TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመኪና_ስርቆት

አዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችን እና 33 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ይስተዋል የነበረውን የተሽከርካሪ ስርቆት ለመከላከል እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ የአዲስ አበባ ፖሊስ በጥናት ላይ በመመስረት የምርመራ እና የክትትል ቡድን አቋቁሞ ባካሄደው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችን ማስመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ተሽከርካሪዎቹ እየተሰረቁ አብዛኞቹ ወደ #ሃዋሳ ከተማ እንደሚወሰዱ በምርመራ ማረጋገጥ እንደተቻለ የገለፀው ፖሊስ ከተሰረቁት ተሽከርካሪዎች መካከል ሰባቱ በአዲስ አበባ የተገኙ ሲሆን የተቀሩት 15 ተሽከርካሪዎች ደግሞ በሀዋሳ ከተማ እና ከሀዋሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ተይዘው ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን አሳውቋል።

ተሽከርካሪ በመስረቅ፣ የተሰረቀውን ተሽከርካሪ በመግዛት እና በመደለል ተሳትፎ ያደረጉ ከአዲስ አበባ 19 ከሃዋሳ ደግሞ 14 በአጠቃላይ 33 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራው በስፋት መቀጠሉን ፖሊስ አክሎ አመልክቷል።

ተሽከርካሪዎቹን ለጥበቃ ምቹ በሆነ ቦታ ባለማቆም በሚፈጠር ክፍተት እና አሽከርካሪዎች ለልዩ ልዩ ጉዳይ የመኪናቸውን ቁልፍ ተሽከርካሪ ላይ ጥለው ሲወርዱ እና የተሽከርካሪውን ቁልፍ በልዩ ልዩ አጋጣሚ በማስቀረፅ ወንጀል ፈፃሚዎቹ የስርቆት ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል።

አዲስ አበባ ፖሊስ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝቦ ለስራው ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉት የፌዴራል ፖሊስና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል።

Via - AA POLICE

@tikvahethiopia