ የተለዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥመው ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት #እንዲተባበር ዋና ሳጅን ወርቅነሽ መልእክት አስተላለፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ ወጥ መሳሪያ ተያዘ‼️

በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ ሰላም ፖሊስ በሕገ-ወጥ ሲነቀሳቀስ የነበሩ 15 ሽጉጦችን #በቁጥጥር ስር ዋለ።

ከደሴ ወደ መካነ ስላም ሲጓዝ በነበረ በተለምዶ ‹ሃይሩፍ› በተባለ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ከተሳፋሪ ጋር ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረን የጦር መሳሪያ ነው የመከነ ስላም ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ #ፍተሻ በቁጥጥር ስር ያዋለው፡፡

የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው ደረሰ በከተመዋ ‹በግለሰቦች ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘዋወራል› የሚባል ጥርጣሬ ስላለ እና በከተመዋ ሰዓት እየጠበቀ ተኩስ ስለሚሰማ በሳምንት ውስጥ በተመረጡ ቀናት ድንገተኛ ፍተሻ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በድንገተኛ ፍተሻው መሠረትም ፖሊስ 15 የቱርክ ስሪት የሆኑ ‹ኢኮል› ሽጉጦች በሻንጣ ሲጓጓዙ ይዟል፡፡ ይሁን እንጅ በፍተሻ ወቅት ሰዎች ከመኪና ወርደው ስለነበር ተጠርጣሪው ሳይያዝ ማምለጡን ዋና ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ግለሰቡ ለጊዜው ቢያመልጥም
‹‹ሽጉጦች ከተያዙበት ሻንጣ ውስጥ ማንነቱን የሚገልጹ የባንክ ደብተር እና የመካነ ሰላም ከተማ ነዋሪነቱን የሚያሳይ መታወቂያው ተገኝቷል›› ብለዋል ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ.ቤትም ማዘዣ በማውጣት ግለሰቡ ወደ ሕግ እንዲቀርብ ጥብቅ ክትትል እያደረገበት እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ተጠርጣሪው ግለሰብ ከዚህ በፊትም ሕገ-ወጥ መሳሪያዎችን በማዘዋወር ሲታማ የነበረ እና ለረጅም ጊዜ ክትትል
ተደርጎበት ሳይያዝ የቆየ እንደሆነም ኃላፊ ጠቁመዋል፡፡

ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው የመካነ ስላም ፖሊስ በተጠናከረ መልኩ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሮችን እንደሚቆጣጠር እና በየዓመቱ
ከአምስት እስከ ስድስት የጦር መሳሪያዎችን ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በመያዝ ለመንግሥት ገቢ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደምም አምስት ሽጉጦችን እንደያዙ ነው ኃላፊው ያስታወቁት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሉአባቦር ዞን‼️

በኢሉአባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 43 #ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 44 የጥይት ካዝና መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለፁት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከትላንት በስቲያ ሲሆን ከጋምቤላ ክልል በኮድ 3 -92943 ኢትዮጵያ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በቡሬ ወረዳ ሲቦ ቀበሌ በተደረገው #ፍተሻ ነው።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢፍጣራችን ለወገናችን " ሶስተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የፊታችን ቅዳሜ ዕለት / ረመዳን 17 ይከናወናል ተብሏል። የዘንድሮው ኢፍጧል " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። የቅዳሜው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት ጉዳት ያደረሰባቸዉና የተቸገሩ ወገኖቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ በሰጡት መግለጫ…
#ረመዷን

" ኢፍጣራችን ለወገናችን "

ምዕመናን ነገ መጋቢት 30 በአዲስ አበባ በሚካሄደው " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ' ሲመጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ደንቦች አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል።

1. የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ፍተሻ ትብብር ማድረግ፤

2. የሰላት መስገጃ ይዘው ይምጡ፤

3. ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ተደርጓል። ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲያሳውቁ።

5. የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅር እና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበው ህብር ብሄራዊ አንድነነቱን በማሳየት ለሃገር ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

6. በዕለቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ ለተቸገሩ ወገኖች የሚሆን ፦
- እንደ ፉርኖ ዱቄት፣
- ሩዝ ፣
- ፓስታ፣
- መኮረኒ፣
- ዘይት፣
- የበቆሎ እህል፣
- ምስር፣
- የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች፣
- የሕፃናት አልሚ ምግቦች
- የንጽህና መጠበቂያ፣
- አልባሳት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይዞ መምጣት ይቻላል።

(ከአዘጋጆቹ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ

ዛሬ በአዲስ አበባ " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ' ይካሄዳል።

ምዕመናን ስትመጡ የሚከተሉትን እንዳትዘነጉ ፦

- ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ፍተሻ ትብብር ማድረግ።

- የሰላት መስገጃ ይዞ መምጣት።

- ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ተደርጓል። ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

- የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅር እና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበው ህብር ብሄራዊ አንድነነቱን በማሳየት ለሃገር #ሰላም እና #ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

- ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎች እና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ አሳውቁ።

- በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ።

(ከአዘጋጆቹ)

@tikvahethiopia
" በኢሬቻ በዓል ላይ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ  ፁህፎችና መልዕክቶችን ይዞ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ ነው " - ግብረ ኃይሉ

እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚገኝባቸው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ አርሰዲ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ።

ይህን የገለፀው የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ነው።

በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተሞች የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፎ ይከናወናል ብሏል።

በአዲስ አበባ ለሚከበረው በዓል ለወንጀል መከላከል ተግባር ልዩ ትኩረት መሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን አብዛኛውን የሰው ኃይል  በወንጀል መከላከል ስራ ላይ እንዲሰማራ መደረጉ ተነግሯል።

በኢሬቻ በዓል ላይ ምን ተከልክሏል ?

- ከባህላዊ አከባበሩ ተቃራኒ የሆኑ ተግባራት መፈፀም አይቻልም።

- ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ  ፁህፎችና መልዕክቶችን ይዞ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

- ባህላዊ ሥርዓቱን ሊያውክ የሚችል ማኛውም ተግባር ማከናወን ፍፁም የተከለከለ ነው።

ግብረ ኃይሉ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች #ፍተሻ መኖሩን ተገንዘበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።

ህብረተሰቡ ማንኛውም አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ መስጠት ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
" ከአባ ገዳ አርማ ውጭ ማንኛውም አይነት የፖለቲካ ድርጅት አርማ ይዞ መገኘት አይቻልም " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

ነገ ቅዳሜ እና እሁድ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ማንኛውንም የፖለቲካ ድርጅት አርማ ይዞ መገኘት እንደማይቻል ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፤ ከአባገዳ አርማ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ በበዓሉ ላይ ይዞ መገኘት እንደማይቻል አሳስቧል።

ኢሬቻ የአንድነትና የወንድማማችነት በዓል እንደሆነ ያስገነዘበው የክልሉ መንግሥት በዓሉ ያለ እምነትና ብሄር ልዩነት በአንድ ላይ ፈጣሪ የሚለመንበትና የሚመሰገንበት ነው ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፤ በኢሬቻ በዓል ላይ ከባህላዊ አከባበሩ ተቃራኒ የሆኑ ተግባራት መፈፀም እንደማይቻል አሳስቧል።

ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ  ፁህፎችና መልዕክቶችን ይዞ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች #ፍተሻ መኖሩን ተገንዘበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነገ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይኖር በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

ቢሮው በአምስት በሮች እንግዶችን በመቀበል ፦
- በጀሞ 3 ፣
- በቃሊቲ ቶታል፣
- ቱሉ ዲምቱ፣
- የካ ጣፎ፣
- አየር ጤና፣
- አዲሱ ገበያና ሳንሱሲ የከተማ አውቶብስ ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የታክሲና ሀይገር ተሸከርካሪዎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራውን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

ነገ በአዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል የበዓሉ ታዳሚዎች እየገቡ ሲሆን በየአካባቢውን የተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ወጣቶች በባህላዊ ልባሰቸው አሸብርቀው በየጎዳናው ላይ እየተዘዋወሩ ባህላዊ ጨዋታዎች እየተጫወቱ ለነገው በዓል እየተዘጋጁ ናቸው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ይኖሩናል።

@tikvahethiopia