TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እና ሳይንስ፦

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ዛሬ በጎጃም እና ሸዋ በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ዝናብ አዘነብን ማለታቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል።

ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ተጨባጭ ሳይንስ ነው ?

የብሄራዊ ሚትሪዮሎጂ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ክንፈ ኃ/ማርያም ዛሬ ምሽት በነበረው የቢቢሲ ሬድዮ ስርጭት፥ "...በቤጂንግ ኦሎምፒክ መክፈቻ ቀን ቻይና በዓሉን በብሩሃማ ቀን ለማክበር ብላ ተጠቅማበታለች። ያ ምን ማለት ነው ደመናማ ሆኖ በዛ ቀን ሊዘንብ የነበረውን በቤጂንግ ኦሎምፒክ አካባቢ በዝናብ መልክ ቀድሞ በማበልፀግ መክፈቻውንም መዝጊያውንም በብሩህ ቀን እንዲከበር አድርጋለች" ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

አቶ ክንፈ፥ "ደመናው ከሌለ ዝናቡን ማበልፀግ አይቻልም ፤ ደመናውን መፍጠር አንችልም፤ ዝናብ ለማበልፀግ ዝግጁ የሆነ ደመና በተፈጥሮ መምጣት አለበት ፤ ሳይንሱም እሱን ነው የሚነግረን ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያን በቴክኒክም በፋሲሊቲም እያገዙ የሚገኙት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) መንግሥት እና የሜትሪዮሎጂ ማዕከል ናቸው ተብሏል።

ቴክኖሎጂው እየተሞከረ ያለው ቀጥታ ከUAE በመጣ ኤርክራፍቱ እና ንጥረ ነገር መሆኑ ነው የተሰማው።

https://telegra.ph/Ethiopia-03-23-2
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ዛሬ ማምሻውን በላከልን መልዕክት ነባር ተማሪዎቹ ከመጋቢት 28-30/2013 ድረስ ወደዩኒቨርስቲው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል።

ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ፦

የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የሆናችሁ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲው በወሰነው መሰረት የመግብያ ቀን መጋቢት 28-30/2013 ዓ/ም መሆኑ ኣውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

ከሰላምታ ጋር!
የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ረጅስትራር ፅ/ቤት

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia🇪🇹

ዛሬ ከቀኑ በ10:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የማዳጋስካር አቻውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚገጥም ይሆናል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ለማለፍ 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ይቀሯታል።

ዛሬ ከማዳጋስካር ጋር የምታደርገው እና ከአንድ ሳምንት በኃላ መጋቢት 21 ከኮትዲቯር ጋር (በአቢጃን) የምታደርገው ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማት እንመኛለን።

@tikvahethsport
በትግራይ_ክልል፣_አክሱም_ከተማ_የተፈጸመው_ከፍተኛ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰት_ምርመራ_ሪፖርት.pdf
610.2 KB
የአክሱም ሪፖርት ፦

በኣክሱም ከተማ ትግራይ ክልል የደረሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፣ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርቱን ትላንት ለሊት ይፋ አድርጓል።

ከበርካታ ሳምንታት ጥረት በኋላ የምርመራ ባለሞያዎቹን ወደ አክሱም ከተማ መላክ መቻሉን ገልፆ ፤ ባለሞያዎቹ ከየካቲት 20 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ድረስ በከተማዋ በመቆየት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን፣ 45 የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዓይን ምስክሮችን እና የሃይማኖት መሪዎችን አነጋግሯል። እንዲሁም 20 ሰዎች የተሳተፉበት የቡድን ውይይት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር አድርጓል።

በተጨማሪ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል፣ ከአክሱም ሪፈራል ሆስፒታል፣ ከሚመለከታቸው የቀበሌ መስተዳደር አካላት እንዲሁም ከሃይማኖት ተቋማት አገልጋዮች የተለያዩ የምስል፣ የድምጽ እና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቧል።

ኢሰመኮ በዚህ ምርመራው ያሰባሰባቸው መረጃዎች በተለይ ከኅዳር 19 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበሩት ሁለት ቀናት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈፀመ አረጋግጧል።

- የአክሱም ከተማና አከባቢው ነዋሪዎች፣
- ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ጦርነት ሸሽተው በከተማዋ የተጠለሉ ተፈናቃዮች እና
- የኅዳር ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር ከተለያየ ቦታዎች የመጡ ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከአንድ መቶ በላይ ሲቪል ሰዎች በወቅቱ በአክሱም ከተማ በነበሩ #የኤርትራ_ወታደሮች መገደላቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል።

*ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ በPDF ፋይል ተያይዟል (በዝርዝር እንመለከተዋለን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ጠራ። የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2013 ተመራቂ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎቹን መጋቢት 5-6 ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል። በ2013 ተመራቂ ያልሆኑ መደበኛ ተማሪዎቹን ደግሞ ከመጋቢት 15 -16 ወደ ግቢ እንዲገቡ ነው ጥሪውን ያቀረበው። የ2013 ተመራቂ ተማሪዎች የሆናችሁና በሽረና በዋናው ግቢ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ሪፓርት የምታደርጉት በዋናው ግቢ ሲሆን የጤና…
ማስታወሻ ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች :-

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የ2013 ተመራቂ ያልሆናችሁ መደበኛ ተማሪዎች ከመጋቢት 15 -16 ወደ ግቢ እንዲገቡ ነው ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

በዚህም በሽረ እና በዋናው ግቢ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ሪፓርት የምታደርጉት በዋናው ግቢ ሲሆን የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በነበራችሁበት ሪፓርት እንድታደርጉ ተብላችኋል።

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ለሚያከናውነው የሰብዓዊ መብት ድጋፍ 170 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ።

በክልሉ በተካሄደው ውጊያ ምክንያት ዜጎች ለከፋ ሰብአዊ መብት ጥሰት ተዳርገዋል ያለው ፕሮግራሙ ለተጎጂዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ለይ በክልሉ ለተፈናቀሉና ለምግብ እጥረት ለተዳረጉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ 170 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ብሏል።

4.5 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም የምግብ ድርጅት ከነዚህ ውስጥ ለ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች እየደገፈ መሆኑን አስታውቋል።

በትግራይ ክልል የተካሄደው ውጊያ የሰብል ስብሰባ በሚካሄድበት ወቅት መሆኑ የተጎጂ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል የሚለው ድርጅቱ ገበያዎች፣ሰብሎች እና ሌሎች መሰረታዊ መገልገያዎች ከጥቅም ዉጪ መሆናቸውን መግለፁን አል ዓይን ኒው በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...እሳቱ በሰው ኃይል ይጠፋል ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ ደርሷል" -ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ By : መ/ር አቤል አሰፋ-ኢኦተቤ ቴቪ ከትላንት ጀምሮ በደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም የሰደድ እሳት ቃጠሎ ተነስቷል። በደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም የተነሳው ሰደድ እሳት ለማጥፋት ከጭሮ /አሰበተፈሪ/፣ አሰቦት መኢሶ እና ከአካባቢው ወረዳዎች ወደ ሥፍራው የተጓዙ ምእመናን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም…
#Attention

አሰቦት ገዳም ዙሪያ የተነሳው እሳት ዛሬም ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም ፤ እሳቱ አቅጣጫውን እየቀያየረ ለቁጥጥር አዳጋች አድርጎታል።

ከቀናት በፊት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ለኢኦተቤ ቴቪ ፥ እሳቱ በሰው ኃይል ይጠፋል ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አሳውቀው መንግሥት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ይገባዋል ሲሉ አስገንዝበው ነበር።

ዛሬ ሌሊት ሙሉ ለሙሉ ገዳሙ ሙሉ ዙሪያውን በእሳት ተከቦ እንዳደረ ወደ ገዳሙም የገባ እንደሆነ ጉዳዩን እየተከታተሉ ለህዝብ እያሳወቁ ከሚገኙ መካከል መምህር ኤፍሬም ዘደብረወግ የተባሉ ወንድም አሳውቀወል።

እንደ አዲስ በተለያየ አቅጣጫ እሳት እየተነሳ ነው ያለው። በጠፉ ቦታዎች ጭምር እንደ አዲስ እየተነሳ መሆኑ ተገልጿል።

በአራቱም አቅጣጫ በመናንያኑ መኖሪያ ከቤተክርስቲያኑ በ25 ሜትርና በ50 ሜትር ርቀት ላይ ደርሷል።

ወጣቶች ብዙ ኪ.ሜ ርቀት ተጉዘው መጥተው እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ቢሆንም እሳቱ በሰው ኃይል የሚጠፋ አልሆነም።

እሳቱን በማጥፋት በርከታ ሰዎች እየተሳተፉ ቢሆንም እነሱ በመዳከማቸው አዲስ የሰው ኃይል ያስፈልጋል ፥ የሚችልም ወደቦታው እንዲሄድ ተጠይቋል።

ምግብ እንደሞከሮኒ፣ ፓስታ ፣ ዱቄት፣ ውሃ እና በቀላሉ እዛው የሚሰሩ የሚችሉ ነገሮችም ይሳፈልጋሉ።

ይህ እሳት በሰው ኃይል የማይጠፋበት ደረጀ በመድረሱ የሚመለከተው አካል ሁሉ በአስቸኳይ ሌሎች አማራጮችን እንዲፈልጉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#SNNPRS

በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ጉንድራ ገራ ቀበሌ ከሰሞኑ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው በረዶ ከ7 መቶ 80 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ በነበሩ ቋሚና ዓመታዊ ሠብሎችና የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በጉዳቱ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ሠብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።

መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዴቻ ወረዳ ጉንድራ ገራ ቀበሌ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው በረዶ ከ 6 መቶ 31 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የነበሩ ቡና ፣ ኮረሪማና እንሠትን የመሳሰሉ ቋሚ ሠብሎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ ከ1 መቶ 53 ሄክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ የነበረ የበቆሎ ችግኝን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ አድርጓል፡፡

በጉዳቱ ሳቢያም 312 እማወራና አባወራዎች ሥር የሚተዳደሩ ከ1 ሺ 5 መቶ 60 በላይ ሠዎች ለችግር ተዳርገዋል፡፡

በ780 የቀንድ ከብቶችና 556 የጋማ ከብቶች ላይም በረዶው ጉዳት አድርሷል ፡፡

በአካባቢው የጣለው በረዶ ከዚህ ቀደም ተከስቶ የማያውቅና ከባድ ነበረ ነው ተብሏል።

አደጋው በጉንድራ ገራ ብቻ ሣይሆን በጉንድራ ሸላ ቀበሌ ላይ የተከሰተ በመሆኑ ሠብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚያስችል የአደጋውን መጠን የመለየት ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ደ.ሬ.ቴ.ድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብልፅግና ፓርቲ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ቅንጀት መሰረቱ።

ገዢው የብልፅና ፓርቲና ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) በመጪው አገራዊ ምርጫ በጋራ ለመወዳደር ያስችለናል ያሉትን ቅንጅት መመስረታቸውን ዐስታወቁ።

የፓርቲዎቹ አመራር ዛሬ ረፋድ በሀዋሳ ኃይሌ ሪዞርት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳሉት የፊታችን ግንቦት ወር ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ 2013 በጥምረት ለመወዳደር ከሚያስችላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በይፋ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቬለ (DW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ ፦

የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ሊመሰረት የሚያስችለው የሪፈረንደም (ህዝበ ወሳኔ) ምርጫ ሊደረግ 65 ቀናት ገደማ ይቀሩታል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን የሚያደራጅ በቦርዱ ስር የፕሮጀክት ቢሮ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለፋና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ይህ የፕሮጀክት ቢሮ ዋናው የሀገር አቅፍ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ባሉ የኦፕሬሽናል ስራዎች እንዳይዋጥ የሚያስችል ነው።

እስከሁን በፕሮጀክት ቢሮው ፤ የህዝበ ውሳኔ በጀት ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል እንዲሁም የህዝበ ውሳኔው አክሽን ፕላን (እቅድ) ተዘጋጅቷል።

ቦርዱ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ያዘጋጀው በጀት 8 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው። ገንዘቡ ከሌሎች የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ሲሆን ሪፈረንደሙ ከሀገር አቀፍ ምርጫው ጋር በአንድ ቀንና በአንድ አይነት ዝግጅት የሚካሄድ በመሆን የወጪ ብክነት አስቀርቷል ተብሏል።

ገንዘቡ በዋናው የምርጫ በጀቱ ውስጥ ስለሌለ ተጨማሪ በሚል ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል ፤ ምላሹን እየተጠባበቀ ይገኛል።

የሪፈረንደም ወጪ በቦርዱ አይሸፈንም ፤ ከዚህ በፊት የሲዳማ ክልል ሪፈረንደም ሲደርግ ወጪው የተሸፈነው በደቡብ ክልል ምክር ቤት ነበር።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የክልል ሪፈረንደም አሁን ላይ በምርጫ ምልክት መረጣ እና ውሳኔ ደረጃ ላይ ይገኛል። ምርጫ ቦርድ ከመራጩ ህዝብ ተወካዮች በኮሚቴ የቀረበለትን የባለ 6 እጆች ጥምረት ተቀብሎ መልሶ ለይሁንታ ልኮታል።

ምልክቱን ሲያፀድቁ የድምፅ መስጫ ወረቀት መታተም ይጀምራል።

የደቡብ ክልል የሚወከለው በ "ጎጆ" ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 ዛሬ ከቀኑ በ10:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የማዳጋስካር አቻውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚገጥም ይሆናል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ለማለፍ 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ይቀሯታል። ዛሬ ከማዳጋስካር ጋር የምታደርገው እና ከአንድ ሳምንት በኃላ መጋቢት 21 ከኮትዲቯር ጋር (በአቢጃን) የምታደርገው ነው። ሀገራችን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለት ጎል አስቆጥሯል።

በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ #ማዳጋስካር አቻው ጋር እየተጫወተ የሚገኘው የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን በኣማኑኤል ገ/ሚካኤል እና ጌታነህ አማካኝነት ሁለት ጎል ማስቆጠር ችሎ ጨዋታውን 2-0 በሆነ ውጤት እየመራ ነው።

ጨዋታውን ሂደት እና ውጤት በቲክቫህ ስፖርት በኩል መከታተል ትችላላችሁ @tikvahethsport

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ሶስተኛ ጎል በአቡበክር ናስር አማካኝነት አገባች።

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም #የማዳጋስካር አቻውን እያስተናገደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአቡበክር ናስር አማካኝነት 3ኛውን ጎል አግብቷል።

የመጀመሪያው የጨዋታው አጋማሽ በኢትዮጵያ የ3 ለ 0 መሪነት ተጠናቋል።

* ከላይ በቪድዮ የተያያዘው የጌታነህ ከበደ ሁለተኛ ጎል ነው።

More : @tikvahethsport
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ 4 - 0 ማዳጋስካር

ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ጋር ያደረገችውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች። አራተኛው ጎል በሽመልስ በቀለ አማካኝነት የተገኘ ነው።

More : @tikvahethsport
አጫጭር የምርጫ 2013 መረጃዎች ፦

- ነገ መጋቢት 16/2013 ዓ/ም የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ይጀምራል። የመራጮች ምዝገባ ነገ ጀምሮ የሚጠናቀቀው ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ነው። (እንደምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ)

- የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከትላንት ጀምሮ ለምርጫ ክልሎች ማሰራጨት ጀምሯል፡፡ ቦርዱ ለአንድ ወር ለሚቆየው የመራጮች ምዝገባ ለ673 የምርጫ ክልሎችና 50 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን ነው ማጓጓዝ የጀመረው።

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ለመራጮች ምዝገባ ያለውን የቁሳቁስ ዝግጅት ለብዙኃን መገናኛ አካላት አስጎብኝቷል፤ በጉብኝቱ ወቅት የኮሚኒኬሽን ኃላፊዋ ወ/ሪት ሶሊያ ሽመልስ እንዲሁም የቦርዱ የሎጂስቲክ ድልድልና ሥርጭት ባለሙያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

- በአፋር ክልል 8 ቀበሌዎች ሊከፈቱ የነበሩ 30 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳይቋቋሙ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል። በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች በአቅራቢያቸው ባለ ሌላ ቀበሌ መመዝገብ እና ድምጻቸውን መስጠት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።

