TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,895 የላብራቶሪ ምርመራ 1,413 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል። ትላንት 1,669 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 175,467 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,550 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 143,710 ሰዎች አገግመዋል። በአሁን ሰዓት…
የዛሬ መጋቢት 5 ሁኔታ ፦

24% national positivity rate.The higest so far!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአራት ሰው አንድ ሰው በኮቪድ ተይዞዋል ወይም ኮቪድ ሊኖርበት ይችላል እንደማለት ነው።

ከ20% በላይ የበሽታው ስርጭት የሚታይባቸው ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ፦
1. ሲዳማ-39%
2. ኦሮሚያ-38%
3. ድሬዳዋ-25%
4. ሐረር-25%
5. አዲስ አበባ-24%

እነዚህ ቁጥሮች ምን ማለት እንደሆኑ አለመገንዘብ በእራስ እና በሀገር ላይ ሞት እንደማወጅ ይቆጠራል።

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

#SPHMMC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
65 ሺህ ብር ወድቆ ያገኘው ወጣት በታማኝነት ለባለቤቱ መለሰ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ የአይሰጋ ቀበሌ ነዋሪና የጎሚስታ ስራ የሚሰራው ወጣት #ያዩ_ሁነኛው መህሩም ተራራ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ 65 ሺህ ጥሬ ብር ያገኘ ቢሆንም ገንዘቡ ለጠፋበት ለአቶ ሰለሞን ጫቅሌ ምንም ሳይቀንስ 65 ሺህ ብሩን በታማኝነት እንደመለሰለት የቋራ ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

አቶ ሰለሞን ፥ ገንዘቡን ላገኘለት ወጣት 10 ሺህ ብር ቢሰጠውም ወጣቱ ገንዘቡ አልቀበልም በሚል ሙሉ ታማኝነቱ እና ደግ ስራውን ከፈጣሪው ማግኘት በመፈለጉ ሊቀበለው አለመቻሉን ገልጿል።

ወጣቱ ሰርተን ከምናገኘው ገንዘብ ውጭ የሰው ገንዘብ መጥቶ ሊጠቅመን ይልቅና የራሳችንንም ይዞብን ስለሚጠፋ ሁላችንም የሰው ገንዘብ የሰው ከመሆኑ በዘለለ ለኛ ስለማይጠቅም ሁላችንም ፈጣሪ ሰርተን የምናገኘውን በረከት ያደርግልን ዘንድ ጎን መዋል ይኖርብናል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ከሳምንታት በፊት #ጉሌድ_ኢብራሂም_ኡመር የተባለ በጅጅጋ ከተማ በባጃጅ ሹፍርና የተሰማራ ወጣት የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጣቸው እናት 300,000 ብር (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባጃጁ ላይ ረስተው ቢወርዱም የብሩ ባለቤት የሆኑትን እናት በመፈለግ የተቀመጡበት ቦታ ድረስ ሄዶ መልሶላቸው ነበር፤ በማህበራዊ ሚዲያም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለወጣት ጉሌድ ኢብራሂም ኡመር ምስጋና ሲያቀርቡ ነበር።

ለዚህ ተግባሩ የሶማሊ ክልል ፕሬዜደንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድም ምስጋና አቅርበውለት እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ሃሳብን ለመግለፅ መሳድብን ምን አመጣው ?

ባለፉት 2 ቀናት የቲክቫህ አስተያየት መስጫ እንዲከፈት ተደርጎ ብዙ ታዝበናል ፤ ይህ የሀገራችንን የማህበራዊ ሚዲያው ሁኔታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።

ስድብ፣ ጥላቻ፣ሰዎችን ለማሸማቀቅ አንገት ለማስደፋት መሞከር፣ያለማስረጃ፣ ያለምንጭ መናገር ተላምደነው አብረን መኖር ከጀመርን ሰነባብተናል።

ብዙ ሺዎች ሃሳባቸውን በአግባቡ የሚገልፁ ቢኖሩም የጥቂቶች ስድብ፣ጥላቻ ብዙዎችን ይመርዛል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሆነ በማንኛውም ቦታ ሃሳብን ለመግለፅ መሳደብ /ሰዎች ማሸማቀቀ፣ አንገት ማስደፋት አይጠበቅብንም። በጨዋ ቋንቋ ማስረዳት ከቻልን እሰየው ፣ የማንግባባት ከሆነ ደግሞ ሌላ ጊዜ ከስሜታዊነት ነፃ ስንሆን መነጋገሩ መልካም ነውም

ከኛ ተቃራኒ ሃሳብ ሲገጥመን ፥ ለምን በትህትና ማስረዳት አቃተን ? ወንድሜ ፣ እህቴ ይህ እንዲህ ነው፤ ሃሳብን /ሃሳብሽን አልደግፈውም በዚህ ምክንያት ... ፤ እስቲ እንዲገባኝ አስረዳኝ/አስረጂኝ ... እያልንም ማውራቱ እንዴት ከበደን ?

