የጢስ ዓባይ ባህር ዳር የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ስርቆት ተፈፀመበት !
ከጢስ ዓባይ የውሃ ኃይል ማመንጫ ወደ ባህር ዳር የተዘረጋው ባለ 132 ኮሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ላይ ስርቆት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ።
ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በተፈፀሙ ስርቆቶች 8 ምሰሶዎች ወድቀዋል፡፡
ይሁንና በአካባቢው ኃይል እንዳልተቋረጠ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ምሰሶዎቹ በመውደቃቸው ከኃይል ማመንጫው በባህር ዳር ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ይላክ የነበረ እስከ 30 ሜጋ ዋት ኃይል መላክ አልተቻለም፡፡
ችግሩንም በየደረጃው ለሚገኙ የመስተዳድር አካላት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን የወደቁትን ምሰሶዎች በመጠገን ወደነበሩበት ለመመለስ የጥገና ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Update
የግብፅ፣ የኢትዮጵያ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቅዳሜ በኪንሻሳ ተገናኝተው በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ለሶስት ቀናት የሚካሄደውን ስብሰባ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቺሲኬዲ ይመሩታል ተብሏል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በውይይቱ ላይ እንደሚገኙም መገለፁን አል ዓይን ዘግቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ የሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ት/ቤቶች አይሰጥም ! በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለዘንድሮ የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከነገ የካቲት 29 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በሀገር ውስጥ ይሰጣል። ይህ ፈተና በመጨረሻ ሰዓት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት #በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች እንደማይሰጥ…
#Update
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በውጭ ሀገር በሳዑዲ አረቢያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤት የ2012 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ከ2013 ተፈታኞች ጋር ፈተናውን እንደሚወስዱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አስታውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሪ እንደገለፁት ፥ ፈተናውን በጊዜ መስጠት ያልተቻለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ነው ብለዋል፤ ከሁለት ወር በኃላ የ2013 ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ አብረው እንዲወስዱ ይደረጋል ሲሉ ተናገርዋል።
ትክክለኛው ጊዜ ባይወሰንም ግንቦት ወይም ሰኔ ላይ ፈተናው ይሰጣል።
የ12ኛ ክፍል ፈተና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች በመጨረሻ ሰዓት መሰረዙን ተገልጾ ነበር።
ከቀናት በፊት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በትግራይ ክልል በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን ካለባቸው ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱት 2,130 እንደሆኑ ገልፆ የቀሩት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ከ2013 ተፈታኞች ጋር ከሁለት ወር በኃላ ፈተናውን እንዲፈተኑ እንደሚደረግ መግለፁ አይዘነጋም።

በሰሜን ምዕራብ ሪጅን የ4ጂ አገልግሎት ጀመረ።
በባህር ዳር እና በአካባቢው ሲከናወኑ የነበሩ የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎች ተጠናቀው ዛሬ የሞባይል ኢንተርኔት በፍጥነት መጠቀም የሚያስችለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ (LTE Advanced) አገልግሎት በይፋ ጀምሯል።
በባህር ዳር ከተማ በተደረገው የፕሮጀክቱ የምርቃት ስነስርዓት ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ እንደተናገሩት ፤ አገልግሎቱ በሰሜን ምዕራብ ሪጅን የሚገኙትን ፦
- ባህርዳር፣
- ደብረማርቆስ፣
- ቻግኒ፣
- ፍኖተ ሰለም፣
- እንጂባራ፣
- ዳንግላ እና ቡሬ ከተሞችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን የኢፕድ ዘግቧል።

"...በ2 ብሔሮች መካከል ፀብ እንደተነሳ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው" - ፖሊስ
ዛሬ ጥዋት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት "አትክልት ተራ" በሁለት ግለሰቦች መካካል በተፈጠረ ፀብ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
ከጠዋቱ በግምት 2፡00 ሰዓት አካባቢ በሁለት የጉልበት ሰራተኞች መካከል በስራ አለመግባባት ምክንያት በተፈጠረ ፀብ የአንደኛው ሕይወት ማለፉን እና ገዳዩ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አሳውቋል።
የተወሰኑ ግለሰቦች የግድያ ወንጀል በፈፀመው ተጠርጣሪ ላይ ጉዳት ለማድረስ በፈጠሩት ፀብ ምክንያት በፖሊስ አባላትና በአካባቢ ጥበቃ ስራ በተሰማሩ አጋዥ ሀይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
ግርግሩን ለማብረድ ፖሊስ ባደረገው ጥረት አካባቢው ተረጋግቶ መደበኛ ሰራ መጀመሩን እና ግርግር በማስነሳት ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ አሰታውቋል፡፡
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሁለት ብሔሮች መካከል ፀብ እንደተነሳ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