• በጋላእቶ/አዳይሌ
• በአዳይቱ/አዳይቱ
• በቴውኦ/አላሌ
• በጉርሙዳሊ/ዳንሌሄላይ
• በኡንዳፎኦ/ኡንዱፎ • በጋዳማይቱ/ጋርባኢሴ
• በአፍዓሶ/አፉአሴ
• በባላእቲ ጎና/መደኒ ቀበሌዎች ነው ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ የተወሰነው።

@Tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention አሰቦት ገዳም ዙሪያ የተነሳው እሳት ዛሬም ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም ፤ እሳቱ አቅጣጫውን እየቀያየረ ለቁጥጥር አዳጋች አድርጎታል። ከቀናት በፊት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ለኢኦተቤ ቴቪ ፥ እሳቱ በሰው ኃይል ይጠፋል ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አሳውቀው መንግሥት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ሌሎች አማራጮችን መጠቀም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Attention

ይህ አጭር ቪድዮ የደብረ ወገገ አሰቦት ገዳም ሰደድ እሳትን የሚያሳይ ሲሆን ከምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት (EOTC TV) የተገኘ ነው።

ዛሬ ከሰዓት ላይ እንዳጋራናችሁ መረጃ እሳቱ በተለያየ አቅጣጫ እየተነሳ ለመቆጣጠር ፍፁም አስቸጋሪ ሆኗል ፤ በሰው ኃይል እሳቱን ማጥፋት ከባድ ስለሆነ ሌሎች አማራጮች እንዲፈለጉ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል ፦

በአንኮበር ወረዳ ወፍ ዋሻ ደን ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እስካሁን መቆጣጠር አልተቻለም።

ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በርካታ በጎ ፈቃደኛ የጎረቤላ ከተማ ወጣቶች ፣ የወረዳው መንግስት ሰራተኞችና እሳቱ በተከሰተበት አካባቢ ያሉ የዘጎ፣ የመሐልወንዝና የሐርአምባ ቀበሌ ነዋሪዎች ቦታው ድረስ በመሄድ እሳቱን ለማጥፋት የቆረጣ ስራና ልዩ ልዩ መንገዶች ሲጠቀሙ የነበሩ ቢሆንም እሳቱን ማጥፋት ከአቅም በላይ እንደሆነባቸው የአንኮበር ወረዳ አሳውቋል።

8 ሽህ 732 ነጥብ 28 ሄክታር ከሚሸፍነው ጠቅላላ ደን ውስጥ በአብዛኛው ማለትም 5 ሽህ 434 ነጥብ 78 ሄክታር (62.24%) በአንኮበር ወረዳ የሚገኘው የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ከመጋቢት 13/2013 ዓ.ም እኩለ ቀን ጀምሮ በእሳት እየነደደ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopia
የኤርትራ ጦር በአል ፋሽጋ ?

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) 'አል ፋሽጋ' አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች ሰፍረዋል በማለት ሪፖርት አውጥቷል።

ይህ ቦታ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር ጉዳይ የሚወዛገቡበት ነው።

የኤርትራ ጦር ሰፍረዋል የተባለው በአወዛጋቢው አል ፋሽጋ ልዩ ስሙ "ባርካት" በተባለ ቦታ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ብሉምበርግ በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ምላሽ ለማግኘት ስልክ ቢመታላቸውም ስልካቸው እንዳልተነሳለት አሳውቋል።

የተመድ ሪፖርት የወጣው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የኤርትራ ጦር ድንበር ተሻግሮ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ካመኑ በኃላ ነው።

ትላንት ዶ/ር አብይ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማትፈልግ ገልፀዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ፥ "ሱዳን አሁን ባለችበት ሁኔታ ከጎረቤት ሀገር ጋር ለመዋጋት የሚያስችል ነገር ላይ አይደለም ያለችው በጣም ብዙ ችግር አለባት ፤ ኢትዮጵያም አሁን ባለችበት ሁኔታ ከሱዳን ጋር ለመዋጋት ብዙ ችግር አለባት ፤ ለሁለታችንም አይስፈልገንም በሰላም በንግግር መፍታት ነው የሚሻለው" ሲሉ ነው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተናግሩት።

የብሉምበርግ ዘጋባ : https://www.bloomberg.com/news/articles/2021-03-24/eritrea-forces-deployed-in-disputed-sudan-ethiopia-area-un-says

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT