TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ' ሳር ቤት አካባቢ በአውቶብስ ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ' እየተባለ በቲክቶክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

ፖሊስ ፤ የከተማው ሰላም መሆን እንቅልፍ የነሳቸው አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስጋት ላይ ለመጣል በቻሉት መጠን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።

እነዚህ አካላት ህዝቡ ደህንነት እንዳይሰማውና ከተማውም ሰላም አንደሌለው ለማሳየት ብዙ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው የፈጠራ ሀሰተኛ ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ይዘው መጥተዋል ሲል ገልጿል።

ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ የተደራጀ ቡድን እንዳለ በማስመሰል ሳር ቤት አካባቢ አውቶቡስ ላይ #ቦንብ_ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።

" ይህ ከእውነታ የራቀ በአዲስ አበባ ሰላም የለም ለማስባል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ ነው " ያለው ፖሊው ሁሉም የከተማው ነዋሪ ይህን ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።

ፖሊስ ፤ የከተማዋን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሌት ተቀን ህልማቸውን " ቲክ ቶክ /#TikTok " በተባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየገለፁ ናቸው ብሎ " በአዲስ አበባ ያለው ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ስራውን እያከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።

ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያዳብር እንደሚገባ አሳስቧል።

ሀሰተኛ መረጃን በሚያሰራጩ አካላት ላይም በህግ አግባብ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል።

@tikvahethiopia