ጥላቻ፣ ተቃራኒ ሃሳብ ለማስተናገድ አለመፈለግ፣ በቡድን ማሰብ/መፍረድ ፣ ጅምላ ፍረጃ፣ ሰዎችን ማሸማቀቅ ፣ ተጎዳን የሚለው ላይ መሳለቅ ውሎ አድሮ ሀገርን አደጋ ላይ መጣሉ አይቀርም።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የጥላቻ ንግግርን በመቃወም ከክልል ክልል የዞርነው ውጤቱን ስላወቅን ነው።

ቲክቫህ መደበኛ ሚዲያ አይደለም ፤ እርስ በእርስ መረጃ ለመቀያየር ፣ ስለሀገር ጉዳይ የምንመክርበት፣ ለተቸገሩት የምንደርስበት ፕላት ፎርም ነው።

ጋዜጠኛው፣ሃኪሙ፣ነጋዴው፣ባለሃብቱ፣ ተቃዋሚው፣ ባለስልጣኑ ፣ ተማሪው፣ አስተማሪው የቲክቫህ አባል ነው።

ቲክቫህ ውስጥ ስድብ ፈፅሞ አይፈቀድም ፤ ተሳዳቢዎችን የመምከር ከፍ ሲል ከአባልነት የመቀነስ ስራ እንሰራለን።

@tikvahethiopia
#Gambella

ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በሰው እና በቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ።

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ፑኩሙ ቀበሌ ንፋስ ቀለቀቅሎ በጣለ ዝናብ በርካታ ቤቶችና ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ፡፡

የፑኩሙ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጆን ኡጁዋቶ እንዳሉት በቀን 04/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5 አካባቢ ንፋስ ቀላቀሎ በጣለው ዝናብ በቀበሌው ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

በደረሰው ጉዳትም 55 የቆርቆሮና 20 የሳር ቤቶች በድምሩ 75 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ትምህርት ቤትን ጨምሮ አራት የመንግስት ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁመው በ3 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ መድረሱን አመልክተዋል፡፡

በመሆኑም በደረሰው አደጋ መልሰው ለመቋቋም የወገንና የመንግስት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋትቤል ሙን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል፡፡

በአደጋው የደረሰ ተጨማሪ ጉዳት እንዳለ ለማጣራት እና እርዳታ ለማሰባሰብ ከተለያየ አካላት የተውጣጣ ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚላክ አስረድተዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ቦታው ላይ በመገኘት ምልከታ ማድረጋቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#አሪፍፔይ

አሪፍ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አክሲዮን ማህበር ለመመስረት የሚያስችለውን የመጀመሪያ ምስረታ ጉባኤ አካሂዷል።

አሪፍ ፔይ 31 የአክሲዮን አባላት ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው ባለአንድ ሺህ ብር የሆኑ 140 ሺህ አክሲዎኖች አሉት።

አክሲዮኑ በገንዘብ እና በአይነት 140 ሚሊዮን ብር ካፒታል እንዳለው ተገልጿል።

አሪፍ ፔይ ስራው ምንድነው ?

አርፊ ፔይ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ አርፍ ፔይ ATM /ኤቲ ኤም/ ካርድን በመጠቀም ክፍያን ለመፈፀም የውሃ፣ መብራት፣ ስልክ፣ ሬስቶራንት ውስጥ ክፍያ ለመፈፀም እና ሌሎች ክፍያዎችን ለመፈፀም ኤቲኤም ካርዶችን ለማንበብ የውጭ ሀገር ካርዶችን ተቀብሎ ክፍያ መፈፀም እና ሌሎች አገልግሎቶችን ይሰጣል ሲሉ አስረድተዋል።

የጥሬ ገንዘብ ግብይትን ወደ ኤሌክትሮኒስ የመቀየር ስራን በስፋት ሰራለሁ የሚለው አሪፍ ፔይ በአንድ ወር ውስጥ ወደ ስራ ለመግባት አቅዶ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

ምንጭ፦ አሪፍ ፔይ ፣ ኢቢኤስ
@tikvahethiopia
ከአንድ አመት በላይ ያለምንም ስራ የተቀመጡት ሃኪሞች ፦

በአማራ ክልል 450 በላይ (ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል) የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው ያለስራ የተቀመጡ ሃኪሞች/ዶክተሮች/ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና እየተዳረጉ ይገኛሉ።

ወደስራ መሰማራት ሳይችሉ ከቀሩ ሃኪሞች መካከል የቲክቫህ አባላት የሆኑም ይገኙበታል።

ሃኪሞቹ ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ያለስራ የተቀመጡ ሲሆን ለሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት አቤት ቢሉም የተሰጣቸው መልስ "በጀት የለንም" የሚል እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌሎች ክልሎች እንዳይሰሩም የቋንቋ ጉዳይ ፈተና እንደሆነባቸው ገልፀዋል።

የሃኪሞቹ ጥያቄ ዛሬም ድረስ ባይቋረጥም መፍትሄ አልተገኘም ፤ በዚህም ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና ተዳርገዋል።

ከነሱ አልፎም ቤተሰቦቻቸውን ለስነ ልቦና ጫና ዳርጓል።

በሀገራችን የህክምና ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ፣ ከታች ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለቀለም ትምህርት ብቻ ቦታ እየሰጡ የመጡ፤ ዩኒቨርሲቲ ከተገባ በኃላም ከባድ 7 ዓመታትን አልፈው ነው የሚመረቁት።

ሃኪሞቹ ለበርካታት አመታት ያህል በስንት ጥረት እና ትግል እዚህ ደርሰው ከፍተኛ የሃኪም እጠረት ባለበት ሀገር ስራ ላይ መሰማራት አለመቻላቸው እንደሚያሳዝናቸው ገልፀዋል።

የቲክቫህ አባላት እንዳሉት ከነሱ ብዙ ነገር ቤተሰቦቻቸው ቢጠብቁም እንኳን ለቤተሰቦቻቸው ሊሆኑ እራሳቸውን ችለው ከቤት መውጣት አልቻሉም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዶ/ር ገነነ ተፈራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የኢትዮጵያ ባዮዳይቨርሲቲ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ገነነ ተፈራ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

ኢንስቲትዩቱ በዶ/ር ገነነ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።

የዶ/ር ገነነ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ኮተቤ ቅድስት ኪደነምህረት ቤተክርስቲያን በ8:00 እንደሚፈፀም ተገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ እንዲያበረታቱ ተጠየቁ !

ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችቸውን የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ እንዲያበረታቱ ጠየቁ።

ዶ/ር ፋውቺ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ትራምፕ "በሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ዘንድ በጣም ታዋቂ ነው" በማለት የፕሬዝዳንቱ ቃል የበርካቶችን ሃሳብ እንደሚለውጥ ተናግረዋል።

ትራምፕ ወጥተው ለደጋፊዎቻቸው ክትባቱን እንዲወስዱ ቢነግሩ በርካቶች ሊከተቡ እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

"በጣም ታዋቂ ሰው ነው። እርሱ ወጥቶ ከተናገረ የማይከተቡበት ምክንያት አይታየኝም" ብለዋል።

ዶክተር ፋውቺ አክለው የትራምፕ አስተዳደር "አሁን ያለንን ክትባት እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ውጤታማ ሥራ ሰርቷል" ብለዋል።

አክለውም ፕሬዝዳንቱ በስልጣን ዘመናቸው በሰሩት ሥራ ክትባቱ ተገኝቶ አሁን ዜጎች አልከተብም ማለታቸው የሚቃረን መሆኑን ገልፀዋል።

"በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። ወጥቶ ቢናገር ነገሮችን መቀየር ይችላል" ብለዋል ዶ/ር ፋውቺ።

በቅርቡ በአሜሪካ የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመለከተው የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ ከሆኑ ወንዶች መካከል 49 በመቶዎቹ የኮሮናቫይረስ ክትባትን መውሰድ አይፈልጉም።

ትራምፕ ባለፈው ወር በሪፐብሊካኖች ጉባኤ ላይ ተገኝተው "ሁላችሁም ሂዱና ተከተቡ" ብለው ነበር።

ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት አስተያየት ሲሰጡ አልተደመጡም።

ትራምፕ ባለፈው ጥር ወር በግላቸው የኮሮናቫይረስ ክትባትን ወስደዋል።

አራት የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ ፣ ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ፣ ቢል ኪሊንተን፣ እና ጂሚ ካርተር ክትባቱን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ ቪዲዮ ላይ ታይተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12 ሰዎች ህይወት የቀጠፈው አደጋ ፦

በቀን 4/07/2013 ዓ/ም በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ቆማ ከተባለ አካባቢ ወደ እስቴ መካነ እየሱስ ከተማ ኮድ 3 አዲስ አበባ ታርጋ ቁጥር 57645 አይሱዙ መኪና ከሌሊቱ 9 ፡00 ሰአት ገደማ 51 ኩንታል ጤፍ እና #25_ሰዎችን ጭኖ ሲጎዝ የነበረ ሲሆን ልዩ ስሙ አጋጥየሾ ቀበሌ አተር አውድማ ከሚባል ጎጥ ላይ ተገልብጦ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከአቅም በላይ መጫን፣የትራፊክ ህግ አለማክበር፣በአቆራጭ ለመክበርና ትርፍ ለማግኘት መሞከር ብዙ ዋጋ እያስከፍለን ነው የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

መረጃው የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ ከ21 ሰዎች በላይ ህይወታቸው አለፈ።

በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በቤዛ ብዙሃን ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡሃች አካባቢ ዛሬ መጋቢት 6/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ከጎንደር ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ ዋሊያ ባስና ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ተነስቶ ወደ ወይን ውሃ ይጎዝ የነበረ ቅጥቅጥ አይሲዙ መኪና ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ21 ሰው በላይ ህይወቱ አልፏል፡፡

መረጃው የሞጣ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታክሲዎች አድማ በአዲስ አበባ ፦

(በአል-ዐይን - AlAIN)

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተሳፋሪዎች ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ገጥሟቸዋል።

ተሳፋሪዋች በታክሲ እጦት ሲንገላቱ ነበር፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከወትሮው የተለዩ ረጃጅም ሰልፎች ተስተውለዋል፡፡

‘ታሪፍ አነሰን’ እንዲሁም ‘በትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች የተጋነነ ቅጣት እየተቀጣን ነው’ በሚሉ ምክንያቶች አድማ የመቱ ታክሲዎች መኖራቸው ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አከለ “የተወሰኑ ባለታክሲዎች ዛሬ ወደ ስራ እንዳልገቡ እናውቃለን” ብለዋል፡፡ “የታክሲ ባለቤቶች ታሪፍ እንዲሻሻልላቸው ጠይቀውናል ፤ በዚህም የህዝብን የመክፈል አቅም እና የነዳጅ ዋጋን ታሳቢ ያደረገ ማሻሻያ ተደርጓል” ሲሉ ገልጸዋል።

ይሁንና ከላይ ከተቀመጡት ምክንያቶች ውጭ “ዝም ብለን የታሪፍ ማሻሻያ አናደርግም” ያሉት ኃላፊው “በዛሬው አድማ ላይ በተሳተፉት ላይ #እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በአድማው የተሳተፉት “ጥቂት ታክሲዋች ናቸው” ያሉት ኃላፊው በከተማው የትራንስፖርት ችግር እንዳይፈጠር ፐብሊክ ባስ፣ ሸገር ባስ እና ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን በስፋት በመጠቀም ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትራፊክ አደጋ ከ21 ሰዎች በላይ ህይወታቸው አለፈ። በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በቤዛ ብዙሃን ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡሃች አካባቢ ዛሬ መጋቢት 6/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ከጎንደር ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ ዋሊያ ባስና ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ተነስቶ ወደ ወይን ውሃ ይጎዝ የነበረ ቅጥቅጥ አይሲዙ መኪና ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ21 ሰው በላይ…
የሟቾች ቁጥር 30 ደረሰ።

ዛሬ መጋቢት 6/2013 ዓ.ም ምስራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በቤዛ ብዙሃን ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡሃች በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 30 መድረሱን የሸጋው ሞጣ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

እንደ ሸጋው ሞጣ አጠቃላይ ሆስፒታል መረጃ በሆስፒታሉ ውስጥ 30 ሰዎች ሞት፣ 6 ለከፍተኛ ህክምና ወደ ባህር ዳር ሪፈር የተባሉ እና 11 ቀላል ቁስለኞች እንደሆኑ አመላክቷል፡፡

መረጃው የሞጣ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ልደቱ አያሌውን ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው።

"የሽግግር መንግሥት ይመስረት የሚል ሰነድ በቤታቸው ተገኝቷል" በሚል በመንግሰት ግልበጣ ተከሰው ለሰባት ወራት ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ በቢሾፍቱ በዋለ ችሎት በነፃ ተሰናብተዋል።

ምንጭ፦ አውሎ ሚዲያ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በቁጥጥር ስር የዋሉ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ፦

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከ3 ሺህ በላይ የብሬን እና የክላሽንኮቭ ጥይት በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የተገኙ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-27129 አማ የሆነ ተሽከርካሪ ከሃራ ከተማ ተጭኖ ወደ መርሳ ከተማ ሊገባ የነበረ 3 ሺህ 184 የብሬን ጥይትና 31 የክላሽንኮቭ ጥይት ትናንት ሌሊት በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

አሽከርካሪውን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ሲዳማ ክልል ጭኮ ከተማ እና በሀዋሳ ከተማ ከተማ ትላንት በግለሰብ ቤት ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

በጭኮ ከተማ 30 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና ሁለት መትረየስ የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ ፋራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ወልደ አማኑኤል ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 98 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከ4,583 መሰል ጥይት ጋር እና 3,546 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል - ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia