TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፀጥታች ችግር ያላባቸው አካባቢዎች ፦

ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ መደፍረስ ፣ እና ከባድ የተኩስ ልውውጥ የነበረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ዛሬ ጋብ ብሎ ቢታይም አሁንም ግን አካባቢዎቹ ከስጋት ቀጠና አልወጡም።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች አሁንም የፀጥታ ስጋት እንዳለባቸው ለAMMA ተናግረዋል።

ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ ናቸው።

ዙጢ ከተማ ላይ የታጠቁ ሰዎች ጥቃት ፈፅመው ንብረት ወድሟል ፤ ንብረት ተዘርፏል ሲል AMMA ዘግቧል። (ዙጢ ከሸዋሮቢት በቅርብ ርቀት ላይ ነው የምትገኘው)

በማጀቴ ዛሬ ከባለፉት ቀናት በተሻለ ሁኔታው ጋብ ቢልም ስጋቱ አሁንም አለ።

ወደ አካባቢው የፀጥታ ኃይል ባለመግባቱ ነዋሪው የደህንነት ስጋት እንዳለበት የአካባቢው ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል ፤ አካባቢው ላይ ኔትዎርክ ይቆራረጣል ፣ መብራትም ተቋርጧል።

ከሚሴ አካባቢ ውጥረቱ እንደቀጠለ ፤ ዛሬም በተለያዩ አቅጣጫዎች የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ቲክቫህ ከሚሴ አባላት አሳውቀዋል። ነዋሪዎችም ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ እንደሆኑ ነው የገለፁት።

በፀጥታ መደፍረስ ጉዞ ለማድረግ ያሰቡ ወገኖችም መንቀሳቀስ አልቻሉም።

በአካባቢው #ተጨማሪ የሀገር መከላከያ ኃይል እና ፌዴራል ፖሊስ ተሰማርቶ የአካባቢውን ደህንነት እንዲያረጋግጥ አባላቶቻችን ጠይቀዋል።

ጀዋሀ እና አጣየ ከተሞች ያሉ የቲክቫህ አባላትን ለማግኘት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

የፀጥታ መደፍረስ ባጋጠመባቸው አካባቢዎች ላይ በርካታ ሀሰተኛና የፈጠራ ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ይገኛል ይህም ህዝቡን ይበልጥ እንዳይረጋጋ እያደረገው ነው።

[AMMA , Sheger FM , Tikvah Family Kamisee]

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! - በእነአቶ ጃዋር መዝገብ ከተጠቀጡት ተከሳሾች 18ቱ ዛሬ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፥ 17ቱ የእምነት-ክህደት ቃል ሰጥተዋል። - "የኦፌኮ አባል ብቻ ስለሆንኩ ነው የተከሰስኩት" - አቶ ጉቱ ሙሊሳ - "የቀረበብኝ ክስ ኦፌኮን ከምርጫ ለማግለል እና ለማዳከም ነው" - አቶ ደጀኔ ጣፋ - አቶ ደጀኔ ለጊዜው ካልተያዙ ግብረአበሮች ጋር በመሆን መገናኛ ብዙሃንን…
እነአቶ ጃዋር ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ. ም. የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ።

ዛሬ የእምነት ክህደት ቃል የሰጡት አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሀ እና አቶ ዓለማየሁ ገለታ ናቸው።

ተከሳሾቹ በቀረበባቸው ክስ ጥፋት አንደሌለባቸው ለፍርድ ቤት መናገራቸውን ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ ኢብሳ ገመዳ ተናግረዋል።

በአቶ ጀዋር ላይ ከቀረቡት ክሶች አንዱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች (አምስት ጳጳሶች እና ሁለት አገልጋዮች) እንዲገደሉ ማስተባበር የሚል ነው።

አቶ ጀዋር ቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ መሆኑን ጠቅሰው "በሃይማኖት አባቶች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚያስችላቸው ሁኔታ አንደሌለ" ተናግረዋል

