TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

በካሜሮን ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የሀገሪቱ መንግሥት ገልጿል፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ዛሬ ዓርብ የካቲት 27/2012 ዓ.ም ነው የመጀሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱ የተረጋገጠው፡፡

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የፈረንሳይ ዜግነት ያለው የ58 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ ግለሰቡ ካሜሩን መዲና ያውንዴ ከገባ በኋላ የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ሲረጋገጥ በቀጥታ ወደ ለይቶ ማቆያ ገብቶ በከተማው ማዕከላዊ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተለ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

#CGTN #AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች...

ዛሬ ጥዋት የሀዋሳ ከተማ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በከተማው የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን ሪፖርት አድርገዋል።

ላለፉት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ነዳጅ ለማግኘት ፈተና ሆኗል፤ በከተማው ረጃጅም የሞተር እና የመኪና ሰልፎች አሉ ብለዋል።

ነዳጅ ለማግኘት መጉላላት እና የስራ መስተጓጎል የየእለት የህይወታችን አንዱ ክፍል ከሆነም ሰንብቷል ሲሉ አማረዋል።

በተመሳሳይ ነዳጅ ለማግኘት በመሰለፍ በሚያጠፉት ጊዜ በአማካይ እስከ 150 ብር እንደሚያጡ በባሕር ዳር አብመድ ያነጋገራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ገልፀዋል፡፡

እናተስ የት ከተማ ይህ ችግር አጋጠማችሁ?

#AMMA #TikvahFamilyHawassa
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም ተከታዮቹ መመሪያዎች ተፈፃሚ እዲሆኑ አዟል፦

- የመዝናኛ ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ከነገ መጋቢት 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ፣
- ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ፣
- ሰርግን ጨምሮ ተያያዥ ማኅበራዊ ግንኙነቶች እንዲቆሙ፣
- የተሽከርካሪ ባለቤቶች ከመደበኛ የመጫን ልካቸው በግማሽ እንዲቀንሱ፣
- የፓርቲም ሆነ የመንግሥት ስብሰባዎች እንዲቆሙ፣
- ለሌሎች ማኅበራዊ መስተጋብሮች እንዲቀንሱ፣
- ሰዎች ወደ ግብይት ማዕከላት አዘውትረው እንዳይሄዱ፣

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሺሻ፣ ጫትና ፑል ቤቶች ላይ ርምጃ ተወሰደ!

በሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝን ለመከላከል የሺሻ፣ ጫትና ፑል ቤቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን የወረርሽኝ መከላከል ግብረ ኃይሉ ገልጿል።

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ኅብረተሰቡ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል!

የጎዳና ተዳዳሪዎች እንዲሁም አቅመ ደካማ ወገኖች ለርሃብ እንዳይጋለጡ ኅብረተሰቡ በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር መሐሪ ታደሰ ጥሪ አቅርበዋል።

የመኝታ ፍራሽና ብርድ ልብስ ፣ አልባሳት ፣ እንደ ማካሮኒ ፣ ፓስታ ፣ ዱቄት ፣ ሩዝ ያሉ የምግብ ዓይነቶችን 'ሙሉ ዓለም የባሕል ማዕከል' በሚገኘው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቦታ ማድረስ ይቻላል።

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በፈረንሳይ በሆስፒታል ያሉ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እቀነሰ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 367 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 23,660 ደርሷል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 586 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 21,678 ደርሷል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 2,091 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 382 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከቻይናና ኢራን በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 6,411 ሰዎች በቫይረሱ መያቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 93,558 ደርሰዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ58,000 በላይ ሆኗል።

- በሩዋንዳ 5 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 212 ደርሷል። በሌላ በኩል 2 ተጨማሪ ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 95 ደርሰዋል።

- በግብፅ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 5,042 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 260 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በተጨማሪ 22 ሰዎች መሞታቸው ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 359 ደርሷል።

- በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 4,996 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 203 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- ትላንት የኬንያ መንግስት የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናዎች መስጫ ጊዜያት እንደማይራዘም አሳውቋል ፤ የዚህ ዓመት የብሔራዊ ፈተናዎች በመርሀ ግብሩ መሠረት የሚሰጡ ይሆናል፡፡ በትምህርት መርሀ ግብሩ ያልተሸፈኑ ይዘቶች በፈተናዎቹ አይካተቱም ተብሏል - #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
16 የኮቪድ-19 ታማሚዎች እየተፈለጉ ነው! በሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል አስራ ስድስት (16) ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል፡፡ የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አውላቸዉ ታደሰ ለአብመድ እንደተናገሩት በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ አስተባባሪ…
#UPDATE

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለባቸው ተረጋግጦ ሲፈለጉ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል 15 መገኘታቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡

ከተገኙት 15 አሽከርካሪዎች ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እና ሦስቱ ደግሞ አዲስ አበባ ወደ ሚገኝ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡

አንድ (1) የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለበት የተረጋገጠ አሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ጥሪ ባለመቀበሉ እስካሁን እንዳልተገኘ እና ፍለጋው መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል - #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 960 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ነሐሴ 18/2012 ዓ.ም ከጧቱ 2 ሰዓት ገደማ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር አቅጣጫ ይጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ አ.አ 30276 የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሸከርካሪ አደንዛዥ እፅ ጭኖ ሲንቀሳቀስ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ሊያዝ ችሏል።

ተጠርጣሪው ተሸከርካሪውን አቁሞ ለጊዜው ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

የአደንዛዥ እፁ ምንነት ለጊዜው በውል ባለመታወቁ በምርመራ ለመለየት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተነግሯል።

ከ አደንዘዥ እፁ ጋር አብሮ የአትክልት እና ፍራፍሬ ፣ 43 ኩንታል የእንስሳት መኖ፣ አብሮ በመጫን ለሽፋን ቢጠቀሙም ለፖሊስ በተደረገ ጥቆማ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ !

- የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

- ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለሀገራችን አሥራ ሦስተኛ ፣ ለአማራ ክልል ደግሞ ሦስተኛ ነው።

- በአሁን ሰዓት ኢንዱስትሪ ፓርኩ 8 የተሟላ ቁሳቁስ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎች የያዘ ሲሆን ፣ በቅርቡ ሥራ ይጀምራሉ።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፖርክ 75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 2ኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ግንባታ 125 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል።

- ፓርኩ በቅርቡ ከ4,000 በላይ ሠራተኞችን ለመቀበል ልየታ ሰርቷል። በሙሉ አቅሙ በ2 ፈረቃ ሲሠራ 10 ሺህ ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

- በአካባቢው ለነበሩ የልማት ተነሺዎች ቅድሚያ የሥራ ዕድል ይሰጣል ተብሏል።

- በፖርኩ እስካሁን ‘ሆፕሉን’ የተባለ ኩባንያ ለጨርቃ ጨርቅ እና ጋርመንት ምርት 8 ሼዶችን ወስዷል። በ1 ሼድ ላይ መሣርያ የገጠመ ሲሆን ሠራተኞችን እያሰለጠነ ይገኛል። ከመጪው መጋቢት ጀምሮ ምርቶቹን ወደ አሜሪካና አውሮፖ ኤክስፖርት ማድረግ ይጀምራል።

#DrAbiyAhmed #AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ተናገሩ። ለዚህም የማኅበረሰቡ መዘናጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሐምሌ ወር ላይ ከነበረው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም 78 በመቶ ምጣኔ አሁን ወደ 52 በመቶ መውረዱን ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ያለው የጽኑ ህሙማን ክፍል ማከሚያ ማዕከላት መጨናነቃቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የፅኑ ህሙማን ክፍል የመጨረሻ የመቀበል አቅም ላይ እየደረሰ ነው ብለዋል።

የፅኑ ህክምና ክትትል ከገቡት 59 በመቶ ህይወታቸው እንዳለፈም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ሊያ ፥ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ ትኩረቱን ካላጠናከረ ከባድ የህይወት መስዋትነት ሊያስከፍል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙት ክትባቶች በዚህ ዓመት ከሚያዝያ ወር በፊት እንደማይደርሱ ተናግረዋል። ክትባቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ #AMMA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia