TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዲላ...

"ከዲላ ነው እምፅፍልህ-የቤንዝል ችግር ከእለት ወደ እለት #እየተባባሰ መምጣቱ የአብዛኛውን ነዋሪ የኑሮ ሁኔታ #እያናጋ ነው። በተለያዪ መገናኛ ብዙሀን የምንሰማው የክምችት ችግር እንደሌለ እና ሰው ሰራሽ መሆኑ እየተገለፀ ነው። በከተማችን ቤንዝል በገባ በሰአታት ውስጥ መኪና ላይ በተጫነ በርሜል እየተገለበጠ ይጓጓዛል ወደየት እንደሚጫንም አናውቅም የመንግስት ባለስልጣናት ጉዳዪን እያዪ ባላየ ማለፍን መርጠዋል። ቸርቻሪዎች እንደ ህጋዊ ነጋዴ በየመንገዱ በፕላስቲክ ኮዳ እየሞሉ በሊትር 60 ብር እየሸጡ ነው። የሚመለከተው አካል ካለ አፋጣኝ ምላሽ እንሻለን፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል፤ ቃጠሎውም #እየተባባሰ እንደሆነ ነው የተሰማው። ከደባርቅ ከተማ ወጣቶች ተሰብስበው ወደ ፓርኩ ሄደው #ለማጥፋት ቢፈልጉም ተሽከርካሪ ማግኘት አለመቻላቸውን ለአብመድ ተናግረዋል።

እሳቱ #ሳንቃ_በር አካባቢም መከሰቱን ወጣቶቹ ተናግረዋል የደባርቅ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የወጣቶችን #ጥቆማ ተጋርቷል።

ከፓርከ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መካከል አቶ #ታደሰ_ይግዛው እሳቱ እሜት ጎጎ እና ሳንቃበር አካባቢ #መባባሱን ገልጸው ወደ ቦታው ለማቅናት ተሽከርካሪ እያፈላለጉ መሆኑን ገልጸዋል። ጊዜው #በመምሸቱ ስልክ የሚያነሳላቸው ሰው ማጣታቸውንም ተናግረዋል። ከዞንና ክልል የሥራ ኃላፊዎች መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ሲል አብመድ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ?

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዛሬ ማምሻውን ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።

በዚህም መግለጫው ባለፉት #8_ወራት በአማራ ክልል በመንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝቡን እጅግ የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ መሆኑን ገልጿል።

" በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ #እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው " ብሏል።

" ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል " ሲል ምክር ቤቱ አስረድቷል።

እንደማሳያም ፦

➡️ በቀን በ29/7/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 የአንድ ቤተሰብ አባላትን እና 1 ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡

➡️ በ28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡

➡️ 29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት 300 ሺህ ንር ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድለዉ ጥለዉታል፡፡

➡️ በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት " ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ " ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት 8 ወራት ፦
- ከ80 በላይ ሙስሊሞች መገደላቸውን
- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መፈናቀላቸውን
- አርባ ሰባት (47) ሰዎች መታገታቸውን
- ከ260 በላይ ዘረፋዎች መፈፀማቸውን አሳውቋል።

" ይህን ዘረፋ፣ ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።

" ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት ፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝብ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች ፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ  " ሲል ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia