TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቸር ወሬ ከኢንጅነር ታከለ ኡማ⬆️

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶች 50 ለሚሆኑ ለተቸገሩ ዜጎች ተሰጡ ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶቸን #ለተቸገሩ የማስተላለፉ ተግባር በሁሉም ክፍለ ከተሞች #ይቀጥላል ብለዋል᎓᎓

የከተማው አስተዳደር የሰጠው ቤትና እያከናወነ ያለው ድሆችን የመርዳት ተግባር ለመደገፍ በላሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ 500 ሺህ ብር እንዲሁም አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚና ሌሎችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል᎓᎓

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች #ሀብታቸውን አስመዘገቡ፡፡ በቢሮው ስር የሚገኙ ተጠሪ መስሪያ ቤቶችም የስራ ኃላፊዎች የሀብት ምዝገባና እድሳት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ይህ አሰራርም ለሌብነት እና ንቅዘት የሚመቹ መንገዶችን ይዘጋል መባሉ ተሰምቷል፡፡ የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እስከ ህዳር 30፣ 2011 ዓ.ም የሀብት ማስመዝገቡ ስራ #ይቀጥላል ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikvahFamily በትላንትናው ዕለት የ2ኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍትና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ዘመቻ መካሄድ ጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር በጥቂት ቀናት 7 ሺህ በላይ መፅሀፍትና 3 ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር መሰብሰቡና በአማራ ክልልና በደቡብ ክልል ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች፣ በአዲስ አበባ ላለ የህዝብ ቤተመፅሀፍ መከፋፈሉ ይታወሳል። በዚህኛው ዙር በመፅሀፍት ደረጃ ከ30 ሺህ በላይ ለመሰብሰብ ታስቧል። በዚህ ዙር…
#ምስጋና

በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም)

ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል።

የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው።

ስራው ከመፅሀፍ ባለፈ የትምህርት መሳሪያዎችን ያካተተ ሲሆን ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ #ከየቤተሰቦቻችን መኖሪያ አካባቢ በመሄድ የተሰበሰቡ ፦

ትላንት ቅዳሜ ፦

- አቶ ዳንኤል ቦጋለ ከልጃቸው ነብዩ ዳንኤልና ከመላ ቤተሰባቸው ጋር መደበኛ መፅሀፍት 58 ፣ አጋዥ 2 ፣ የህፃናት 2 ፣ ልብወለደ 1 ፣ የግል ት/ቤት 11 መፅሀፍት አበርክተዋል።

- ወ/ሮ ኑሪያ አደም ከልጆቻቸው ሲያ አህመዝ ፣ ሀናን አህመድ፣ ረምላ አህመድ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር 9 አጋዥ መፅሀፍት ፣ መዝገበ ቃላት 3 ፣ መደበኛ 19 መፅሀፍት እና አንድ ሞኒተር አበርክተዋል።

- ወ/ሮ ሰብለ ተሾመ ከልጆቻቸው በረከት ፍስሃ፣ በእምነት ፍስሃ፣ በፍቅር ፍስሃ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር 38 መደበኛ መፅሀፍ 5 አጋዥ መፅሀፍ አበርክተዋል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የ5 ሺህ ብር 106 መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።

- ዶ/ር አለማየሁ ሀብተገብርኤል ከልጆቻቸው ቤተልሄም ፣ መክሊት፣ ዳግማዊት እና በመላው ቤተሰባቸው ስም አንድ #ከለር_ፕሪንተር እና #ሞኒተር አበርክተዋል።

#ይቀጥላል
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምስጋና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም) ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል። የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው። ስራው ከመፅሀፍ…
#የቀጠለ

ዛሬ እሁድ፦

- ካሌብ ጌትነት 10 መደበኛ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ወ/ሮ ሀሊማ ሙዘሚል ሀሰን እና አቶ አብድላዚዝ አህመድ ከልጃቸው ነሂማ አብድላዚዝ መሀመድ ጋር 31 መደበኛ መፅሀፍ ፣ 2 የግል ት/ቤት መፅሀፍ አበርክተዋል።

- መቅደስ ደረጀ መደበኛ 55 መፅሀፍ አበርክታለች።

- ናታን ደመቀ 8 አዲስ አጋዥ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬ ከልጆቻቸው ፀጋ ተመስገን፣ ሜሎና ተመስገን፣ ናርዶስ ተመስገን ጋር በመላው ቤተሰባቸው ስም 7060 ብር ወጪ አድርገው 45 መፅሀፍ ገዝተው አስረክበዋል።

- ወ/ሮ ህይወት እንድርያስ ከልጃቸው ቤዛዊት ነጋሽ ጋር 10 አጋዥ ፣ 3 መደበኛ መፅሀፍ አስረክበዋል።

- ሀዊ ጨምዴሳ 20 አጋዥ መፅሀፍት፣ 34 መደበኛ መፅሀፍት አስረክባለች።

- ወ/ሮ ፀጋ ለማ፣ ከልጆቻቸው በእምነት ወንደሰን፣ ያሬድ ወንደሰን እና እድላዊት ወንደሰን 25 መደበኛ እና 5 አጋዥ መፀሀፍት አበርክተዋል።

- አሚር መኑር 48 አጋዥ ፣ 14 መደበኛ መፅሀፍ አበርክቷል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል ከለቡ 28 መደበኛ መፅሀፍት ፣ 29 አጋዥ መፅሀፍት፣ 4 ልብወለድ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ኤግዞም የፋርማሲ እቃዎች አከፋፋይ 3000 ብር ወጪ የሆነባቸው መፅሀፍት አስረክቧል።

- አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የቤተሰባችን አባል የ2000 ብር መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።

ሁላችሁንም ቤተሰቦቻችንን እናመሰግናለን።

በዚሁ አጋጣሚ ጃፋር መፅሀፍት ቤትን እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።

የትላንት ቅዳሜ እና የዛሬ እሁድ #ድምር ብቻ ፦

👉 1,089 መፅሀፍት
👉 2 ላፕቶፕ
👉 2 ሞኒተር
👉 1 ፕሪንተር

#አዲስ_አበባ

#ይቀጥላል