TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባለስልጣኑ ተገደሉ።

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የሄበን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ በሪሶ ቡልዬ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በየተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

አቶ በሪሶ ትላንት ምሽት 1:30 ነው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው።

የሄበን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አቶ በሪሶ ለህዝቡ ሰላም እና እድገት ቀን እና ማታ ሲለፉ የነበሩ የህዝብ አገልጋይ መሆናቸውን አውስቶ በህልፈታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ፦

የተመድ (UN) ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊ ሚሼል ባሽሌት በትግራይ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎችን በተመለከተ ለሚደረገው ማጣራት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከስምምነት መደረሱን መግለፃቸውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል።

የኮሚሽኑ ቃለ አቀባይ ጆናታን ፈውለር ኃላፊዋ ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አማካኝነት የቀረበውን የ ’አብረን እናጣራ’ ጥሪ በበጎ መልኩ ተቀብለውታል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ቃል አቀባዩ አክለው ፥ “የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሁን ላይ ተፈጸመ የተባለውን ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል እቅድ ነድፈው ፣ ተልእኮቸቸውን በተቻለ ፍጥነት ለመፈጸም በመስራት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ሰቆጣ እና አካባቢው ምን ተፈጥሯል ?

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን "የሰቆጣ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከአሉባልታ እና ሽብርን ከሚነዙ ሀይሎች ራሱን በመጠበቅ ከጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን አካባቢውን ይጠብቅ" ሲል መግለጫ አውጥቷል።

የአስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ፥ "በመከላከያ፣ አማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የህወሓት ቡድን የፃግብጅ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን #የፃታ_ከተማ ላይ ዛሬ መጋቢት 9/2013 ዓ.ም ወረራ ፈጽመዋል" ሲል አስታውቋል።

ነገር ግን መግለጫው ስለፃታ ከተማ ወረራ/አሁን ላይ ስላለው ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አይገልፅም።

የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ "በብሄረሰብ አስተዳደሩና በአካባቢው ትክክለኛ ያልሆኑ እና የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሳይሸበር ራሱን ከአሉባልታ በመጠበቅና አሉባልታ የሚያሰራጭቱን በማጋለጥ ከጸጥታ ሀይሉ ጎን እንዲሰለፍ" ሲል በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

እስካሁን ድረስ በሰቆጣ እንዲሁም አካባቢዋ ምንም የተከሰተ የጸጥታ ችግር አለመኖሩ የተገለፀ ሲሆን ማህበረሰቡ መደበኛ የእለት ከእለት ተግባሩን እያከናወነ ከጸጥታ ኃይል ጋር በመሆን አካባቢውን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Alert😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 600 ደረሰ።

ዛሬም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,055 የላብራቶሪ ምርመራ 2,057 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 330 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 181,869 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,602 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 145,349 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

የዛሬ መጋቢት 9 ሁኔታ ፦

- 600 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች

- በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ 2,057 ይህ 26% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ ነው (#እስካሁን_ከፍተኛው) በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበን አናውቅም ፤

- 10 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 8 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦

1. ሲዳማ-45%
2. ድሬዳዋ-40%
3. አዲስ አበባ-26%
4. ኦሮሚያ- 31%
5. ደቡብ- 20%
6. አማራ- 20%
7. ቤንሻንጉል-29%
8. ሐረር- 23%

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ የሚረዳ "ምርጫዬ" የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ !

ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዲሁም ፓርቲዎች ሀሳባቸውን ለህዝቡ እንዲሸጡ የሚያስችል ምርጫዬ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያና ድረ ገጽ ማዘጋጀቱን እውነት ኮሚኒኬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

በአሁኑ ወቅት መራጮች ስለሚመርጡት ፓርቲ እና ተመራጭ የመረጃ ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ይህንን ፍላጎት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ መሸፈን ይቻል ዘንድ ይህ መተግበሪያና ድረ-ገጽ መዘጋጀቱ ነው ያስታወቁት።

በተለይ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳዎችን ለማድረግ ቴክኖሎጂውን እንደ ትልቅ አቅም መጠቀም እንደሚገባ የጠቀሱት አዘጋጆቹ ሁሉንም ፓርቲ ያለምንም ክፍያ በእኩል ለማሳተፍ የሚያስችል መድረክ መመቻቸቱንም ጠቁመዋል።

በምርጫ መተግበሪያው/ ድረ ገጹ ላይ የፓርቲዎች መግለጫ፣የሲቪክ ማህበራት እና የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድ መረጃ፣ ለፓርቲዎች ድጋፍ የሚደረግበት የእርዳታ ወይም የልገሳ ፎርም፤ ሰነዶች እና ተቀሳቃሽ ምስሎች ማጋሪያ፣ ዜና፣ ወደ ማህበራዊ ገጽ ማጋሪያ እንዲሁም ኩነቶችን ማስተዋወቂያ በውስጡ አካቷል።