የ9 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ ፦
በ22/07/ 2013 ዓ/ም ከጥዋቱ 3 ስአት ሲሆን መነሻውን በማዕ/ዊ ጎንደር አይከል ከተማ ያደረገው አንድ አባዱላ (በተለምዶ) የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የታርጋ ቁጥር ኮድ-3 -22330 አማ ወደ ጎንደር እየተጓዘ እያለ በማዕ/ዊ ጎንደር አስተዳደር ዞን ምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ድርማ ቀበሌ ሲደርስ ድርማ ወንዝ ድልድዩ ላይ ዘሎ በመግባትና በመገልበጡ አሽከርካሪውን ጨምሮ የ5 ወንዶችና የ4 ሴቶች በድምሩ የ9 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።
በ2 ሴቶችና በ 3 ወንዶች በድምሩ በ 5 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ቁስለኞቹ በጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
መረጃው የማዕ/ዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ የኮ/ሚድያ ዋና ክፍል ነው።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳትደናገጡ!
ዛሬ ምሽት ከ3 ሰዓት እስከ 4:30 በአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ለግንባታ ስራ ሲባል "ድማሚት" ስለሚፈነዳ ህብረተሰቡ በሁኔታው እንዳይደናገጥ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ስፍራ ላይ ነው ድማሚቱ የሚፈነዳው፡፡
በመሆኑም ሕብረተሰቡ በሁኔታው እንዳይደናገጥ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
#ሼር #Share

"መንግስት ከመግለጫ የዘለለ ተጨባጭ እና የሚታይ ስራ ይስራ" -የቲክቫህ አባላት በ @tikvahethiopiaBot
በተለያየ ጊዜያት በተለያዩ ክፍሎች ላይ ያለሃጢያታቸው ስለሚገደሉት ንፁሃን እና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው ሴቶች ፣ ህፃናት ፣ ገበሬዎች፣ እናቶች መንግስት ከተደጋጋሚ መግለጫ በዘለለ ተጨባጭ ስራ ሰርቶ ሊያስይ እንደሚገባ የቲክቫህ አባላት አሳስበዋል።
እየተገደሉ ያሉት ዜጎችን ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ የሌሉ እና በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ሽኩቻን እንኳን በቅጡ የማያውቁ ናቸው ብለዋል።
ጥቃቶች የሚፈፀሙት አንዴ ወይም ሁለቴ አይደለም እጅግ ተደጋጋሚ ነው ፤ የአንድ ሰሞን አጀንዳ ሆነው እያለፉ በርካቶችን እያሳጣ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ምድር በየትኛውም ክፍል ስለሚገደሉ ንፁሃን መንግስት በየጊዜው መግለጫ ከመስጠት ባለፈ የሚታይ እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ሊፈልግ ይገባል ብለዋል።
የችግሮቹን ስፋት፣ ሁኔታና ትክክለኛ መንስኤዎችን በአግባቡ ለህዝብ ሊገልፅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
አንድ ጊዜ ረገብ እያለና እየተረሳ፣ የአንድ ሰሞን አጀንድ እየሆነ ዘላቂ መፍትሄ ሳይገኝ ዛሬም የንፁሃን ሞት ቀጥሏል ብለዋል።
በሀገሪቱ የሞት፣ የስቃይ ዜና መስማት እየተለመደ መጥቷል ፤ ይህን ነገር ነገ ሳይሆን ዛሬ መፍትሄ ይፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል።
ከሞት፣ ከአካል ጉዳት፣ ከንብረት ውድመት በተጨማሪ በታዳጊ ልጆች ስነልቦና ላይ እያሳረፈ ያለው እጅግ ከባድ ተፅእኖ ትኩረት እንደሚፈልግ አሳወቀዋል።
በተጨማሪም በየትኛውም ጊዜ ዜጎች ስለደረሰባቸው በደል እና ስለሚደርስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሚናገሩበት ወቅት "ስም በመለጠፍ" ዜጎች ዝም እንዲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራው ህዝብን የሚያራርቅ ስራ ሊቆም ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
@tikvahethiopia

