TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ ጋር እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በተለያዩ ዙሮች በሥራ ፈጠራና ፋይናንስ ላይ ለሚሰጠው የስልጠና ፕሮግራም የመክፈቻ መርኃግብር በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል።

ለስልጠናው ከተመዘገቡ ከ3000 በላይ አመልካቾች ውስጥ በተለያየ መስፈርት የተመለመሉ 400 የሚሆኑ ሰልጣኞች በሁለት ዙር ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

በመጀመሪያ ዙር ስልጠናውን እንዲወስዱ የተመረጡ 200 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ ለሦስት ወራት ሥልጠናውን የሚያገኙ ይሆናል።

የመጀመሪያው ወር ስልጠና በአካል ተገኝተው ይወስዳሉ። በ2ኛው ወር ሰልጣኞቹ በመረጡት የቢዝነስ ኃሳብ ላይ ድጋፍ እንዲያገኙ እገዛ ይደረግላቸዋል። በ3ኛው ወር ኃሳባቸውን ለሦስተኛ አካል እንዲያስረዱ በማድረግ ሰልጣኞች የቢዝነስ ኃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ ምዕራፍ እንዲያደርሱት ይደረጋል።

በመጨረሻም በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፉ ሰልጣኞች ያቀረቡትን የቢዝነስ ኃሳብ ለኢንቨስተሮች እንዲሁም የቢዝነስ ኃሳቦች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ግለሰቦች እንዲያቀርቡ እድሉ ይመቻችላቸዋል ተብሏል።

በመክፈቻው መርኃግብር የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ የስቴም ፓወር ዋና ስራ አስፈጻሚ ቅድስት ገብረአምላክን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶችና ሰልጣኞች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

#STEMPower #VISA #TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia
#Update

ስቴም ፓወር ከቪዛ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና 114 ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ለሦስት ወር ተከታትለው አጠናቀዋል።

በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከተካፈሉ ሰልጣኞች የሰሯቸው ፕሮጀክቶች የተለያዩ ምዕራፎችን አልፈው በቅርቡ ሥራዎቻቸውን ለኢንቨስተሮች የሚያቀርቡ ሲሆን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋርም ትስስር የሚፈጠርላቸው ይሆናል።

የስልጠናው ሁለተኛ ዙር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን በዚህ ዙር ሦስት መቶ ሰልጣኞች ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በስልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ ዝርዝር መስፈርቶች እና ምዝገባውን https://telegra.ph/TRAINING-ANNOUNCEMENT-04-09 ላይ ያገኙታል።

https://forms.office.com/r/6cXD0LffWe

#STEMpower #VISA #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ!

ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሁን ላይ 4ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት በምዝገባ ላይ እንገኛለን።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 9 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, including coaching and pitching)

• 8 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

👉 የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

👉 የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

👉 ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን፤

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ 👇
https://forms.office.com/r/TtnFJdedji

#StemPower #VISA #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Update

ስቴም ፓወር (STEMpower) ከቪዛ (Visa) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት 4 ዙሮች ከ600 በላይ ሰልጣኞችን አሳትፏል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ ሰልጣኞች መካከል የፈጠራ ሀሳባቸውን ወደ መሬት በማውረድ ሥራ የጀመሩ እና ለመጀመር በሂደት ላይ ያሉ ሰልጣኞች ይገኙበታል።

አሁን ደግሞ 5ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት ምዝገባው እየተካሄደ ነው።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 6 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, Coaching and Pitching)

• 9 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ ሐምሌ 22 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3PK7LY2

#StemPower #VISA #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ! ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል። ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። አሁን ላይ 4ተኛ…
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት 4ኛ ዙር በማጠናቀቅ 240 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስቴም ፓወር በቀጣይ አምስተኛ ዙር ሰልጣኞችን መዝገባ በማከናወን ሥልጠናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16 ሥልጠናው መሰጠት ይጀምራል። በኦላይን ለመሰልጠን ለተመዘገቡም ስለጠናውን እየተሰጠ ይገኛል።

ከ4ኛው ዙር የተመረጡ ምርጥ 4 ፕሮጀክቶች፦

1. ግብርና እና ምግብ ዘርፍ፦

- ዮፍታሔ ሳሙኤል - Mushroom Agro-processing

- ​​ስጦታው አበራ - Punt Flour from Gipto

2. አገልግሎት ዘርፍ፦

- Wujo Digital Iqub

3. ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ:

- መኮንን አስማረ - Agricultural Chemical Spray & Aerial Mapping Drone

በልዩ ዘርፍ፦ ዶ/ር ትዝታ አለሙ - Biruh Hiwot Mental Health Consultancy

#STEMpower #VISA #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#STEMPower  #EIPA

ስቴም ፖወር በተለያዩ ዙር ባሰለጠናቸው ወጣቶች እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በሚገኘው ማምረቻ ቦታው የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን የባለቤትነት መብት ጥበቃ እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

የሁለቱ ተቋማት ስምምነት በተለይ ወጣቶች የሚሰሯቸው የፈጠራ ውጤቶች በሌሎች እንዳይቀሙ እና አቅማቸውን አጎልብተው ወደገበያ እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም የተለያዩ ሥልጠናዎች ለወጣቶቹ እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
#STEMPower   #TikvahEthiopia

ስቴም ፖወር ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ግቢ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት 7 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የወጣቶች የመጀመሪያ ደረጃ የአቅም ግንባታ ሥልጠና የምርቃትና የማበረታቻ መርሐግብር በትላንትናው ዕለት ተከናውኗል።

ሥልጠናውን ለመውሰድ 2,289 ወጣቶች የተመዘገቡ ሲሆን 578 ወጣቶች በስልጠናው ተካፍለዋል (ቢያንስ የስልጠናውን አንዱን ክፍል ወስደዋል።

ከሰልጣኞቹ 60% የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 40% የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

በዕለቱ ከ5 ቀናት በላይ የተሰጡ ስልጠናዎችን የተከታተሉ ሰልጣኞች ከስቴም ፖወርና ከቲክቫህ የተዘጋጀላቸውን ሰርተፊኬት የወሰዱ ሲሆን ሌሎች ሰልጣኞች ዲጂታል ሰርተፊኬት የሚደርሳቸው ይሆናል።

በመርሐግብሩ ላይ በስቴም ፖወር፣ ቪዛና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትብብር በተሰጡ ስልጠናዎች አልፈው የራሳቸውን ድርጅት የመሰረቱትና በፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የተሰማሩት ውጆ አፕ (Wujo App) ለተመራቂዎች ሥራቸውን አስተዋውቀው አስመርቀዋል።

በቀጣይ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሥልጠናዎችን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#STEMpower #VISA #TikvahEthiopia

ስቴም ፓወር፣ ቪዛና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመተባበር ሲያዘጋጁት የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስቴም ፓወር (STEMpower) ፣ ቪዛ (Visa) እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) በጋራ በመሆን ሲያዘጋጁት የቆዩትና በአስር ዙር የተሰጠው የስራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ተገባዷል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በአስር ዙር ሲሰጥ በነበረው በዚህ ሥልጠና በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል 16,400 ሰልጣኞች ስልጠናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። ይህም በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየ ነበር።

በዚህ ሥልጠና፥ 2,420 በሰልጣኞች ያሰለጠኑ ሲሆን ሥልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ከጨረሱ ሰልጣኞች ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ጀማሪ ቢዝነሶችን በራሳቸው ጀምረው ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል።

በዚህ ፕሮጀክት ከሥልጠናው ባሻገር ነፃ የቢዝነስ ማማከር እና ለፕሮቶ ታይፕ መስሪያ የሚሆን የማሽነሪ እና ጥሬ እቃ ለሰልጣኞች ሲያቀርብ ቆይቷል።

በዚህ አጋጣሚ ወጣቶችን በስፋት ተጠቃሚ ባደረገውና ለውጥ መፍጠር በቻለው በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተሳተፉ አጋር አካላትን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሊያመሰግን ይወዳል።

@tikvahethiopia