#UNESCO
ዓለም አቀፉ የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ለባለሙያዎች ስልጠና እና ለቁሳቁስ ማሟያ የሚሆን 74 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መመደቡን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
(AMMA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#UNESCO #ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት የዓለም አቀፍ የቅርስ ኮሚቴ የዩኔስኮ አባል ሆና ተመረጠች። ኢትዮጵያ በተመሳሳይ የዩኔስኮ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እና የዓለም አቀፍ ቅርስ ኮሚቴ አባል ሆና እንደምታገለግልም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#መስቀል
#ፍቼ_ጫምባላላ
#የገዳ_ስርዓት
#ጥምቀት
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO ) ያስመዘገበቻቸው የቅርሶች ብዛት 13 ደርሷል። እነዚህ ቅርሶች በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ የተመዘገቡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ አክሱም፣ የኮንሶ ባህላዊ እርከን ይገኙበታል። በሚቀጥለው ዓመት በማይዳሰስ ቅርስነት ይመዘገባል ተብሎ የሚጠበቀው አሸንዳ አሸንድዬ ይገኝበታል።
(BBC)

#UNESCO #WHO
" ... ድርጅቶቹ ያለአድሎ ኃላፊነታቸውን ሊወጡና የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ውድመት በይፋ ማውገዝ ይጠበቅባቸው ነበር " - አቶ ዮሴፍ ካሳዬ
ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ካሳዬ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተጠሪ ከሆኑት ዶ/ር ዮሚኮ ዮኮዝኪ እና የዓለም ጤና ድርጅት ተጠሪ ዶ/ር በርማ ኤች. ሳምቦ ጋር ተወያይተዋል።
በወቅቱም አቶ ዮሴፍ ፥ የህወሓት የሽብር ቡድን የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአፋር እና አማራ ክልሎች የባህላዊ ቅርሶች እና የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈጸመውን ውድመት ለማውገዝ ድርጅቶቹ ቸልተኝነት ማሳየታቸው ገልጸውላቸዋል።
አቶ ዮሴፍ ፥ " ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ንብረቶች ላይ የደረሰው ውድመት እና የንብረት ዘረፋ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው " ያሉ ሲሆን " የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በቸልታ ማለፉ ህወሃት በተግባሩ እንዲገፋበት አበረታቶታል " ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባልነቷ ከሁሉም የተመድ ድርጅቶች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላት አንስተው፣ ድርጅቶቹም ያለአድሎ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ውድመት በይፋ ማውገዝ ይጠበቅባቸው እንደነበረ አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።
የስራ ኃላፊዎቹ በበኩላቸው ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር ስላደረጉት ውይይት ምስጋናቸውን ገልፀው፣ ያላቸውን ኃላፊነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያን ጉዳይ በአንክሮ ለመመልከት ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#DrHirutKassaw የሻደይ፤ አሸንድየ እና አሸንዳ በዓላት በማይዳሰሱ ቅርስነት የመመዝገብ ጉዳይ በሚቀጥለው አመት በዩኔስኮ ድምጽ እንደሚሰጥበትና እንደሚመዘገቡ እንደሚጠበቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ለአልዓይን ተናግርዋል። የዘንድሮ አሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድየ በዓላት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ እየተከበሩ አይደለም። @tikvahethiopiaBot…
#UNESCO
በትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚገኙ ባህላዊ የሴቶች ጨዋታ የሆኑት አሸንዳ/ ሻደይ/ አሸንድዬ/ አይኒዋሪ/ ማርያ/ ሶለል በሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ምዝገባ ላይ UNESCO ዛሬ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ቢቢሲ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ታሪካዊ ትውፊቶቹ በቅርስነት እንዲመዘገቡ ለተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከአመታት በፊት ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ፓሪስ በሚደረገው ዝግጅት እልባት ያገኛል።
* Update
በኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለሥልጣን ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ ግርማ ለምዝገባው የሚያስፈልገውን መስፈርት ለማሟላት በገምጋሚ አካላት በኩል ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ምላሽና ማብራሪያ ቢቀርብም በዚህ ዓመት ለሚሰጠው ውሳኔ ሳይደርስ መቅረቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።