#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷
ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,294 የላብራቶሪ ምርመራ 2,372 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,327 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 208,961 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,890 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 159,436 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 853 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

Audio
የምዕራብ ወለጋው ግድያ ?
ከሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ዞን የተፈፀመው ግድያ በ "ኦነግ ሸኔ" እንደሆነ የዞኑ የፀጥታ እና አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዩ ምህረቱ ይገልፃሉ።
ለዚህም በቂ የሆነ ማረጋገጫ አለኝ ይላሉ ፤ ጥቃት ከፈፀሙት ውስጥ 3ቱ በፀጥታ ኃይሎች ተገድለው የ "ኦነግ ሸኔ" ታጣሪዎች ናቸው ህብረተሰቡ እንዲያቸው ተደርጓል ብለዋል።
ንፁሃንን እየገደለ ያለው "ኦነግ ሸኔ" ስለመሆኑ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም ተጨባጭ ህብረተሰቡ የሚናገረው መሬት ላይ ያለ እውነታ ነው ሲሉ አስረግጠዋል።
.
.
"...መንግስት ኦነግ ሸኔ ነው የገደላቸው ካለ ኦነግ ሸኔ የሚባል ድርጅት ፈልገህ አናግር -አቶ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ)
አቶ ኩምሳ ድሪባ (መሮ) "ኦነግ ሸኔ" ስለሚባል ነገር አይመለከተኝም፤ በማያገባን ጉዳይ ሳንጠራ አቤት ምንልበት ምክንያት የለም፤ እኛ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነን፤ በዚህ ስም የቀረበብን ክስ የለም ሲሉ ትላንት ምሽት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።
የኦነሰ በንፁሃን ግድያ እጁን አያስገባም የሚሉት አቶ ኩምሳ ድሪባ፤ በሰራዊቱ የተከሰተ ግድያ የለም ሲሉ ይናገራሉ።
አንድ ብሄር መሰረት ያደረገ ቀርቶ አንዲት ነብስ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እጅ ቢጠፋ ከባድ ተጠያቂነት ነው ያለው ብለዋል።
አቶ ኩምሳ፥ "..ይሄ ነገር ተደጋገመ ብዙ ዩቱበሮች ፣ ከሁኔታው ርቀት ያሉ አክቲቪስቶች ንግድ አድርገውታል ፤ መወቃቀሱ መወነጃጀሉ ለነኚህ ለሚያልቁት አማራ ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ አንበል ኢትዮጵያዊም አንበል ፥ ለሚያልቁት ንፁሃን የእግዜር ፍጡራን መጫወቻ ቁማር መሆን የለበትም እና እንዲህ ያለው ግድያ ኢትዮጵያ ውስጥ በዝቷል ገለልተኛ አካል ያጣራ" ብለዋል።
በሌላ በኩል በማህበራዊ ሚዲያ "መሮ" ተደገለ ተብሎ የሚወራው ሀሰት ነው ብለዋል።

#DrAbiyAhmed
ዛሬ መጋቢት 24 ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙበት ቀን ነው።
ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 3 ዓመት ነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዶክተር አብይ አህመድን (በዛን ወቅት የኢህአዴግ ሊቀመንበር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሰየመው።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚታየው ጠ/ሚሩ ወደስልጣን ከመጡበት ጊዜ ያሳኳቸውን፣ የተገበሯቸውን ተግባራት በማንሳት የሚደግፏቸው ፤ በአንፃሩ ያሉ ጉድለቶችን በማንሳትም የሚቃወሟቸው በርካቶች ናቸው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"..የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ሁሉንም ጎረቤቶቻችን በተለይም የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች የሆኑትን ሱዳን እና ግብፅን በእጅጉ የሚጠቅም ነው።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ወንዙ ተሸክሞት ይሄድ የነበረው ደለል ስለሚቀር በግብፅ እና በሱዳን ያሉ ግድቦች በተለይም በደለል እየተሞላ የሚሰጠው ጥቅም በከፍተኛ መጠን የቀነሰው የሱዳን የሮሰሪስ ግድብ ከዚህ አደጋ ነፃ ይሆናል።
.
.
ጥቅሙ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገሮች በተለይ ለሱዳን እና ግብፅ ጭምር በመሆኑ ፍትህ የሰፈነበት ሁኔታ ቢኖር የግድቡን ወጪ 3ቱም ሀገራት ሊሸፍኑት በተገባ ነበር።
እያንዳንዱ ሀገር ከግድቡ በሚያገኘው ጥቅም ልክ ወጪውን ይሸፍን ቢባል ሱዳን የወጪውን 30%፣ግብፅ የወጪውን 20% መሸፈን በተገባቸው ነበር።
ይሁንና በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ እንዲህ አይነቱ ገንቢና ፍትሃዊ አሰራር ሊሰፍን አልቻለም፤በመሆኑም ወጪው በሙሉ ኢትዮጵያ ለመሸፈን ተገዳለች።
ይባስ ብሎ ግድቡን ለመስራት ብድር እና እርዳታ እንዳናገኝ የተለያዩ ኃይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበረን ሀገር ወይም ተቋም ማግኘት አልቻልንም።
ስለሆነም ወጪውን ብቻችንን ከመሸፈን አልፈን ከራሳችን ቁጠባ ለመሸፈን የምንገደድበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
.
.
ያለን አማራጭ አንድም ግድቡን አለመስራት፥አለበለዚያ እንደምንም ወጪውን በራሳችን መሸፈን ነው። ከነዚህ ሁለት ከባድ አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ እንደሚሆን ግልፅ ነው።በተለመደው ወኔው ምንም ያህል ድሃ ብንሆንም ድህነታችንን ለማስወገድ ማንኛውም መስዋዕነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፤ ስለዚህ ፕሮጀክቱ መሰራት አለበት እንደሚል ለአፍታም ያህል አልጠራጠርም"
የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ
መጋቢት 24/2003 ዓ.ም ከተናገሩት

የ2012 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት በአጭር ጊዜ ነው ይፋ የተደረገው ፥ ፈተናው እንዴት በዚህ ፍጥነት ታርሞ ይፋ ሊሆን ቻለ ?
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ዲለሞ ኦቶሬ በትላንትና ምሽት የቢቢሲ ሬድዮ ስርጭት ላይ ቀርበው ከላይ በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እሳቸው እንዳሉት የመጀመሪያው ምክንያት በሰላም መጠናቀቁ ነው። ፈተናው በሰላም ባይጠናቀቅ ኖሮ የሚጣራ ጉዳይ፣ በፖሊስ የተያዘ ጉዳይ፣ የዝርፊያ ሁኔታ ስለሚኖር የእርማቱ ጊዜ እንዲዘገይ ያደርገዋል ብለዋል።
ሁለተኛው የሰዓት አጠቃቀም ሲሆን፥ ፈተናው ሲታረም የነበረው በፈረቃ 24 ሰዓት ነው። ተማሪዎች በፈተናው መዘግየት ስለተጎዱ ሌላው ቢቀር ውጤቱ በቶሎ ይገለፅ የሚል አቋም ተወስዶ ነው ፈተናው የታረመው ሲሉ ገልፀዋል።
ፈተናውን ለማረም ምንም አይነት አዲስ ቴክኖሎጂ በትግበራ ላይ ያልዋለ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ በDRS ሲስተም (በማሽን) ነው የታረመው አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል የ2013 ፈተና በኦንላይን እንዲሰጥ ውጤቱም እዛው በኦንላይ እንዲታወቅ የሚደረግበትን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።
ከ2013 የፈተና ዝግጅት ጋር በተያያዘ ፦
- የቀረው የታብሌት መግባት ብቻ ነው።
- ታብሌቶቹ ከሆንግኮንግ የሚመጡ ሲሆን በኮቪድ-19 ምክንያት አልገቡም።
- ወደ900 ሺህ ተማሪ ስለሚፈተን፤ 900 ሺህ ታብሌት እንዲመጣ እየተደረገ ነው።
- ለሌላ ዓመት ተማሪዎች ታብሌቱን በአግባቡ እንዲቀመጥ ተደርጎ እንዲጠቀሙበትም ማድረግ ይቻላል።
- ከታብሌት ውጭ ሌላው ዝግጅት ያለቀ ነው። ላፕቶፖች ገብተዋል፣ ኢንተርኔት የሚገኝበት ቴክኖሎጂ በየፈተና ጣቢያው ተተክሏል።
PHOTO:NEAEA (2019)

