TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#KOBO የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ። የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ…
#ወልድያ

የወልድያ ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላለፈ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዛሬ ጥሪ አቅርቧል።

" የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻው እየተፋለሙ ነው "  ያለው የወልድያ ከተማ " የአካባቢው ማኅበረሰብ አካባቢውን ተረጋግቶ በመጠቅ ለጥምር ጦሩ የተለመደ ሁለተናዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ ይቀጥል " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ከተማ አስተዳደሩ " የጦርነቱ የፍልሚያ ቦታ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከራያ ሚዳ አልዘለለም " ያለ ሲሆን ሾልኮ ለማለፍና በወሬ ለመፍታት የተደረገው ስልትም እስካሁን አልሰመረም ብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ መልዕክቱን ያሰራጨው የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ በአካላዊ እንቅስቅሴ ጭምር በማጣራት መሆኑን አመልክቷል።

ምንም እንኳን አሁንም መሳሪያ ወርዶ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ እየቀረቡ ቢሆንም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል። ህወሓት ከዚህ ቀደም ለሰብዓዊነት ሲባል ተኩስ አቁም በታወጀበት ወቅት ከነበረበት ቦታ ወደፊት በመምጣት የአማራ ክልል ቦታዎችን እየያዘ ነው።

በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ መንግስት እንደተገለፀው የኢትዮጵያ መከላከያ ከቆቦ ከተማ ለቆ ወጥቷል፤ በዚህም ቆቦ በህወሓት ስር ይገኛል።

መንግስት ፤ ህወሓት #የህዝብ_ማዕበል ስልት በመጠቀም ጥቃት እያደረሰ መሆኑን በመግለፅ የህዝብ ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ መከላከያው " ቆቦ " ን መልቀቁን በትለንትናው መግለጫ ማስረዳቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወልድያ

ወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተንታኝ ነን የሚሉ የውጭ አካላት በማህበራዊ ሚዲያው ወልድያን በተመለከተ ሀሰተኛ ዜና እያሰራጩ ይገኛሉ።

" ከወልድያ አመራሩ ወጥቷል፣ ወልድያንም ህወሓት ይዟል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ሁሉም ሀሰት መሆኑና ህዝቡን ለማሸበር የሚሰራ ስራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ አይነት በሀሰት ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ፣ ህዝብን ለማስደንገጥ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉና በዚህ ሳቢያ ብዙ መመሰቃቀል ሲፈጠር እንደነበር አይዘነጋም።

እስካሁን ድረስ በወልድያና በቀጠናው ባለው ሁኔታ ከወልድያ ከተማም ይሁን ከጅቡቲ ወደብ የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን ከተለመደው የዕለት ተዕለት ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ እንዳልተከሰተ ከወልድያ ከተማ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው የወጡ፤ የትራንስፖርት አጥተውም በእግር የተጓዙ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

አንዳንድ መልዕክት የላኩ የግቢው ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ " ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግ ፤ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ እነሱም ቤተሰብም ጭምር ጭንቀት ላይ በመሆኑና በዚህ ሁኔታ ትምህርትን በንቃት መከታተል ስለሚያስቸግር ተቋማቸው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።

በተማሪዎቹ ስጋት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ደቡብ_ወሎ በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው…
#Update

#ሰቆጣ

መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወልድያ

ወልድያ አዳሯ #ሰላም የነበረ ሲሆን ዛሬ በ27/12/2014 ባንኮች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

በወልድያ ከተማ አቢሲኒያ እና ህብረት ባንክ ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ጨምሮ ሌሎች በከተማዋ ያሉ ባንኮች አገልግሎት ለመሰጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ገልጿል።

የወልድያ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለሰ አሁንም ቢሆን ወልድያ ሰላም እንደሆነች ገልፀው ፤ ህዝቡ እንዲረጋጋ እና ከሀሰተኛ ወሬ እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ሰቆጣ መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል። #ኮምቦልቻ ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር። በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው…
#Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን መፈፀሙን ከተማ አሳውቋል።

@tikvahethiopia