#Ethiopia
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ2020 ጀምሮ ምንም ፈንድ ያላገኘችው ኢትዮጵያ ብድር እንዲለቀቅላት ከIMF ተከታታይ ድርድሮች እያካሄደች ነው።
ከIMF 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደጠየቀች ተነግሯል።
ድርጅቱ ብደሩን ለመስጠት ኢትዮጵያ ብር ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም #እንዲዳከም ማድረግ እንዳለባት እንደጠየቀ ተጠቁሟል።
ግን ይህ እንደቅድመ ሁኔታ ይቀመጥ አይቀመጥ ድርጅቱ ማረጋገጫ አልሰጠም። ነገር ግን ተለዋዋጭ የሆነ የገበያ ሁኔታ የሚወስን የውጭ ምንዛሬ ተመን መኖር እንዳለበት እንደሚያምን ሮይተርስ አስነብቧል።
ምንም እንኳን እየተካሄዱ ባሉ ተከታታይ ድርድሮች በኢትዮጵያ እና IMF መካከል ልዩነቶች ቢኖሩም ስምምነት ላይ የመድረስ #ተስፋ_እንዳለ የIMF የኢትዮጵያ ልዑክ አልቫሮ ፒርስ ተናግረዋል።
ፒስርስ ፥ " አሁንም ልዩነቶች ቢኖሩም ድርድር ግን ቀጥሏል። አስቸጋሪ ነግሮች ቢኖሩም ስምምነት ላይ የመድረሱ ተስፋ አለ " ብለዋል።
የኢትዮጵያን #የኢኮኖሚ_ሪፎርም_መደገፍ ላይ በአብዛኛው ስምምነት እንዳለ ነው የተሰማው።
ከዶላር አንጻር የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም ከፍተኛ በሆነ የዋጋ ንረት እየተፈተነች ላለችው ኢትዮጵያ ይበልጥ ፈተና ሊሆንባት ይችላል።
ግን ደግሞ IMF የግዴታ ያ ካልተደረገ ብድር አለቀም ካለ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ውጭ ምንዛሬ እጥረት ውስጥ የምትገኝ በመሆኑ ሌላ አማራጭ ላይኖራት ይችላል የሚሉ አሉ።
ከቀናት በፊት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ እና የብሄራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ በተገኙበት ከIMF ኃላፊ ክሪስታሊያ ጆርጂያ ጋር ተገናኝተው መክረው ነበር።
ምክክሩ IMF በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሪፎርም በሚደግፍበት መንገድ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተጠቅሷል። ዝርዝር ጉዳዩ ግን አይታወቅም።
መረጃው የሮይተርስ ነው።
@tikvahethiopia