ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #በታጣቂዎች በፈጠሩት የጸጥታ ስጋት ቀደም ሲል ለተረጅዎች ዕርዳታ ለማድረስ የሄዱ 5 ከባድ መኪናዎች ለ28 ቀናት መመለስ አለመቻላቸውን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሸገር ተናግሯል፡፡
በኮሚሽኑ የአቅርቦትና ሎጅስቲክ
ዳይሬክተር #ሐይድሮስ_ሀሰን እንዳሉት ኮሚሽኑ ባሁኑ ሰዓት በ10 ካሚዮኖች አስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ ቢያስጭንም በጸጥታ ስጋት ሳቢያ ወደ ካማሺ ዞን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ ለአማራጭ በአማራ ክልል ኢንጅባራ በኩል ለመላክ የታሰበ ሲሆን የቤንሻንጉል ክልል መንግሥትም በፖሊስ አሳጅባለሁ ብሏል፡፡
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopa

ፕሬዘዳንቱ ታፈኑ‼️
የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር #ደላሳ_ቡልቻ ትላንት ከደንቢዶሎ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ላይ ሳሉ #በታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸው ተሰማ።
ምንጭ:- ELU,Jawar Mohammed
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Update በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ በ6 ከተሞች 11 ባንኮች #በታጣቂዎች_ተዘርፈዋል። ከተዘረፉት መካከል በቀቤ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በመቻራ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በጋባ ሮቢ ከተማ የኦሮሚያ ህብረትስራ ባንክ ይገኙበታል። እንዲሁም በጉሊሶ ከተማ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ እና የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ፤ በኢናንጎ ከተማ ንግድ ባንክና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፤ በጫንቃ ከተማ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተዘርፈዋል።
via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ግጭቱ የተከሰተው የማኅበረሰቡ አባላት ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ርምጃ ነው!"-- የቅማንት ኮሚቴ ሊቀመንበር ፈቃዱ ማሞ
በአማራ ክልል ጎንደር ሰሞኑን #በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 22 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፕሬዚደንት ደሳለኝ ጫኔን ጠቅሶ እንደዘገበው፦ ግጭቱ የተፈጠረው ባለፈው ዐርብ ታጣቂዎች ወደ ጎንደር የሚጓዙ ሰዎችን ከሚኒባስ አስወርደው 10 ሰዎችን ከገደሉ በኋላ ነው ብሏል። በሚቀጥለው ቀን 12 ወታደሮች መገዳለቸውንም አክለው ጠቅሰዋል ብሏል ሮይተርስ። ፕሬዚዳንቱ የደረሰው ጥቃት ከቅማንት ኮሚቴ ጋር ይያያዛል ማለታቸውንም ዘግቧል።
የቅማንት ኮሚቴ ሊቀመንበር ፈቃዱ ማሞ ወቀሳውን አስተባብለው ግጭቱ የተከሰተው የማኅበረሰቡ አባላት ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ርምጃ ነው ማለታቸውንም የዜና ምንጩ አትቷል። የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ «በጥናት ላይ የተመሰረተ የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ» መዘጋጀቱን በመግለጥ «ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እየተሠራ» ነው ሲል አስታውቋል።
Via ሮይተርስ /DW/

#ከሰሞኑን
(ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት)
- በኢህአዴግ ዘመን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ " የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር " ሆነው ሰሞኑን ተሹመዋል።
በሌላ የሹመት መረጃ ፤ የቀድሞ የ " ብአዴን " ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱ ተቋሙን ለ10 ወራት በዋና ዳይሬክተርነት የመጡር አቶ ብሩ ወልዴ ከኃላፊነት በመልቀቃቸው ነው።
- ሰሞኑን አሜሪካ ፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ ፣ ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም እና የሰላም ድርድር እንዲጀመር በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።
በመግለጫው ፦
• ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወታደራዊ ግጭት እንዲቆም ፤ ይህንን ለማድረግ ስምምነት እንዲደረስ፣
• የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ
• #የኤርትራ_ሠራዊት ከግጭት ተሳትፎው እንዲታቀብ እና ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዲወጣ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር መለስ ዓለም ፥ " መግለጫው ከዚህ በፊት ከወጡት መግጫዎች የተለየ ነገር የለውም " ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ፤ " መንግሥት ሰላም እንዲመጣ ቀደም ሲል የወሰዳቸው የመተማመን ምንፈስ የሚፈጥሩ እርምጃዎች አሉ። " ያሉ ሲሆን " መንግሥት ለሰላም ዝግጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሞኢቦን በቀለ ከትላንት በስቲያ በቡራዩ ከተማ እና አዲስ አበባ አዋሣኝ (ልዩ ቦታው ሳንሱዚ) ቤታቸው አካባቢ ምሽት 1 ሰዓት ገደማ " ማንነታቸው ባልታወቀ " ሰዎች #በጥይት_ተመተው መገደላቸውን ፓርቲው ገልጿል። አቶ ሞኢቦን በቀለ በጥይት ከተመቱ በኃላ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም። ኦነግ ግድያው ፤ " በገለልተኛ አካል " ይጣራሊኝ ሲል ጠይቋል።
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፤ መተከል ዞን፤ ማንዱራ ወረዳ #በታጣቂዎች_ጥቃት የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ሂስ ሄጮን ጨምሮ ስድስት (6) ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾች መካከል ሹፌራቸው እና አንድ የመከላከያ ፤ ሶስት የፌዴራል ፖሊስ ይገኙበታል።
- የኢትዮጵያ መንግስት #ለአይርላንድ በፃፈው ደብዳቤ ሀገሪቱ " በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ደባ እየፈፀመች " መሆኑን በመገልፅ ከዚህ አይነት ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል። ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያያዞ አየርላንድ " ህወሓትን በመደገፍ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ውስጥ ያላትን የተለዋጭ መቀመጫ በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲፈጠር ግፊት እያደረገች ነው " ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት እንዲሻክር እየተንቀሳቀሰች ነው ሲል ገልጿል። ሀገሪቱ ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል።
NB. አየርላንድ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ለም/ቤቱ ጥያቄ ከሚያቀርቡ አገራት መካከል ዋነኛዋ ናት።
#ከሰሞኑን ፦ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰቡ እና በአጭሩ የቀረቡ።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ወንጂ🕯 ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ። እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል። " አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል። ከተገደሉት…
#ወንጂ🕯
ለስራ በወጡበት #በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ ተገድለው ከተገኙት ዜጎች መካከል አንዱ አቶ ግርማ በላቸው እንደሚባሉና የኢትዮ ስኳር ፋብሪካ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ/ማ የስራ ባልደረባ እንደነበሩ ተነግሯል።
ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው በታጣቂዎች ታግተው ፤ በግፍ ተገድለው የተገኙት ለወንጂ ስኳር ፋብሪካ ድጋፍ ለመስጠት በወጡበት ነው።
በኦሮሚያ ክልል ፤ በቅርቡ የጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 አባቶች ታግተው በግፍ መገደላቸው የሚዘነጋ አይደለም።

#ኮሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በኮሬ ዞን በተፈጸመ ጥቃት 3 ታዳጊ ልጆችን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገደሉ። ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት በጎርካ ወረዳ ፤ " ቆቦ ቀበሌ " ነው ተብሏል። የኮሬ ዞን አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ፥ ለንጹሐን አርሶ አደሮች ሞት ምክንያት ለሆነው ጥቃት " በምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና ፀረ-ሰላም " ሲል የጠራቸውን አካላት ተጠያቂ አድርጓል። እንደ አካባቢው…
“ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ” - ነዋሪዎች
በኮሬ ዞን ፤ #በታጣቂዎች አማካኝነት ንጹሃን ላይ የሚደርስ ጥቃት በእርቀ ሰላም ተፈቶ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ከ4 ወራት ወዲህ በማገርሸቱ የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል።
ባለስልጣናቱና ነዋሪዎቹ ለድርጊቱ የ " ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች " ን ተጠያቂ አድርገዋል።
የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ ምን አሉ ?