የG7 ሀገራት መግለጫ ፡
የካናዳ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ጃፓን ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩኤስኤ የሚገኙበት የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የትግራይን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ የጋራ መግለጫ አወጡ።
በመግለጫው የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ፣ በቅርቡ ሪፖርት የተደረጉ በትግራይ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች እንዲሁም የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ ጥሰት በጣም አሳስቦናል ብለዋል።
መግለጫው አክሎ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ ያለውን “ግድያ ፣ ጾታዊ ጥቃቶችን ፣ ያለ ልዩነት የሚፈጸም ከባድ ድብደባ እና በትግራይ ነዋሪዎች እና የኤርትራ ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን አስገዳጅ መፈናቀል” እንደሚያወግዙ ገልፀዋል።
ሁሉም ወገኖች የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ እና የሰብዓዊ መብቶችን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ማክበር እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ለእንዲህ ዓይነት ጥሰቶች ተጠያቂ መሆን ያለባቸውን ለመጠየቅ ላሳየው ቁርጠኝነት እውቅና የሰጠው መግለጫው መንግስት ቃሉን ተግባራዊ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በቅርቡ ጠ/ሚ ዐቢይ የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ይወጣሉ በሚል ያወጡትን መግለጫ በደስታ እንደሚቀበሉም መግለጫው ጠቁሟል፡፡ ይህ ሂደት በፍጥነት ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈጸም እንዳለበትም ነው የተገለጸው፡፡
የቡድን 7 ሀገራት ፥ “አመጽ እንዲቆም እና ትግራይን ጨምሮ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና ወደ ተአማኒ ምርጫ እና ወደ ሰፊ ብሔራዊ እርቅ የሚወስድ ግልፅ ፣ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል።
More : telegra.ph/AlAIN-04-02-4
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

የተሰረቁ የመኪና መለዋወጫዎችእና 4 ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
የአዲስ አበባ ፖኪስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለልማት ተብለው በተዘጋጁ የመንግስት ቦታዎች ላይ ፖሊስ በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ባደረገው የአሰሳ ስራ በርካታ የተሰረቁ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
የምርመራ ስራም እየተሰራ መሆኑን አሳውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ክልል ልዩ ቦታ አሜሪካን ግቢ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
መንግስት ለልማት ብሎ ባዘጋጀቸው ቦታዎች ላይ ግለሰቦቹ በህገ- ወጥ መንገድ የሸራ ቤት ወጥረው ለተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባርና ለወንጀል መሸሸጊያነት በማዋል ከተለያዩ ቦታዎች የሰረቋቸውን የመኪና እቃ መለዋወጫዎችን በዚሁ የሸራ ቤት ውስጥ አከማችተው በደላላ አማካኝነት በተለምዶ ሱማሌ ተራ እየተባለ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ ለሌሎች ግለሰቦች ሲሸጡ እንደነበረ የምርመራ ውጤቱ አመላክቷል።
ከተያዙት የመኪና እቃ መለዋወጫዎች መካከል ፦
- 183 ስፖኪዮ፣
- 122 የመኪና የፍሬን ጉሚኒ፣
- 21 ፍሬቻ ባለመስታወት ፣
- 3 የመኪና ቴፕ፣
- 36 የመኪና ቸርኬ ጌጣጌጥ በኤግዚቢትነት መያዛቸውን ፖሊስ አሳውቋል።
ንብረት የጠፋባቸው ግለሰቦች በወቅቱ ወደ አቅራቢያቸው ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ስለማመልከታቸውና የጠፋባቸውን የእቃ አይነት ማስረጃዎችን ይዘው በመቅረብ ንብረታቸውን መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።
መረጃው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መርካቶ አካባቢ ፖሊስ ነው።