እውነት ኮሚኒኬሽን ኃ/የ/የግ/ማኅበር በወጣቶች የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን ይህንን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን፤ በተለይ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን አስመልክቶ በሙያቸው በበጎ ፈቃደኝነት ሥራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።

ወደፊት ትልልቅ ለውጥ የሚፈጥሩ የቴከኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ገቢያው ለማምጣት በሂደት ላይ እንደሚገኙ ገልጸውልናል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ትላንት ምሽት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ በትግራይ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተጨማሪ የ52 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቀዋል።

አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ከተፈጠረ አንስቶ ያደረገችው ድጋፍ 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

ሚኒስትሩ አሁንም ቢሆን አሜሪካ በትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያሳስባት ገልፀዋል።

በስቴት ዲፐርትመንት በኩልን በወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ ተደራሽነት በማሳደግ የሰራቸውን ስራዎች አሜሪካ እውቅና እንደምትሰጥ ገልፃለች።

በመግለጫው ላይ ያለ ፖለቲካዊ መፍትሄ በትግራይ የሰብዓዊ ሁኔታው እየተባባሰ ሊቀጥል እንደሚችል ይገልፃል ፤ ግጭት ቆሞ በአስቸኳይ የኤርትራ ወታደሮች እና የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ያሰፈራቸውን የአማራ ክልል ኃይሎች እንዲነሱ ማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብሏል።

ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ግፎች በኢትዮጵያ መከላከያ ውስጥም ሆነ በህወሓት፣ በኤርትራ ኃይል ወይም በአማራ ክልል ኃይል ተጠያቂ አካል መኖር አለበት ይላል የስቴት ዲፓርትመት መግለጫ።

www.state.gov

ብሊንከን ከዚህ ቀደምም ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የአማራ ኃይል ይውጣ ሲሉ ማናገራቸው እና ፥ የአማራ ክልል መንግስትም ትግራይ ውስጥ እንደሌለ እና የአማራ ኃይል አሁን ያለበት ቦታ "በታሪክም የትግራይ እንዳልሆነ" ፤ የአማራ ኃይል ትግራይ ውስጥ አለ እየተባለ የሚገለፀውም ስህተት እንደሆነ የሚገልፅ ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በዚህ ጉዳይ ሉአላዊነትን የሚጋፋ ፣ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልጋ የመግባትና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል መግለጫ እንደሰጠበት ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ትላንት ምሽት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ በትግራይ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተጨማሪ የ52 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቀዋል። አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ከተፈጠረ አንስቶ ያደረገችው ድጋፍ 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ሚኒስትሩ አሁንም ቢሆን አሜሪካ በትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያሳስባት ገልፀዋል። በስቴት ዲፐርትመንት…
#Tigray

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ፍፁም አረጋ የአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ በኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል ተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ በመወሰናቸው ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እኤአ ከ1903 ጀምሮ የዘለቀ ነው ብለዋል።

አሁኑ አሜሪካ ያደረገችው ድጋፍ ሌሎችም የልማት አጋሮች ተመሳሳይ የሆነ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማበረታታት ተምሳሌት ይሆናል ሲሉ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው አስፍረዋል።

@tikvahethiopia
በርበሬና ሽሮ ውስጥ የከለር ኬሚካል ፉርሽካና ሰጋቱራ ቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ግለሰብ ተያዘ !

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ባእድ ነገሮችን ከምግብ እህል ጋር በመቀላቀል ለገበያ ያቀርብ የነበረ ነጋዴ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።

የጤና ቢሮው ምክትል የቢሮ ሀላፊ እና የጤና እና ጤና ነክ አገ/ግ/ጥ/ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ እንደገለጹት በሀይቅ ዳር ክ/ከተማ አሮጌ ገበያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ወፍጮ ቤት በርበሬ ሽሮ እና እርድ በማለት የተለያዩ እንደሰጋቱራና ጥራጊ ያሉ ነገሮችን በመፍጨት እና የተለያዩ ከለር ያላቸው ኬሚካሎችን በማደባለቅ ለገበያ ሲያቀርብ እንደነበርና አሁንም ከ200 ኩንታል በላይ ለገበያ የተዘጋጀ በቁጥጥር ስር መዋሉንገልጸዋል።

ቢሮው ተጠርጣሪው በፍጥነት ለህግ ቀርቦ ተገቢውን የሆነ ቅጣት እንደሚያገኝ አሳውቋል።

ለገበያ የተዘጋጀው የእህል አይነት ላይ በተደረገው ምርመራ ባእድ ነገር የተቀላቀለበት መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የሚጨመረው የከለር ኬሚካል በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰውን የጉዳት መጠን ለማጣራት የላቦራቶሪ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

ህብረተሰቡ እንዲህ ባለጉዳይ የተለየ ጥርጣሬ ሲያጋጥመው ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልጸው ሸማቹም ቢቻል በቤት ውስጥ አዘጋጅቶ እንዲጠቀም አልያም የታወቁ እና ህጋዊ ከሆኑ ተቋማት እንዲገበያይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አሳስቧል።

