TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የመምህራንድምጽ

" አይደለም ያለ ደመወዝ በደመወዝም እንኳን ኑሮን አልቻልነውም ፤ ደመወዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል " -  መምህራን
 
ከየካቲት ወር 2016 ጀምሮ #እየተቆራረጠ 50% ፣ 30% እየተከፈለ ቆይቶ እስከ የሰኔ ወር ሳይጨምር ውዝፍ ደመወዝ ከ70 እስከ 120% አልተከፈለንም ያሉ በጎፋ ዞን የአይዳ ፣ ገዜ ጎፋ እና ደምባ ጎፋ ወረዳ መምህራን ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ያለደሞዝ አይደለም በደሞዝም ኑሮን አልቻልነዉም " የሚሉት መምህራኑ " ስቃያችን መች ነዉ የሚያበቃው ? " ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር፥ " የመምህራኑን ድምጽ በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ሳሳዉቅ ቆይቻለሁ " ብሏል።

መምህራኑም አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው እንደነበርም አስረድቷል።

ነገር ግን የዞኑ አስተዳደር እና የትምህርት መምሪያው ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠቱ መምህራኑ የአመራሩን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሰምኑ እነዚህ መምህራን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሠልፍ ለመጠየቅ ሲሞክሩ  የዞኑ መምህራን ማህበር ከአመራሩ ጋር ውይይት እያደረገ በመሆኑ ሠልፍ እንዳይወጡና በትዕግስት እንዲጠብቁ በማድረግ መመለሱን ማህበሩን አሳውቆናል።

ይሁና መምህራኑ ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ጥያቄ ለማቅረብ ወደተለያዩ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች መሄዳቸውና በዛም " በዚህ ደረጃ መቀጠል አንችልም ደሞዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል !! " በማለት ድምጻቸዉን ማሰማታቸዉ ተገልጿል።

እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ካሁን በፊትም በሌሎች የክልሉ ዞኖች ውስጥም መስተዋላቸውን አንስተን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዉ ዶክተር ታምራት ይገዙ ፤ "  ችግሩን እንደ ክልል ከየካቲት ወር ጀምሮ መቅረፍ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመምህራንን ደሞዝ በተመለከተ አሰራሩ ዲሴንትራላይዝ ተደርጎ ለየዞኖቹ መሰጠቱን የገለጹት ኃላፊዉ " እኛ ቴክኒካል ድጋፍ እያደረግን ብቻ ነው ያለው " በማለት የደመወዝ ጉዳይ ለነሱ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

" ችግሩ በዚህ ደረጃ ከተስተዋለ ግን ገምግመን ድጋፍ የምንሰጥ ይሆናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የመምህራንድምጽ

“ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም ” - የአፋር ክልል መምህራን 

“ ያልተመገበ መምህር ክፍል ግባ ቢባልም ሊገባ አይችልም ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር


በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የሚገኙ መምህራን ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው፣ በዚህም ቤተሰብ ራሱ ማስተዳደር እንዳልቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

መምህራኑ፣ “ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ታዲያ ቤተሰብስ እንዴት እናስተዳድር? ” ሲሉ በአንክሮ ጠይቀዋል።

ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው የሚመለከታቸውን አካላት እንደጠየቁ፣ ሆኖም መፍትሄ እንደሌለ፣ በዚህም ችግር ላይ እንደሆኑ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበርም ቅሬታው አግባብ መሆኑን ገልጾ፣ “ እንደውም እስከ ርዕሰ መስተዳደሩ ቢሮ ድረስ ጋውናቸውን ለብሰው ሂደው በክልሉ ልዩ ኃይል ነው የተመለሱት ” ብሏል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፣ “ ቅሬታቸው የቆዬ ነው። የ3 ወራት ደመወዝ ተባለ እንጂ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ የትምህርት ማሻሻያ፣ የደረጃ እድገት የማይሰጥበት አካባቢ አለ ” ብለዋል።