የዛሬውን የችሎት ውሎ ያንብቡ (ቢቢሲ)👇
https://telegra.ph/BBC-03-22-2
በወፍ ዋሻ ደን እሳት ቃጠሎ ተነሳ።

በወፍ ዋሻ ደን ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል።

በአሁኑ ሰዓት እሳቱ ወደ እመምህረትና መስጫ ቀበሌዎች አድማሱን እያሠፋ መሆኑ ተገልጿል።

በአካባቢው ማህበረሰብ ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ማስቆም አልተቻለም፡፡

የክልልና የፌዴራል መንግሥት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ስፍራው የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን አብዛኛው ክፍል የሚገኝበት በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያስፈልገው የአንኮበር ወረዳ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
OJ_L_2021_099I_FULL_EN_TXT.pdf
17.1 MB
የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ጣለ።

የአውሮፓ ህብረት (EU) በሜ/ጄነራል አብርሃ ካሳ በሚመራው የኤርትራ ብሔራዊ ደህንነት ቢሮ (ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ) ላይ ማዕቀብ ጥሏል።

ማዕቀቡ የጉዞ እገዳ እንዲሁም የሀብት/ገንዘብ እገዳን ይጨምራል።

አውሮፓ ህብረት ማዕቀቡን የጣለው በኤርትራ ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን፣ በተለይም የዘፈቀደ እስራት ፣ ያለፍርድ ግድያ፣ የሰዎችን ደብዛ በማጥፋት እና በማሰቃየት ምክንያት ነው።

በተጨማሪም ህብረቱ ከሩስያ፣ ቻይና ፣ ሰሜን ኮሪያ ፣ ሊቢያ ፣ ደቡብ ሱዳን ግለሰቦች ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ማዕቀብ ጥሏል።

እንዲሁም ከማይናማር መፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ 11 ግለሰቦች ላይ መዕቀብ ተጥሏል።

ከEU የተገኘው ዝርዝር መረጃ ከላይ በPDF ተያይዟል (17 MB) ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
OJ_L_2021_099I_FULL_EN_TXT.pdf
ቻይና ማዕቀብ ጣለች።

ቻይና በአውሮፓ ህብረት 10 ባለሥልጣናትና አራት የአውሮፓ ህብረት ተቋማት ላይ የአጸፋ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።

ሀገሪቱ ማዕቀቡን የጣለችው የአውሮፓ ህብረት (EU) በሰብአዊ መብት ጥሰት ማዕቀብ በጣለባት በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ነው።

የአውሮፓ ኅብረት ተጠያቂ ያላቸው ቻይናውያን ላይ ማዕቀብ የጣለው ቺንያንግ በሚገኙ አናሳ ሙስሊም ማህበረሰቦች ላይ ለተፈፀመ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑን አስታውቆ እነዚህ ሰዎች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡና በአውሮፓ ኅብረት ሀገራት ያላቸውን ገንዘብ እንዳያንቅሱ ከልክሏል።

ቻይና በበኩሏ "ከባድ ጣልቃ ገብነት" ፈጽመዋል ፤ ዓለም አቀፍ ሕግጋትንም ጥሰዋል ባለቻቸው የአውሮፓ ኅብረት ተቋማት እና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሏን ዶቼ ቨለ (DW) ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AlertEthiopia😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 653 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረገው 6,922 የላብራቶሪ ምርመራ 1,537 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 15 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 1,119 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 188,902 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,674 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 148,571 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
OJ_L_2021_099I_FULL_EN_TXT.pdf
ኤርትራ የአውሮፓ ሕብረትን የማዕቀብ ውሳኔ ተቃወመች።

ውሳኔውን የተመለከተ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ህብረቱ ተፈጽመዋል ካላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ በኤርትራ ብሔራዊ ደኅንነት መ/ቤት ላይ ያሳለፈው የማዕቀብ ውሳኔ ተገቢነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡

ህብረቱ ኤርትራን በዚህ መልኩ ሊመለከት የሚችልበትና ለዚህ ውሳኔ የሚያበቃው “የሞራልም ሆነ የህግ ልዕልና” እንደሌለው በመጠቆም ውሳኔውን “መሰረተ ቢስ” ሲል አጣጥሏል፡፡

ህብረቱ “ቀጣናው (ምስራቅ አፍሪካ) ችግሮችን በራሱ እንዲፈታ ከማገዝ ይልቅ ህወሓትን ለመታደግ እየሰራ ይገኛል” ሲል ነው ሚኒስቴሩ በመግለጫው የወቀሰው፡፡

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥እንዲህ ባለ መንገድ ኤርትራን ዒላማ ማድረጉ በዋናነት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለው ግንኙነት “ሽብልቅ ለመቀርቀር” በማሰብ እንደሆነ ነው የገለፀው።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በአርባ ምንጭ "ሼቻ ገበያ" የእሳት አደጋ ደረሰ።

ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት 3:00 ሰዓት አከባቢ በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ገበያ ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት አደጋ ደርሷል።

አደጋው በአከባቢው ህብረተሰብ፣ በእሳት አደጋ ማጥፍያ መኪና እና በጸጥታ አካላት ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ የጉዳቱን መጠንና የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን የአርባ ምንጭ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰቆጣ እና አካባቢው ምን ተፈጥሯል ? የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን "የሰቆጣ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከአሉባልታ እና ሽብርን ከሚነዙ ሀይሎች ራሱን በመጠበቅ ከጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን አካባቢውን ይጠብቅ" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የአስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ፥ "በመከላከያ፣ አማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የህወሓት ቡድን የፃግብጅ ወረዳ…
በፃታው ጥቃት በርካቶች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በፃታ ከተማ በተፈፀመው ጥቃት የፃግብጅ ወረዳ የሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ጠቅልሌ ጌታሁንን ጨምሮ ብዙ ሰዎች መሞታቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የፃግብጂ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሄኖክ ነጋሽ በጥቃቱ የ76 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ እንደተረጋገጠ ገልጸው ሰላማዊ ሰዎችም በጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል ብለዋል።

ይህ አሃዝ እስከ ትናንት ድረስ የተገኘ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል።

በወቅቱ በማይጨው በኩል የነበረው የመከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው ሲደርስ ከተማዋ ተረጋግታለች ታጣቂዎቹ መከላከያ መጣ ሲባል ነው ከተማዋን ለቅቀው ወጡ፣ ከመከላከያ ጋር የተደረገ ተኩስም አልነበረም ተብሏል።

https://telegra.ph/BBC-Report-Tsata-City-03-23
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

ም/ቤቱ በስብሰባው የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ አፅድቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት ላቀረቡት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመው ለጥያቄዎቹ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-03-23

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በየአካባቢው ስላሉ ግጭቶች ፦

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ በየቦታው የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት ሕዝቡ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ሊቆም ይገባል አሉ።

በየቦታው እየታዩ ያሉ ግጭቶችን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ በመከላከያ ሰራዊት ብቻ ችግሩን ሙሉ በሙሉ መፍታት እንደማይቻል ስለሆነም ሕዝቡ ወታደራዊ አገራዊ ግዴታን ከመወጣት ጀምሮ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ግጭትና ሞት በቀላል በምኞት አይቆምም ፤ ስራ ይፈልጋል ያሉ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ዜጎች ወደው እና ፈቅደው እንዲሳተፉ ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል።

"እስካሁን ያያነው በፌስቡክ ነው የሚሳተፉት ፤ ፉከራ ብቻ ነው፤ በአካል ሄዶ አንድም ሰው የሚሳተፍ የለም፤ ይህ ተቋም በሰው ሀብት መገንባትና መጠናከር ይኖርበታል" ብለዋል።

ሰላም ፣ ልማት ፣ ዕድገት ይምጣ ሲል ወጣቱ በእነዚህ ተቋማት መሳተፍም ይኖርበታል እና ያልተሳተፈበትን ችግር አልተፈታም ማለትም ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"አንድ ቦታ ግጭት ሲፈጠር ዘለን መግባት አንችልም" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

ለህብዝ ተወካዮች ም/ቤት ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የትም ቦታ ላይ ችግር ሲፈጠር ሁሉንም ነገር ከፌዴራል መንግስት ጋር የማያያዝ ችግር አለ ፤ ይህ ደግሞ በሌላው ዜጋ ብቻ ሳይሆን በምክር ቤት አባላቱም ጭምር የሚታይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

አሁን ባለው የሀገሪቱ ቅርፅ ውስጥ የፌዴራሉ መንግስት ስልጣን የተከለለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

"እየተከተልን ባለነው የፌዴራል ስርዓት ውስጥ አንድ ቦታ ግጭት ሲያጋጥም ክልሉ ና እርዳኝ ካላለው በስተቀር የፌዴራል መንግስት ዘሎ መግባት አይችልም" ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ችሎት !

እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ፡፡

ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸመ ወንጀል ነው ያለው አቃቤ ህግ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሆነው አዲስ አባባ ቁጭ ብለው ሲፈጽሙ የነበረው ወንጀል አንድ ቦታ አለመሆኑን ማመላከቻ ነው ብሏል በምላሹ።

ይህ የሚያሳየው በሃገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች መፈጸማቸውን ስለሆነ በአካባቢ ስልጣን ሳይገደብ ጉዳያቸው መታየት ያለበት በፌዴራል ፍርድ ቤት ነው ሲል በጠበቆቻቸው ያነሱት መከራከሪያ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል።

ፍርድቤቱ ምርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ችሎቱ አቶ ስብሃት በግል ሃኪም እንዲታከሙ የታዘዘው ትዕዛዝ ተፈጻሚ እንዲሆን አዟል።

አምባሳደር አባይ ወልዱ ለዐይናቸው ህመም በግል እንዲታከሙ ያቀረቡት አቤቱታን ተቀብሎ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

https://telegra.ph/Ato-Sibhat-Nega-03-23
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ትግራይ መግባቱን ዛሬ በነበራቸው ማብራሪያ አረጋግጡ።

ነገር ግን የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንቅስቃሴ እያደረገ በእኛ ህዝብ ላይ በጥፋት በሚገለጽ የሚያደርጋቸውን ጥፋቶች በማንኛውም መንገድ አንቀበልም ብለዋል።

ይህንን የማንቀበለው የኤርትራ ጦር ስለሆነ ሳይሆን የእኛ ወታደርም ጥፋት አጥፍቶ ከሆነ አንቀበልም ሲሉ ገልፀዋል።

ዶ/ር አብይ ፥ ዘመቻው በግልጽ ከተለዩ ጠላቶች ጋር እንጂ ከህዝባችን ጋር አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ከኤርትራ መንግስት ጋር አራት አምስት ጊዜ ከፍተኛ አመራሮች ወደዚያም ወደዚህም ተልኮ ንግግር ሲደረግ መቆየቱን አሳውቀዋል።

የኤርትራ ጦር ይፈፅሟቸዋል ከሚባሉት በደሎች ጋር በተገናኘ፥ "ለኤርትራ መንግስት አቅርበናል፤ የኤርትራ መንግስት ይህንን በከፍተኛ መንገድ ነው የኮነነው፤ ማንም በዚህ ተግባር የሚሳተፍ የእኔ ወታደር ካለ እርምጃ እወስዳለሁ" ብሏል ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ዶ/ር አብይ አህመድ የኤርትራን ህዝብ እና መንግስት ዳግም አመስግነዋል።

"የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በገዛ ወገኑ ክህደት ተፈጽሞበት የኤርትራ ህዝብና መንግስት ወደ እሱ የሄዱትን ወታደሮች የያዘበት፣ ወደፈለጉበት እንዲሄዱ የደገፈበት መንገድ የሁል ጊዜም የኢትዮጵያ ባለውለታ ያደርገዋል" ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Eritrea---Ethiopia-03-23
#Silte

በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ በትላንትናው እለት በቡኔ ቀበሌ በደረሰ የቤት ቃጠሎ ከ78 ቤት ሙሉበሙሉ የወደመ ሲሆን በቤቶቹ ይኖሩ የነበሩ 450 ግለሰቦችን ቤት አልባ ከድርጓል።

ለጊዜው የእሳት አደጋው መነሻ በውል ባይታወቅም የ52 አባወራዎች ቤት ሙሉበሙሉ ሲወድም ከ57,500,000 ብር በለይ ንብረት ማውደሙን ተገልጿል።

በዕለቱ የነበረው የአየር ሁኔታ ነፋሻማና ወቅቱም በጋ መሆኑ ተደምሮ የእሳቱን ፍጥነት ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን በስፍራው የነበሩ አባወራዎች ለወረዳው መንግስት ኮመንኬሽን ተነግሯል።

በባለፋት ተከታታይ የበጋ ወራት በወረዳችን ከ98 በላይ ቤቶች በእሳት አደጋ ወድመዋል።

@tikvahethiopia
#AlertEthiopia😷

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደአስከፊ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 693 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረገው 7,092 የላብራቶሪ ምርመራ 1,692 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 19 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 1,019 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 190,594 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,693 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 149,590 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT