TIKVAH-ETHIOPIA
ባለስልጣኑ ተገደሉ። በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የሄበን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ በሪሶ ቡልዬ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በየተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። አቶ በሪሶ ትላንት ምሽት 1:30 ነው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው። የሄበን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አቶ በሪሶ ለህዝቡ ሰላም እና እድገት ቀን እና ማታ ሲለፉ የነበሩ የህዝብ አገልጋይ…
"...ገዳዮችን ለመያዝ የዞኑ ፖሊስ መርማሪ ቡድን አዘጋጅቶ ወደ ስራ አሰማርቷል" - አቶ አበራ ቡኖ (የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ)
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ባልታወቁ ታጣቂዎች የተገደሉት የሔባን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የቀብር ሥነ-ስርዓት ዛሬ መፈፀሙ ተገለፀ።
የሔባን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ በሪሶ ቡሊዬ ባለፈዉ ረቡዕ ምሽት ነው በታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተመተው የተገደሉት።
የ3 ልጆች አባት የሆኑት በሪሶ ቡሊዬ በሻሸመኔ በስብሰባ ላይ ውለው በአርሲ ነጌሌ ከተማ 01 ቀበሌ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ለመግባት ከተሸከርካሪ ሲወርዱ ነው በሶስት ጥይት ተመትተው የተገደሉት።
የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቡኖ፥ "ገዳዮችን ለመያዝ የዞኑ ፖሊስ መርማሪ ቡድን አዘጋጅቶ ወደ ስራ አሰማርቷል" ብለዋል።
ለ9 ወራት ብቻ ወረዳውን ያስተዳደሩት የአቶ በሪሶ ቡሊዬ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰቦቻቸውና የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ተፈፅሞአል።
ባለፈው ቅዳሜ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከቀድሞ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በወረዳው የተሰራውን የበጋ ስንዴ ምርት ሲጎበኙ አቶ በሪሶን አበረታተውት እንደነበር የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ አሳውቋል። (ዶቼ ቨለ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የኮቪድ-19 ክትባት በኢትዮጵያ ፦ • እስከ ትላንት ከ1,400 በላይ ሰዎች ክትባት ወስደዋል • 35 ያህል ሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት ተደርጓል በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት የፍቃዱን የአፈፃፀም መመሪያ መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። የክትባቱ ደህንነት ለመከታተል እና በሚፈለገው ፍጥነት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ…
ቀላል የጎንዮሽ ጉዳት የተባሉት የትኞቹ ናቸው ?
ኢትዮጵያ ውስጥ እስከትላንት የኮቪድ - 19 ክትባት ከወሰዱ ከ1,400 በላይ ሰዎች 35 ሰዎች ላይ ቀላል የጐንዬሽ ጉዳት ሪፖርት ተደርጓል።
ይህ ማለት ልክ እንደሌሌች ክትባቶች ሁሉ የእራስ ምታት፣ ድካም እና የክትባት መስጫ አካል ላይ መቅላት ሲሆኑ እነዚህ ደግሞ በጥናቱም ወቅት የታዩ እና የሚጠበቅ ቀላል የጐንዮሽ ጉዳት ነው።
እስካሁን በክትባቱ ምክንያት የ "ከፋ ጐንዬሽ ጉዳት" ሪፖርት አልተደረገም ፤ በሌሎች ሀገራት አጋጥሟል የተባለው የደም መርጋት ችግርም አላጋጠመም።
ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተላከልን መልዕክት።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOt

#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ
የዛሬ የኮቪድ19 ሪፖርት ምን ይመስላል ?
- 624 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች
- 24% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ
- 16 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች
በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 6 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦
1. ሲዳማ-48%
3. ድሬዳዋ-22%
3. አዲስ አበባ-25%
4. ኦሮሚያ- 25%
5. ደቡብ- 21%
6. አማራ- 24%
በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟል።
በፍጥነት የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካላደረግን እና ሁላችንም በሚገባ ካልተጠነቀቅን የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ከእነዚህ ቁጥሮች በላይ ምስክር የለም::
ሁላችንም የበሽታውን ስርጭት በመግታት የራሳችን እና የምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ሕይወት እናድን።
ያዕቆብ ሰማን
ጤና ሚኒስቴር
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
@tikvahethiopia

የዓለም አገራት ህዝቦች የደስተኝነት ደረጃ ፤ የኢትዮጵያ ስንተኛ ?
በተመድ በሚደገፈው በዓመታዊ የዓለም አገራት ሕዝቦችን ደስተኝነት በሚለካው ጥናት ፤ ከ149 አገራት ሕዝቦችን የደስተኝነት ደረጃ #ኢትዮጵያ 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ከዓለም አገራት በተለያዩ መለኪያዎች ደስተኛ ሕዝብ ያላት ቀዳሚዋ አገር ፊንላንድ ስትሆን ዴንማርክ ሁለተኛ ፣ ስዊትዘርላንድ ሦስተኛ ፣ አይስላንድ አራተኛ እና ኔዘርላንድስ አምስተኛ በመሆን ተከትለዋታል።
ከአንደኛ እስከ አስረኛ ደረጃ ከያዙት አገራት ውስጥ አውሮፓዊ አገር ያልሆነችው ኒውዚላንድ ብቻ ናት።
ይህ ውጤት የተገኘው ጋሉፕ በተባለው የመረጃ ተንታኝ አማካይነት ደስተኛነታቸውን ለማወቅ ከ149 የዓለም አገራት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ነው።
ይህ የሰዎች የደስተኝነት ሁኔታ የተለካው የሚያገኙት ማኅበራዊ ድጋፍ፣ ግለሰባዊ ነጻነት፣ ጠቅላላ አገራዊ ምርት (ጂዲፒ) እና በአገራቱ ውስጥ ባለው የሙስና መጠንን ጨምሮ ሌሎችንም መመዘኛዎች በመመልከት ነው።
በዚህ ዓመቱ ጥናት ከዓለም አገራት ውስጥ ደስተኛ ያልሆኑ ሕዝቦች ይኖሩባቸዋል የተባሉት አፍጋኒስታን፣ ሌሶቶ፣ ሩዋንዳ እና ዚምባብዌ ናቸው።
የጥናቱ አዘጋጆች እንዳሉት ዓለምን ባጠቃት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ አንድ ሦስተኛ በሚሆኑ አገራት ውስጥ "አሉታዊ የሆኑ ስሜቶች በተደጋጋሚ የመከሰታቸው ሁኔታ ከፍተኛ ነበር" ብለዋል።
የእስያ አገራት ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ደረጃ መሻሻልን ሲያሳዩ ቻይና ቀደም ባለው ዓመት ከነበራት የ94ኛ ደረጃ ወደ 84ኛ ከፍ ብላለች።
Via BBC

#AstraZeneca አጫጭር መረጃዎች ፦
- WHO የክትባት ደህንነት አማካሪ ኮሚቴ የአስታራዜኔካ ክትባት ተጠቂነትን ለመከላከል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞትን ይቀንሳል ብለዋል። አማካሪ ኮሚቴው እንዳለው ተገኘው መረጃ የደም መርጋት መጨመርን አያሳይም ብሏል፡፡
- የአውሮፓ የመድሃት ኤጀንስ ክትባቱ እንደተባለው የጎላ የደም ማርጋት ችግር እንደሌለበት እና ክትባቱ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ ውጤታማነት እንደሆነ አሳውቋል።
- ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እና ጀርመን ያቋረጡትን የአስትራዜኔካ ክትባት መስጠት እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።
- የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትላንት አርብ የአስትራዜኔካ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ተከትበዋል።
- የ55 ዓመቱ የፈረንሳይ ጠ/ሚ ዣን ካስቴክስ የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ትላንት ተከትበዋል፤ ፈረንሳይ 55 እና ከዛ በላይ እድሜ ላላቸው ዜጎቿ ክትባቱን መስጠት እንደምትቀጥልም ተገልጿል።
- Africa CDC የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባትን መስጠት እንዲቀጥሉ ብሏል።
Source : France 24, Sky News , Al Ain, Africa CDC, WHO
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

“ነእፓ ለጣምራ መንግስት ምስረታ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር እየሰራ አይደለም”- ነእፓ
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር የጣምራ መንግስት ለመመስረት ምንም አይነት ውይይት ወይም ምንም ስምምነት አለማድረጉን አስታውቋል።
በትላንትናው እለት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነእፓ ከእናት ፓርቲ ጋር የጣምራ መንግስት ለመመስረት እየሰራ እንደሆነ የሚገልፅ ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ ነው ፓርቲው ይህንን ያስታወቀው።
“የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነእፓ የጣምራ መንግስት ለመመስረት ከእናት ፓርቲ ጋር እየሰራ እንደሆነ ያሰራጨውን የተሳሳተ ዜና እንዲያስተካክል እንጠይቃለን” ሲል ጠይቋል።
ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሚዲያ ተቋማት ምርጫ ሆነ ሌሎች ጉዳዮችን ከመዘገባቸው በፊት የመረጃውን ትክክለኝነት በማረጋገጥ ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ እና የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
የምርጫው ውጤት በኢትዮጵያ ውስጥ የጣምራ መንግስት የሚቋቋምበትን ሁኔታ ከፈጠረ የሚመሰረተው የጣምራ መንግስት ፓርቲዎች በሚያገኙት የህዝብ ድምጽ መሰረት በፓርቲዎች መካከል በሚደረግ ድርድር የሚፈጸም እንደሚሆን ፓርቲው ገልጿል፡፡

የእናት ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ታሰሩ።
በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ጋሞ ዞን፣ከምባ ወረዳ፣ ከምባ ምርጫ ክልል የእናት ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጬ ተወዳዳሪ የሆኑት መምህር በድሉ አለባቸው "ግርግር አስነስተዋል" በሚል ምክንያት ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት መታሰራቸውን ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
ፓርቲው ፥ "ጉዳዩ በቀላሉ ይፈታል የሚል ግምት የነበረን ቢሆንም እስከአሁን ቃላቸውን ተቀብለን እንላቀቸዋለን በሚል ሽንገላ የከምባ ከተማ ፖሊስ እስካሁን ድረስ አስሮ ይዟቸዋል" ብሏል በመግለጫው።
"በዚህ ጊዜ የሚደረግ እንዲህ ያለ መሠረተ ቢስ ክስ የእጩዎቻችንን መልካም ስምና ዝና ሆን ተብሎ ለማጉድፍ፣ እና ለሌሎች እጩዎችም የማስፈራሪያ መልዕክት ለማስተላለፍ ያሰበ እንጂ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዳልሆነ እንረዳለን" ሲል ገልጿል።
እናት ፓርቲ ፥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ገልጾ እስሩ ፖለቲካዊ እንድምታ ያለው እሥር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል አሳስቧል።

አጣዬ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጀምሮ የፀጥታ መደፍረስ ተከስቷል።
ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን በዝርዝር ማወቅ አልተቻለም።
የቲክቫህ አጣዬ አባላት ከትላንት ምሽት ጀምሮ አካባቢው በተኩስ እሩምታ ሲናጥ እንደነበር ገልፀው የሚመለከተው አካል እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬም በአካባቢው ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ሲሆን ወደ ደሴ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እና መንገደኞች መንገድ ላይ ለመቆም ተገደዋል።
በአካባቢው ለፀጥታው መደፍረስ ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡ ሲሆን በጣዬ የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መረጃ አቀናጅተን ወደበኃላ የምናቀርብ ይሆናል።
አሁን ላይ ህዝቡ በሰላም መደፍረስ ከፍተኛ ችግር ላይ ሰለወደቀ አካባቢውን የማረጋጋት ስራ እንዲሰራ አባላቶቻችን ጠየቀዋል።
ከላይ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት አጣዬ አካባቢ በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚሄዱ መኪናዎች ደብረ ሲና ላይ መቆማቸውን የሚያሳይ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ የታጠቁ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ በፅፅቃ ከተማ አከባቢ 8 አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።
"አስር (10) ማንነታቸው አልታወቀም" የተባሉና ትጥቅ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎችን ነው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት የገለፀው
ግለሠቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑን ተገልጿል።
@tikvahethiopia
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ በፅፅቃ ከተማ አከባቢ 8 አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።
"አስር (10) ማንነታቸው አልታወቀም" የተባሉና ትጥቅ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎችን ነው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት የገለፀው
ግለሠቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑን ተገልጿል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በአጣዬ እና አካባቢው አለመረጋጋት የሰው ህይወት አልፏል።
ከትላንት አርብ ምሽት ጀምሮ በተኩስ እሩምታ ስትናጥ በነበረው አጣዬ የሰዎች ህይወት አልፏል።
ትላንት አርብ ምሽት በነበረው ተኩስ አንድ ሰው ሲሞት 2 ሰው መቁሰሉ ተሰምቷል።
የኤፍራታና ግድም ወረዳ የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አልታየ እስከ ረፋድ ድረስ የ4 ሰዎችን ሞት መመልከታቸውን ለቢቢሲ አሳውቀዋል።
የተከፈተውን ተኩስ ተከትሎ የአጣዬ ከተማ የ01 ቀበሌ "ሙሉ በሙሉ በታጣቂዎች መያዙን" ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ከለሊት ጀምሮ ደግሞ በማጀቴ የታጠቁ ኃይሎች ተኩስ ከፍተው ሰዎች መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል። የተጎጂዎች ቁጥር በውል አይታወቅም።
አሁንም በአካባቢው ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ሲሆን ተጨማሪ የፌዴራል/ክልል ኃይል ወደ አካባቢው እንዲገባ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲያረጋግጥ እየተጠየቀ ነው።
የባንኮች እና የሰዎች ንብረት ተዘርፏል።
በሰላም መደፍረስ ምክንያት ተሸከርካሪዎች አሁንም በመንገድ ላይ እንደቆሙ ይገኛሉ። መንገደኞችም በሁሉም አቅጣጫ እየተንገላቱ ነው።
ለአካባቢው የፀጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት መነሻ አሁንም በተለያዩ ወገኖች የተለያዩ ምክንያቶች እየቀረቡ ነው።
የክልሉ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።
ከዚህ ቀደምም በተለያየ ጊዜ በአጣዬ እና አካባቢው በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የሰዎች ህይወት እንዳለፈ/ንብረት እንደወደመ የሚዘነጋ አይደለም።
PHOTO : MUSI (Tikvah-Family Dbersina)

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ.pdf
95.5 KB
#UPDATE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛዉን አጠቃላይ ምርጫ ለመታዘብ ለሲቪል ማህበራት እውቅና የመስጠት ስራውን እንዳጠናቀቀ ዛሬ አሳውቋል።
በምርጫው 134,109 የአገር ውስጥ ታዛቢዎች ይሰማራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- በሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሰሩ 8 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረቡ 61,851 ሴት ታዛቢዎች (46%) ሲሆኑ፣
- በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ስር የታቀፉ 7 ማህበራትን ያካተተ 244 ታዛቢዎች እና
- በሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ሂደትን ለመታዘብ በተመረጠ 1 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የቀረቡ 100 ታዛቢዎች እና በስሩ 37 ያህል ሲቪል ማህበራትን ያቀፈ የሲቪል ማህበረሰብ ኔትወርክ ይገኙበታል።

በደቡብ ጎንደር ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን እና የመገበያያ ገንዘቦችን የያዙ ግለሰቦች በተደረገ የፖሊስ ፍተሻ አንዳቤት ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል።
ግለሠቦቹ ከጎንደር ጭነው ሲመጡ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አንዳቤት ከተማ ላይ በተደረገ ፍተሻ ፦
- ከ1 ሽህ 500 በላይ ጥይቶች፣
- 3 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ፣
- 1 ካዝናና 37 ሽህ700 ብር በቁጥጥር ስር እንደዋለ ፖሊስ አሳውቋል።
መሳሪያውን ሲያዘዋውሩ የተያዙት 3 ግለሰቦች እና የመኪና አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።
ግለሰቦቹ የሃሰት መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል ተብሏል።
የአንዳቤት ወረዳ የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሲሳይ እንየው ግለሰቦቹ የያዙት ህገ ወጥ ጥይት #ከመንግስት_ካዝና ጭምር የወጡ እንደሆነ መረጃው የሚያመላክት መሆኑን በመጥቀስ ግለሰቦቹም ህጋዊ ነን በማለት ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል ብለዋል፡፡
መንግስት እንደዚህ አይነት ተግባር በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ የሆነ ርምጃ መውሰድ እንዳለበት የተጠቆመ ሲሆን
የሚመለከተው አካል የፍተሻና የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል።
አሽከርካሪዎች የሚጭኑትን እቃ በደንብ በመፈተሸ ከተጠያቂነትና ከህገ ወጥ ስራዎች ራሳቸውን መቆጠብ አለባቸው ተብሏል።
መረጃውን ከአንዳቤት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው ያገኘነው።