➡️ “ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች በቀጠናው ላይ ገብተው 4 ሰዎችን በአንድ ቀን ገድለዋል። ”
➡️ “ የመንግሥት መዋቅር እዛ አካባቢ ላይ Functional ስላልሆነ ኦነግ ሸኔ በነጻነት ተንቀሳቅሰው በቀጠናው ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ። ”
➡️ “ እርቅ ተፈጽሞ ከኀዳር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ወዲህ ከጉጂ ዞን ጋ መልካም ግንኙነት ተፈጥሮ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከ4 ወራት ወዲህ ታጣቂዎቹ እንደገና ጥቃት እያደረሱ ነው። ”
ቃላቸውን የሰጡን የቆቦ ቀበሌ ነዋሪ ምን አሉ ?
👉 “ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ተገድለዋል። 4ቱ የቆቦ ቀበሌ ነዋሪዎች እሁድ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከብት በሚጠብቁበት ነው የተገደሉት። "
👉 “ከዚያ በፊት ዳኖ ቀበሌ 2 ሰዎች ተገድለዋል። ሌላም የሞተ አለ። ”
👉 “ ታጣቂዎቹ #ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ጥቃት ያደርሱ ነበር በዚህም ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ”
👉 “ በ2015 ዓ/ም እርቅ ተፈጽሞ ጥቃቱ ቆሞ ነበር። ከወራት ወዲህ ጥቃቱ አገርሽቶ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ”
👉 “ በቆቦ ቀበሌ እርቁ ከተፈጸመ ወዲህ ብቻ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ”
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን አካል ምን አሉ ?
▪️ “ በቀን 08/08/2016 የሁለት አርሶ አደሮች ሕይወትም አልፏል። እስከ ሚያዚያ 8/2016 ብቻ 19 ንጹሐን ከህዳር 1/2015 ዕርቅ በኋላ ተገድለዋል። ”
▪️ “ ከ19ኙ ሟቾች በተጨማሪ እሁድ ሚያዚያ 13 በቆቦ ቀበሌ፦
- ተመን እንግዳ ሶልዳንቶ
- ይርጋ ሚትኩ ሶልዳንቶ
- ነብዩ ቡና
- አባይ ፍቅሬ የተባሉ ሰዎች ተገድለዋል። ”
▪️ “ ንጹሐንን የገደሉ ለሕግ ይቅረቡ። ”
ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#Amhara የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ። በወረዳው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ትለንትና በምሽት በመግባት እንደገደሏቸው ተሰምቷል። ወረዳው ባወጣው የሀዘን መግለጫው ፥ " አቶ አልብስ ለዓመታት በቀውስ ነጋዴዎች ለችግር ተጋልጦ የሴራ ፖለቲካ መሸቀጫ የተደረገውን የጀውሃና አካባቢው ማህበረሰብ ቀርቦ በማወያየት መተማመን ፈጥሮና አደራጅቶ ወደ ቀደመ…
#AmharaRegion
ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ተገደሉ።
የቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።
ወ/ሮ ሚሊሹ በዛሬው እለት ነው የተገደሉት።
እንደ ወረዳው መረጃ ፥ የመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ውለው ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ነው ጥቃት ተሰንዝሮባቸው የተገደሉት።
ግድያ የተፈጸመባቸው አመራሯ በእናትነት ላይ ነፍሰ ጡርነትን ይዘው እንደነበር ተገልጿል።
የወረዳው አስተዳደር ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ " ግድያው የተፈጸመው በጽንፈኛ አካላት #በተተኮሰ ጥይት ነው " ብሏል።
ከቀናት በፊት የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪው አቶ አልብስ አደፍራሽ #በታጣቂዎች_መገደላቸው ይታወሳል።
በሌላ በኩል ከሰሞኑን በወልዲያ ከተማ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ #የቦምብ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል።
ጥቃቶቹ በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤትና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ ነው የተሰማው።
ጥቃቱ አነጣጥሮባቸው ነበር ከተባሉት ውስጥ፦
➡️ የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ
➡️ የወልዲያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ ይገኙበታል።
መኖሪያ ቤታቸው ላይ ነበር ጥቃት የተፈጸመው።
ከዚህም ባለፈ የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።
" #ባልታወቁ_አካላት " ተፈጽሟል በተባሉት ጥቃቶች በባለስልጣናቱ ላይ ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።
በቅርቡ የጉባ ላፍቶ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በፖሊስ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ተነግሯል።
ባለፈው #ሚያዚያ ወር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ከስብሰባ ሲመለሱ በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም።
#TikvahEthiopia
#BBCAmharic