Via Tariku Dubale
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ክትባት በኢትዮጵያ ፦

• እስከ ትላንት ከ1,400 በላይ ሰዎች ክትባት ወስደዋል
• 35 ያህል ሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት ተደርጓል

በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት የፍቃዱን የአፈፃፀም መመሪያ መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የክትባቱ ደህንነት ለመከታተል እና በሚፈለገው ፍጥነት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

እስከትናንት ድረስ ከ1,400 በላይ ሰዎች ክትባት የወሰዱ ሲሆን 35 ያህል ሰዎች ላይ ነው የሚጠበቅ የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት የተደረገው ተብሏል።

ክትባቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያግዝ በመሆኑ በጎንዮሽ ጉዳቱ መደናገጥ እንደማያስፈልግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መግለፁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኢትዮጵየ መንግስት ከህወሓት ቡድን ጋር ይተባበራሉ ላላቸው አካላት #የመጨረሻ ማሳሰቢያ ዛሬ ሰጠ።

ከመግለጫው ላይ የተወሰደ፦

"...በወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩ እና በዚህም መናሻ የፍርድ ቤት መያዣ ከወጣባቸው ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካ አመራሮች በስተቀር ሌሎች ዜጎች ያለ ስጋት ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደቀያቸው እና መኖሪያቸው በመመለስ ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ያቀርባል። በዚህ መንገድ ከአጥፊው ቡድን ተለይተው ወደሰላማዊ ኑሯቸው የሚመለሱ የክልሉ ተወላጆች ዜጎች፣ የትኛውም የህግ ተጠያቂነት ሳይኖርባቸው ፣ ከአጥፊ ተግባራት ተቆጥበው ወደ ስራቸው እና ኑሯቸው በሰላም መሰማራት ይችላሉ፤ እነዚህን ዜጎች በመልካም ሁኔታ ለመቀበል እንዲተባበሩ እና የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ለየሚመለከታቸው የፀጥታ፣ የአስዳደር እና ህግ አስከባሪ ተቋማት አስፈላጊው መመሪያ ተሰጥቷቸዋል" - የጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵየ መንግስት ከህወሓት ቡድን ጋር ይተባበራሉ ላላቸው አካላት #የመጨረሻ ማሳሰቢያ ዛሬ ሰጠ። ከመግለጫው ላይ የተወሰደ፦ "...በወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩ እና በዚህም መናሻ የፍርድ ቤት መያዣ ከወጣባቸው ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካ አመራሮች በስተቀር ሌሎች ዜጎች ያለ ስጋት ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በአንድ ሳምንት…
መንግስት ላልተያዙ የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ ፦

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ያልተያዙ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮች በሰላም እጃቸውን ለህግ አስከባሪ ተቋማት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

ከዛሬው መግለጫ የተወሰደ ፦

"...የፍ/ቤት መያዣ የወጣባቸው ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች በሰላም እጃቸውን ለህግ አስከባሪ ተቋማት እንዲሰጡ መንግስት ጥሪ ያቀርባል።

እነዚህ አመራሮች እስከዛሬ ከደረሰው ሀገራዊ ጥፋት እና ጉዳት በመማር ለፍትህ ራሳቸውን በማቅረብ ፣ ተጨማሪ ሀገራዊ ኪሳራ እንዳይደርስ እና በከንቱ የዜጎች ደም እንዳይፈስ የበኩላቸውን በጎ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ መንግስት ጥሪ ያቀርባል።

ይሄንን የሚያደርጉ ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና የፖለቲካዊ አመራሮች ራሳቸውን ከከፋ ቅጣት ፤ ወገናቸውን ከመጎሳቀል ይታደጉታል።

ይሄ የመጨረሻ ጥሪ ተጠቅመው ራሳቸውን ለፍትህ በማያቀርቡ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ ህግ በሚፈቅደው ሁሉም ዓይነት መንገድ ፣ ህግ ለማስከበር ሲባል አስፈላጊው ሁሉ የሚፈፀም መሆኑን ቀድመን እንገልፃለን።" - የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

* ሙሉ የመግለጫውን ሃሳብ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የትግራይ የተፈናቃዮች ሁኔታ ፦

• "እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች በኃይል ተፈናቅለዋል። የዞኑ ነዋሪዎች በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና አንዳንድ ሊህቃን በሚፈፅሙት ተግባር ነው እየተፈናቀሉ የሚገኙት" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን

• "750 ሺ የትግራይ ተወላጅ ተፈናቀለ የተባለው ነጭ ውሸት ነው፤ የዚህን ያህል የትግራይ ተወላጅ ቦታው ላይ አይኖርም፥ የአማራ ተወላጆች ናቸው በብዛት የሚኖሩት፤ ወልቃይት እና ራያ አካባቢን በምዕራብ ትግራይ ስም መጥራት ተገቢና ወቅታዊ አይደለም፤ ጊዜው ያለፈበት ነው" - የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን

https://telegra.ph/Tigray-03-19