በአጣዬ እና አካባቢው አለመረጋጋት የሰው ህይወት አልፏል። ከትላንት አርብ ምሽት ጀምሮ በተኩስ እሩምታ ስትናጥ በነበረው አጣዬ የሰዎች ህይወት አልፏል። ትላንት አርብ ምሽት በነበረው ተኩስ አንድ ሰው ሲሞት 2 ሰው መቁሰሉ ተሰምቷል። የኤፍራታና ግድም ወረዳ የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አልታየ እስከ ረፋድ ድረስ የ4 ሰዎችን ሞት መመልከታቸውን ለቢቢሲ…
አጣዬና አካባቢው ፦
አቶ አበራ መኮንን(የሰሜን ሽዋ ዞን የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ) ለአብመድ በሰጡት መረጃ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣየና አካባቢው እንዲሁም ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ አካባቢዎች ተኩስ መከፈቱን ተናግረዋል፡፡
አቶ አበራ ፥ አጣየ አካባቢ 1 ሰው በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል በሚል ግጭት መከሰቱን ተናግረዋል።
እንዴት እና በማን በተተኮሰ ጥይት የሰው ህይወት እንዳለፈ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም/በዘገባው ላይ አልተካተተም።
ነገር ግን የሰው ህይወት ካለፈ በኃላ ጉዳዩን አመራሩ በማወያየት በሽምግልና የተፈታ ቢሆንም ድንገት ማታ ላይ ተኩስ መከፈቱን አሳውቀዋል።
ተኩሱ ከተጀመረ በኋላ የጸጥታ መዋቅሩን በማንቀሳቀስ የማረጋጋት ሥራ ሲሠራ ከቆየ በኋላ የፌደራል ፖሊስ እንዲገባ መደረጉን ተናገረዋል።
ችግሩ ከአቅም በላይ በመሆኑ እና ሊቆጣጠር የሚችል በቂ የጸጥታ ኀይል ባለመሠማራቱ ወደ ሌሎች አካባቢ ሰፍቶ ተኩሱ እስካሁን መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡
ተኩሱ በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ እንደነበርም ነው የገለጹት፡፡ አሁን ላይ ተኩሱ በመጠኑም ቢሆን ጋብ በማለቱ የማረጋጋትና ሌሎች ሥራዎች እየተከናወነ እንደሆነ ነው ኃላፊው ያብራሩት፡፡
ጉዳዩን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል ጸጥታ ኃይል እንዲገባ እየተጠየቀ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው አንዳንድ ቦታዎች ለእንቅስቃሴ የተዘጉ እና የተያዙ በመሆኑ ባለው ኃይልም ቢሆን ችግሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ኃላፊው በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ወደፊት ተጣርቶ ለሕዝብ እንደሚገለጽ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

#Alert_Sidama😷
በሲዳማ ክልል በኮቪድ-19 ምክንያት ሁሉም "አጋዥ አርትፍሻል መተንፈሻ ማሽን" ተይዞ አልቋል። ዛሬ ጽኑ ህክምና የገቡ ሰዎች ቁጥር 10 ደርሷል።
በቀጣይ ቀናት ይህ ውጤት ካልተቀየረ ቀሪ ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ማሽኑን በወረፋ እንዲጠቀሙ የግድ ይሆናል።
በሌላ በኩል በከባድ ህመም ውስጥ ሆኖነው ኦክስጂን እርዳታ ላይ ያሉ ሰዎች 55 ደርሰዋል።
ከቀን ወደ ቀን ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ እንዲሁም የICU ክብካቤ የምፈልግ የኮቪድ-19 ተጠቂ ቁጥር እየጨመረ ነው።
ሰው ከታመመ በኋላ በህክምና ተረድቶ የመትረፍ እድሉም እየጠበበ እየሄደ ነው።
ኦክስጅንና አርትፍሻል መተንፈሻ ማሽን ካለቀ ደግሞ በከባድ ኮቪድ ህመም ያሉትን ማከምም ሆነ ማትረፍ አዳጋች ነው።
ሁሉም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር አሁም ጥሪ እየቀረበ ነው።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ/ም

#AlertEthiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 29 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,227 የላብራቶሪ ምርመራ 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 586 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 185,641 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,647 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 146,273 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 576 ሰዎች በፅኑ የታመሙ ሲሆን በሀገራችን የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ከባለፉት ቀናት መቀነስ አሳይቷል።
#Purpose #Tikvah