“ አሁን ላይ ደግሞ ደመወዝ ይቆረጣል። ለድርጅት ተብሎ ሁሉ ደመወዝ የሚቆረጥበት አካባቢ አለ ” ሲሉ ተናግረዋል።

መምህራኑ የ3 ወራት ደመወዝ እንደተቆረጠባቸው፣ በዚህም የክልሉ መምህራን ማኀበር፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር  ጥረት እንዳደረጉ የገለጹት አቶ ሽመልስ፣ “ ታች ያለው አመራር የላይኛውን የሚሰማ አይደለም ” ብለዋል።

“ መምህራን ግን ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተጋለጡ ናቸው፤ እዚያ አካባቢም (ሰመራ) በጣም የከፋ ችግር ነው ያለው ” ሲሉ አክለዋል።

ታዲያ ማኀበሩ ለቅሬታው ምን ምላሽ አገኘ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ “ ቀደም ብለን ለርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አወል አርባ ደብዳቤ ፅፈንላቸዋል። እሳቸውም ለታችኛው መዋቅር ችግሮቹ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ብለው በደብዳቤ አሳውቀዋል ” ብለዋል።

ሆኖም ከታች ያሉት አመራሮች ጉልበተኛ እንደሆኑ ነው አቶ ሽመልስ ያስረዱት።

“ አንድ መምህር ደመወዙ እየተቆረጠበት፣ ጉልበቱ ሌላ ጋ ከሆነ፣ ያልተመገበ መምህር ክፍል ውስጥ ግባ ቢባልም ሊገባ አይችልም። በጉልበት ቢገባ እንኳ ያስተምራል ወይ ? የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው ” ብለዋል።

ይህ ድርጊት መማር ማስተማሩ ላይ በቀጣይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸው፣ “ ምስቅልቅሉ የወጣ አሰራር ነው ያለው ” ሲሉ ወቅሰዋል።

“ የታችኛው አመራር ለትምህርት የማያስብ፣ ለጊዜው ለፓለቲካ ተቆጥሮ የማሰጠውን አጀንዳ ብቻ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ፣ መደማመጥ የሌለበት፣ ለትውልድ የማያስብ አመራር እያየሁ ነው ” ነው ያሉት።

በአማራ ክልል ያለው የመምህራን ቅሬታ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የመምህራንድምጽ

" የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ በዚህ ክረምት ለአቅም ግንባታ ስልጠና የገቡ መምህራኖችና ቤተሰቦቻቸው ለረሀብና ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል " ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ገልጸ።

" መምህራኑ በዚህ ሁኔታ በረሀብ ውስጥ ሆነው  መቀጠል አይችሉም የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ያስፈልገዋል " ሲል መልእክቱን አስተላልፏል።

ማህበሩ የሰኔ ወር ደመወዝ እስካሁን ያልተከፈላቸዉ ወረዳዎች 21 መድረሱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከነዚህ 21 ወረዳዎች 13ቱ በፐርሰንት ተቆራርጦ ጥቂት ገንዘቦች እንደገባላቸው ፤ በዚህ ሁኔታ መምህራኑ ህይወት ከባድ እንደሆነባቸው ገልጿል።

" የሚመለከታቸዉ አካላት ለደመወዝ መቆራረጥና አለመግባት እንደምክንያት የሚያቀርቡት የክልል ፋይናንስ ገንዘብ ባለ ማውረዳቸው ነው " የሚል ነው ያለው ማህበሩ " አሁን ላይ መምህራን ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ፤ ኑሮን መቋቋም እንዳልቻሉ ፤ በዚህም ምክንያት አልፎ አልፎ የመማር ማስተማር ሥራ እየተስተጓጎለ መቆየቱን አሳውቋል።

በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ በተደረገው የምክር ቤት ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ይኸው የደመወዝ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የደመወዝ መዘግየትና በፕርሰንት መከፈል አግባብ እንዳልሆነና የክልሉ መንግስትም ለመምህራን ደመወዝ የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት ደመወዝና ጥቅማ ጥቅማቸው ወቅቱን ጠብቆ በጊዜ እንዲከፈል መመሪያ ሰጥቶ ነበር።

ነገር ግን አሁንም የሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ደመወዝ እስከ ድረስ ሙሉ ያልተከፈላቸውና በፐርሰንት እየተከፈላቸው ያሉ መምህራን መኖራቸውን ማህበሩ አመልክቷል።

ማህበሩ " አሁን ላይ የሰኔ ደሞዝ በመዘግየቱ ምክኒያት  የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና የገቡ የክልላችን መምህራኖችና ቤተሰቦቻቸው ለረሀብና ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል " ብሏል።

" ይህ ሁኔታ ስልጠናውን እንዳያስተጓጉለው አፋጣኝ መፍትሄ ያሻዋል " ም ሲል አሳስቧል።

የመምህራን ከደሞዝ መቆራረጥ ጋር ሲስተዋል የከረመ ከባድ ችግር በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊቀጥል ስለማይገባ መምህሩ የለፋበትንና የሚገባውን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በወቅቱ እንዲከፈል  የሚመለከታቸው አካላት ሁሉም  የድርሻቸውን እንዲወጡ አጽንኦት ሰጥቶ ጠይቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመምህራን ደመወዝ ጋር በተያያዘ በሰጠን ምላሽ " የደመወዝ ጉዳይ ዲሴንትራላይዝ ሆኗል የሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ አመራሮችን ነው " በማለት ችግሩ ካለ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድና መምህራን ደመወዝ ሊዘገይም ሆነ ሊቆራረጥባቸዉ እንደማይገባ መግለጹ የሚታወስ ነዉ።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የመምህራንድምጽ

° “ የደመወዝና የቤት ችግርን በተመለከተ የተገባልን ቃል አልተፈጸመም ” - የዩኒቨርሲቲ መምህራን

° “ ተደራጅተው መጠየቅ ነው ጠቃሚ የሚሆነው ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር


የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና የደመወዝ ጭማሪን በተመለከተ ተገብቶልን የነበረው ቃል እስካሁን አልተፈጸመልንም ሲሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰሙ።

" ምንም እንኳን በይፋም ባይሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ፤ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት ስብሰባ ቃል ገብተው ነበር " ያሉት መምህራኑ ሆኖም ጭማሪ እንዳልተደረገላቸው ገልጸዋል፡፡

ከጭማሪው ጋር በተያያዘ ካሁን በፊት በጠቅላይ ሚንስትሩ ትዕዛዝ  ከመምህራን ማህበር ፥ ከትምህርት ሚንስትር እና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተዉጣጣ ኮሚቴ ተሰይሞና ተጠንቶ ተግባራዊ ሊደረግ የነበረ ባለ ሶስት አማራጭ የደሞዝ ስኬል አማራጭ እንደነበር አንስተዋል።

" የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ይህ ጥናት ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለተወካዮቻችን ገልጸው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ አልተደረገም " ብለዋል።

" ከዛ በኋላ ህዳር 26 ጀምሮ አድማ ተደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ጥር 2015 ዓ.ም ላይ ሐምሌ 1/2015 ጀምሮ ጭማሪ ይደረጋል ያሉ ቢሆንም እስካሁን የተደረገ ጭማሪ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በሀገራችን ከፍተኛ ወጭ ወጥቶበት ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የተጠና ደመወዝ ተግባራዊ ሳይደረግ ቀርቷል። " ያሉት መምህራኑ ተግባራዊ እንደማይደረግ ከታወቀ ፦
° ጥናቱን ለምን አጠኑት ?
° ለምንስ ከፍተኛ ወጭ ወጥቶ እንዲጠና ተደረገ ?
° ከተጠና በኋላስ ለምን ተግባራዊ ሳይደረግ ቀረ ?
° ከአሁን በፊት የተጠናውን ጥናት ተትቶ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከመጡ ጀምሮ ባለሙያ መድቤ እያስጠናሁ ነው ያለሁት ጥናት በሚቀጥለው ህዳር 2017 ይጠናቀቃል ማለት ምን ማለት ነው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም ነሐሴ 30/2015 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር አመራሮች በተገኙበት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩኒቨርቲ መምህራን የቤት ችግር በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ መግለጻቸውን ማኀበሩ በወቅቱ ማስረዳቱን አውስተዋል፡

ቃል ሲገባላቸው ቢቆይም እስካሁን በተግባር የተገለጸ ነገር እንደሌለ፣ በዚህም የኑሮ ውድነቱ መቋቋም እንዳልቻሉ አስረድተው፣ " የደመወዝና የቤት ችግርን በተመለከተ የተገባልን ቃል አልተፈጸመም " ሲሉ አማረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም መምህራኑ ላደረባቸው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ለመሆኑ መምህራኑ ተገብቶልን ነበር ያሉት ቃል በተግባር ከምን ደረሰ ? ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ)ን ጠይቋል፡፡

የማኀበሩ ፕሬዚንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ዩኒቨርሲቲ ላይ አንዳንድ ከእሳቸው (ከጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ማለታቸው ነው) ጋር ያወራናቸው ገዳዮች ነበሩ፡፡

ከክልል ርዕሳነ መስተዳድር ጋር አውርቻለሁ እንሄድበታለን ብለው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተደጋጋሚ ማግኘት አይቻልም፣ አገሪቷ ያለችበት ኮሚትመንትም ብዙ ነው፡፡

እንደዛም ሆኖ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከከተማ አስተዳደር ጋር ተመካክረን ችግሩን የፈቱበትን ሁኔታ ሼር እየተደራረጉ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡

ስለዚህ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያለውን የመምህራን ቅሬታ ፈርዘር የምንሄድበት ነገር እንዳለ ይሰማኛል። " ብለዋል።


ለቅሬታው መፍትሄ ለመስጠት የተኬደበት ነገር አለ ? የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጭራሽ ጥያቄያችን ተዘንግቷል የሚል ቅሬታ አላቸው ፤ ለሚለው ጥያቄያችን ፕሬዚዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል።

" እኛ መቼም ችግሩ እንዲፈታ ነው የምንፈልገው፡፡ ያ ደግሞ እንዲሆን የራሳችንን ክትትል ነው የምናደርገው፡፡ ወዲያው ደግሞ የሚፈለገው ሁሉ ላይሆን ይችላል።

እሳቸው (ጠ/ሚ አቢይ (ዶ/ር) ማለታቸው ነው) ያሉት ነገር አለ፡፡ እኛም ያልነው አለ፡፡ ከምን ደረሰ? እንዴት እንፍታ? ብለን መከታተላችን አይቀርም፡፡ ግን ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴርም የራሱን አስተዋጽዖ ቢያደርግ መልካም ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያዋጣቸው በየራሳቸው ማኀበር በየኒቨርሲቲ ደረጃ እደረጀን ነው ባልተደራጁባቸው እንዲደራጁ፣ ተደራጅተው መጠየቅ ነው ጠቃሚ የሚሆነው " ብለዋል።

ከዩኒቨርሲቲ በታች ባሉ የትምህርት ተቋማት የመምህራን የቤት ችግር እየተፈታ መሆኑን ማኀበሩ ያስረዳ ሲሆን፣ ከመምህራኑ ቅሬታ ጋር በቀጣይ ይቀርባል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የመምህራንድምጽ

° " ግንባታው እንዲቆም ተደርጎብናል " - መምህራን

° " ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል፤ ምርመራ ተጀምሯል " - የሀዋሳ ፖሊስ

ከሰሞኑን " በማህበር ተደራጅተን የምንገነባውን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማስቆም እንዲገነባልን ውል የገባውን ተቋራጭ አሰሩብን " ያሉ የሀዋሳ ከተማ መምህራን ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

መምህራኑ " አመራሩ ሊደግፈን ሲገባ እየገፋን ነው " ብለዋል።

" በሀገሪቱ ጠ/ ሚኒስትር ሳይቀር ለመምህራን ድጋፍ ተደርጎ የቤት ባለቤት የምንሆንበት መንገድ ይመቻች በተባለበት በዚህ ወቅት መምህራን የሚገነቡትን ቤት አስቁሞ ተቋራጭን ማሰር መንግስትና መምህራንን ለማጋጨት የታሰበ ሴራ እንጅ ሌላ ምንም አይደለም " ብለዋል።

" ድርጊቱ አሳፋሪ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

መምህራኑ፤ ከሳምንት በፊት አመራሩ በመምጣት " በርቱ " እንዳላቸውና ከፌደራል ሳይቀር እንግዳ ጋብዞ ፣ እገዛ ልናደርግ ዝግጁ ነን " እንዳላቸው ተናግረዋል።

በድንገት ግን ተገልብጦ ስራው ህጋዊ አይደለም ማለቱን ጠቁመዋል።

" ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በውይይት ማስተካከል ይቻላል " የሚሉት መምህራኑ ለ9 አመታት የቆመ ቤት ድንገት መሰራት ሲጀምር ለማስቆም መሯሯጥ ከጀርባው ሌላ ዓላማ ያነገበ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መምህራኑ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሩትን የህንጻ ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 መቀየራቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የማህበራት ማደራጃ እና የከንቲባ ጽህፈት ቤት የሚያውቀው እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ ሆኖ እያለ ግንባታው #እንዲቆም መታዘዙን ገልጸው ፤ " ወቅቱ መምህራን የሚደገፉበት እንጅ ጥሪታቸውን ያፈሰሱበትን የሚቀሙበት አይደለምና እንቅፋት የሆኑብን አካላት ሊተዉን ይገባል " ብለዋል።

" በህግ አምላክ እጃችሁን ከድሀው መምህራን ላይ አንሱልን ፤ ይህ ባይሆን ግን አደባባይ በመውጣት ጩኸታችንን ለማሰማት ዝግጁ ነን " ሲሉም ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማው አስተዳደር ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በአጠቃላይ ለስድስት የመምህራን መ/ቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት የጻፈውን ደብዳቤ ደርሶት ተመልክቷል።

በዚህም ደብዳቤው ፦

- የነበረው ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 ማስተካከያ እንዲደረግ ተጠይቆ የG+4 ዲዛይን መሰጠቱ ፤

- ነገር ግን ይህ ዲዛይን የመምህራን መ/ቤቶች ማህበራት ከተደራጁበት አላማ አንጻር ተጻራሪ ዓላማ እንዳለው ስለተደረሰበት የG+4 ዲዛይን መሰረዙን ሌላ ደብዳቤ እስኪላክላቸው ድረስ ቀድሞ በነበረውም G+3 ዲዛይን ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ ያዛል።

የመምህራኑን ጥያቄ ይዘን ጥያቄ ያቀረብንለት የከተማው ፖሊስ ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደዉ ምርመራ እንደጀመሩበት በመግለጽ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የመምህራንድምጽ

" መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " - የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን

" በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ

ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በደረሰን የቅሬታ መልእክት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸዉ በመግለጽ በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ መሳተፍ እንዳልቻሉ ነግረዉናል።

መምህራኑ እንደሚሉት አሁን ላይ ከፊሉ በመንግስት አቅም ማሻሻያ ፕሮግራሞች ግማሹ ደግሞ በራሱ ፍላጎት ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ቢያቀናም ደሞዝ አለመለቀቁን ተከትሎ ግን ችግር ላይ ወድቀዋል።

አሁን ላይ በገቡባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ አላማቸዉን ካለማሳካታቸዉ ባለፈ ጥለዋቸዉ የመጡ ቤተሰቦቻቼዉ ረሀብ ላይ መዉደቃቸዉን ተከትሎ የሄዱበትን የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ጥለዉ ለቀን ስራ መዳረጋቸዉን ይገልጻሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በትራንስፖርት ችግር ምክኒያት ብዙ መምህራን በሚያስተምርበት አካባቢ ቢቀሩም በእንቅርት ላይ እንዲሉ ባሉበት አካባቢም የወባ ወረሽኝ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

ችግሩን የመንግስት አካላት ያዉቁታል የሚሉት የጎሪጌሻ የሜኒት ማጅና ቱም የጎልዲያና ሻሻ እንዲሁም የጋቺት እና ሱርማ ወረዳ  ቅሬታ አቅራቢዎች " መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቀናት በፊት ያነጋገርናቸዉ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ  በበኩላቸዉ በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል ብለዋል።

ሀላፊዉ አክለዉም ምናልባትም ችግሩ የበጀት ከሆነ አሁን ላይ በየወረዳዉ ግብር እየተሰበሰበ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት ችግሩ  ይፈታል በማለት የደሞዝ ችግሮ በቅርቡ እንደሚፈታ ገልጸዉልናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የመምህራንድምጽ

“ ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ አካቢዎች አሉ፡፡ ግን በአንዴ 700 ሺሕ መምህር አይዳረስም ” - ማኀበሩ

የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የቤትና የደመወዝ ችግር እየተፈታላቸው እንዳልሆነ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

መምህራኑ የገለጹት፣ ቤት የተሰጣቸው መምህራን ቢኖሩም ያልተሰጣቸውም እንዳሉ፣ ይህ ደግሞ በተለይ ከዝቅተኛ ደመወዝ ጋር ተዳብሎ ኑሮውን በእጅጉ እንዳከበደባቸው ነው፡፡

ቅሬታውን ያቀረቡት በተለይ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎ የሚገኙ መምህራን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲቀረፍ፣ ደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ የራሱን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ጠይቃዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመምህራኑን ቅሬታ ይዞ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ)ን ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ ምን አሉ ?

“ ሶማሌ ክልል አካባቢ ላይ ምንም አይነት መሬት አልሰጡም፡፡ ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ አካቢዎች አሉ፡፡ በሶማሌና አፋር ክልሎች፡፡ ግን በአንዴ 700 ሺሕ መምህር አይዳረስም፡፡

ድሬዳዋ በጣም ብዙ መምህራን ተሰጥተዋል፡፡ ሀረሪ ላይ በዚህ ዓመት ብቻ ለ34 መምህራን አንድ ሙሉ ኮንዶሚኒየም ተሰጥቷል፡፡ የአጠቃለይ ትምህርት ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ እተሰጠ ነው፡፡ አልተቋረጠም፡፡

ደብረ ብርሃን ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ኦሮሚያ ክልል ለምሳሌ በትምህርት
ቤት ጭምር መኖሪያ ቤት እየተሰራ ነው ለመምህራን፡፡

አዲስ አበባ ላይ በዚህ አመት ብቻ ከ400 በላይ ቤቶች ተሰጥተዋል፡፡ አሁን ደግሞ ቦታ ለመስጠት ተደራጁ ተብሎ በመደራጀት ላይ ናቸው፡፡

ለእያንዳንዱ ለ700 ሺሕ መምህር በአንድ ጊዜ መስጠት አይቻልም፡፡ ሁላችንም በአንዴ ቸኩለን የቤት ባለቤት እንሁን ቢባል አይቻልም፡፡ ችግሮች አሉ፡፡ በሂደት የአባሎቻችን ጥያቄ እየተመለሰ መሄድ አለበት ትክክል ነው፡፡

ከደመወዝ ጋር በተያያዘ የሥራ ክብደት ምዘና ተሰጥቷል፡፡

ደፍሬ ነው የምናገረው በሥራ ክብደት ምዘናው መምህራን የተቀመጡበት ቦታ ትክክለኛ ቦታ ላይ ነው፡፡ ኢንፈሌሽኑ ኢንፈሌትድ ሆኗል፡፡

እሱን ጥያቄ ለጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) አንስተናል፡፡ ከደመወዝ ጋር በአጠቃለይ የተያያዘው ምናልባት እንደ መንግስት አሁን ከከረንሲ ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚጨመር ነገር አለ ሚባል ነገር አለ፡፡ አጠቃላይ ሆነውን ነገር የምናየው ነው የሚሆነው፡፡

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቅሬታ ግን አልተፈታም፡፡

የእነርሱ በተለዬ መንገድ መፈታት ነበረበት እየተፈታ አይደለም፡፡

ለጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር)ም አንስተናል፡፡ አሁንም በሂደት ላይ ነው፡፡ ዛሬ ተጠይቆ ነገ መልስ ይገኛል የሚል እምነት የለንም እናም የሂደት ውጤት ነው። ”

የማኀበሩ ፕሬዚዳን ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፦

“ ስታክ አድጎ የነበረው የዩኒቨርሲቲዎች እንጂ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ላይ ችግር የለም፡፡ ግን አንዳንድ ክልሎች አካባቢዎች የመሬት አቅርቦት ችግርም አለባቸው፡፡ ግን ያልሄዱባቸው ደግሞ እንዳለ ሪፖርት አለ፡፡

አይሆናችሁም የሚል ሳይሆን ከቢሮክራሲ ጋር የሚያያዝ  ነገር ነው ችግሩ፡፡ የእኛም አመራር በቅርበት ክትትል አድረጎ ከሚመለከታቸው ጋር ሆኖ ማስፈጸም፣ መምህራንም በማኀበር መደራጀት አለባቸው፡፡ ያልተሟሉ ነገሮች ካሉ እነርሱን ማሟላት የሚያፈልግ ይመስለኛል። ” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Lecturers Claims and questions -.pdf
1.3 MB
🔈 #የመምህራንድምጽ

የዩኒቨርስቲ መምህራን ጉዳይ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ መምህራኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ መልዕክት የላከ መምህር ፥ " የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነንም መሆን የፈለግነውን ሆነናል ነገር ግን እንኳ ቤተሰብ ልናስተዳድር እራሳችንን እንኳ መመገብ አልቻንም ልጅ ወልድን እንዳናሳድግ ሆነናል " ብሏል።

" የከፍተኛ ትምህርት መምህራን ሆነን ጎዳና ልንወጣ ነው " ያሉት መምህሩ " ምንም ጥርጥር የለውም የምሠማንም የለም። ድምጻችን ግን ይሰማ " ብለዋል።

መምህራንና የቴክኒክ ረዳቶች ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የሚከፈላቸው ክፍያ አይደለም ህይወትን ለመቀየር ከወር ወር ለመድረስ ፈተና እንደሆነባቸው አመልክተዋል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚጠይቁት ምንድነው ? ከላይ በፋይል ተይይዟል።

@tikvahethiopia
🔈#የመምህራንድምጽ

ድምጻቸውን ለማሰማት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተሰባስበው በመመካከር ላይ የነበሩ መምህራን በፖሊስ ተበተኑ።

በወላይታ ዞን ስር ያሉ መምህራን " ሀሳባችን እንዳንገልጽ ፖሊስ አደናቀፈን " ሲሉ ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" ወደመንግስት አካላት በመሄድ ረሀባችን እወቁልንና ደሞዛችን በወቅቱ ክፈሉን በማለት  ልናሳዉቅ እንጅ ረብሻ ለመፍጠር አልነበረም ተሰባስበን ስንመካከር የነበረው " የሚሉት መምህራኑ " ከረሀባችን በላይ ተሰባስበን በመመካከር ድምጻችን እንዳናሰማ መደረጉ አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ላለፉት 3 ወራት ያለደሞዝ ቆይተን የሰኔን ብቻ ሰጥተውናል ይሄ ለመምህራን ችግር ግድ የለሽ መሆናቸውን " አሳይቶናል ብለዋል።

አሁን ላይ በዱቤ ይሰጡን የነበሩ ነጋዴዎችም መከልከል በመጀመራቸዉ ተቸግረናል ሲሉ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

" ስራቸውን ለመስራትና የባለስልጣናቱን ትእዛዝ ለመፈጸም የመጡ ፖሊሶች  እንኳን ረሀባችሁን እኛም እናውቀዋለን " በማለት እያዘኑ በተኑን በማለት ሀዘናቸውን የገለጹት መምህራኑ " ከዚህ በላይ ሞት እንጅ ሌላ ተስፋ እየታየን አይደለም "  ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

" በመሆኑም አሁን ላይ በፖሊስ በመገፋታችንና ባለስልጣናቱም ስብሰባ ገቡ በመባላቸዉ  ወደመጣንባቸው አካባቢዎች ብንመለስም ረሀባችን የከፋ መሆኑን ለመግለጽ  ተጠናክረን መጮሀችን ይቀጥላል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በክልሉ ስላለዉ የመምህራን ደሞዝ መዘግየትና መቆራሪጥ ላነሳንለት ጥያቄ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ወረዳዎች ከገቢያቸዉ ክፍያ የሚፈጽሙበት አስራር መዘርጋቱንና ችግሮች ከተፈጠሩ ጣልቃ በመግባት እርማት እንደሚደረግ መግለጹ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈#የመምህራንድምጽ

" መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ እኛ መኖር ከብዶናል !! " - ቃላቸውን የሰጡ መምህራን

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

የማህበሩ ስብሰባ ላይ ፦

መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣

ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣

ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣

ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣

በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣

የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ...ወዘተ በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተው ነበር።

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የትምህርት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተው ምላሽ እንደሰጡ በማህበሩ ተገልጿል።

ስብሰባው የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀው።

ይህንን የማህበሩን ስብሰባ መደረግ የሰሙና ማህበሩም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠውን ቃል ያነበቡ በርካታ መምህራን መልዕክታቸውን ልከዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ መምህራን ፥ " እኛ መግለጫና የማይጨበጥ ወሬና መስማት ሰልችቶናል የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

" እኛ መኖር ከብዶናል !! ስብሰባ ከዛ መግለጫ ምን ይሰራልናል ? ምን ያህል ዋጋ እየከፈልን እንዳለን እኛ ነን የምናውቀው ልጅ ማሳደግ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር እጅጉን ፈተና ከሆነብን ሰንብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ማህበር በየጊዜው መግለጫ ነው የሚሰጠን ምንድነው ጠብ የሚል ስራ የተሰራው ? ይሄን ይመልሱልን " ሲሉ ጠይቀዋል።

" መግለጫና ወሬ ምንድነው የሚሰራልን ? ችግራችንን ደጋግሞ መናገር መፍትሄ ከሌለው ጥቁሙ ምን ላይ ነው ? የማይታወቅ ችግር ያለ ይመስል ሁሌ አንድ አይነት ነገር መናገር ያሰለቻል ደክሞናል " ብለዋል።

" መብታቸውን የእንጀራ ጥያቄያቸውን የላባቸውን ደመወዝ ስለጠየቁ ብቻ መምህራን መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ሲሆን እንኳን መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም " ሲሉ አማረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ መምህራን ፥" በሚዲያው መግለጫ ሳይሆን ተግባራዊ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ ብቻ ነው የምንፈልገው " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

" ሰራተኛው ኑሮው ቢከድበውና የሚጮኽበት እዲሁም ችግሩን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠው ቢያጣ ነው ወደሚዲያ የሚቀርበው ስለዚህ እባካችሁ ድምጻችንን ይሰማና መፍትሄ ስጡን " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM