TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SEMERA

የአፋር እና የሶማሌ/ኢሳ ጎሳን/ ግጭት ለማስቆም ይረዳል የተባለ እና መፍትሄውንም ይጠቁማል የተባለ መጽሐፍ በሰመራ ከተማ ተመርቋል፡፡ መጽሐፉ በዋናነት የአፋርና የሶማሌ/ኢሳ ጎሳዎች/ በወንድማማችነትና በአብሮነት የኖሩበትን ታሪክ የሚዳስስ ሲሆን በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት የሚፈጥሩ የተለያዩ አካላት እንዳሉም ይጠቅሳል፡፡ ይሁንና ግጭት መፍጠር የሚፈልጉ አካላት የህዝብን አንድነት ለመሸርሸር አስበው በመሆኑ የአፋርና የኢሳ ጎሳዎች ለረጅም ዘመናት ያዳበሩትን አብሮነት ይዘው መቀጠል እንዳለባቸው ደራሲው አሎ ያዩ መሀመድ ገልጸዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEMERA

"Yes For Peace No for Terrorism!"

PHOTO: Abu Jaefar Dalol/TIKVAH FAMILY/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR #SEMERA

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር ፍልስፍና መጽሐፍ በአፋር እና ሐረሪ ክልሎች ደረጃ ነገ በሰመራና ሐረር ከተሞች እንደሚመረቅ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEMERA

የያንጉዲራሳ ብሄራዊ ፓርክን ለአፋር ክልል ለማስረከብ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለስልጣ አስታወቀ። በርክክቡ ዙሪያ ባለስልጣኑ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሰመራ ከተማ ውይይት ዛሬ አካሂዷል።

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEMERA

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የሰመራ ሎግያ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጤና ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ማህሙዳ ኢብራሂም እንደተናገሩት በከተማው የኮሌራ በሽታ የተከሰተው ከጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ነው።

እስካሁን ድረስም በበሽታው 26 ሰዎች ሲያዙ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል። በሰመራ ጤና ጣቢያ ጊዜያዊ የሕክምና ማዕከል ተዘጋጅቶ በበሽታው ለተያዙ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ኃላፊው አመልክተዋል።


(ENA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Semera

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን ለማክበር ሰመራ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቷ ከክልሉ አመራሮች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከፌዴራል ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚመክሩም ይጠበቃል።

በከተማው በሚኖራቸው ቆይታ በሰመራ ዩኒቨርስቲ ከሴት ተማሪዎችና አመራሮች ተሳትፎና ከስርዓተ-ጾታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ተመልክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታልን የሥራ እንቅስቃሴ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሰመራ ዩኒቨርስቲና በተመረጡ የከተማው አካባቢዎች ችግኝ ይተክላሉ ተብሎም ይጠበቃል። ፕሬዝዳንቷ ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክር ቤት ሰብሳቢ መሆናቸው ይታወቃል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Semera : በአፋር ክልል መዲና ሰመራ በአሁን ሰዓት በርካቶች የተገኙበት የውይይት መድረክ እየተካሄደ መሆኑን አፋር ማስ ሚዲያ ዘግቧል።

ውይይቱ #በወቅታዊ_ጉዳይ ዙሪያ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የአፋር ክልል ወጣቶች ፣ ሴቶች እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች ተካፋይ መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኦባሳንጆ ኮምቦልቻ ገብተዋል። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕከተኛ ኦሊሴንጎን አባሳንጆ ዛሬ ኮምቦልቻ ገብተዋል። በትላንትናው ዕለት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ ፤ የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን በመግለፅ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ…
#Afar, #Semera📍

ከትላንት በስቲያ ሰኞ በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ አፋር ክልል ሰመራ ገብተዋል።

ኦባሳንጆ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በሰመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሀንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ሰመራ መግባታቸውን ከአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia