TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኩታበር⬆️ከደሴ ኩታበር ወደ ደላንታ /ወገል ጤና ሲጓዝ የነበረ FSR አይሱዙ ቅጥቅጥ የህዘብ ማመላለሻ መኪና ዛሬ ነሐሴ 30 2010 ዓ/ም ከጧቱ 1፡30 አካባቢ ከኩታበር ከተማ ወጣ ብሎ በግምት 10 ኪ/ሜ እንደተጓዘ #አደጋ ደርሶበታል፡፡ በአደጋው በተሳፋሪዎች ላይ #ቀላልና #ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

©የኩታበር ወረዳ የኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመጪው አዲስ ዓመት ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ በዓሉን እንዲያከብር ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ለወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ አባላትን በልዩ ልዩ ስፍራዎች ማሰማራቱን ገልጿል፡፡

የ2011አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ኮሚሽኑ አስታውሶ በዓሉን ምክንያት በማድረግም ጳጉሜን አምስት በሚሊንየም አዳራሽ
ከሚዘጋጀው ፕሮግራም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ስፍራዎች የመዝናኛ ዝግጅቶች ስለሚኖሩ ድንገተኛ #አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

📌ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ጥቆማ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ
መስመሮችን እና 011 1 11 01 11፣ 011 8 69 88 23 በመደወል ማሳወቅ ይችላል ተብሏል፡፡

©የአዲስ አበባ ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️

በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ #አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ6 ሰዎች ላይ ደግሞ #ከባድ እና #ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ በተለይ ለኢቲቪ በስልክ እንደገለፁት አደጋዎቹ የደረሱት በአቃቂ፣ ቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች ነው፡፡

አደጋዎቹ የደረሱት እግረኞች መንገድ በማቋረጥ ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑን የገለፁት ባለሙያው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለሥልጣን በዋዜማውም ሆነ በዛሬው ዕለት ምንም አይነት የእሳት አደጋ #አለመከሰቱን ገልጿል፡፡

በአዲሱ ዓመት ሕብረተሰቡ ከተለያዩ አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና ጥንቃቄ እንዲያደርግ መስሪያ ቤቶቹ አሳስበዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመቐለ እየተካሄደ ባለው 13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ
ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር #ደብረፅዮን_ገብረሚካኤል በጉባኤው መክፈቻ ላይ ያስተላለፏቸው ዋና ዋና ሀሳቦች ፡-

▪️በመልካም አስተዳደር እየተሰቃየ ያለው ህዝባችን መፍትሄ እንዲያገኝ ህወሓት አበክሮ ይሰራል፡፡

▪️የክልሉን ህዝብ ከድህነት ለማውጣት ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

▪️በውጭ እና በአገር ውስጥ ህገ መንግስቱንና መንግስትን #ለመናድ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ያለውን ሙከራ እናወግዛለን፡፡

▪️የዜጎቻችን ህገመንግስታዊ መብት እየተጣሰ መጥቷል፣ ብሄርን ከብሄርን የሚያጋጩ ኃይሎችን ልንመክታቸው ይገባል፡፡

▪️ይህን ጉዳይ በአግባቡ ካልያዝነው አገራችን ችግር ውስጥ ትገባለች፡፡

▪️የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

▪️የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ያለፈውን የችግር ግዜ ማካካስ የሚያስችሉ ስራዎች ይሰራሉ፡፡

▪️ይህ ጉባኤ የህዝባችን ህዳሴ ማረጋገጫ በመሆኑ ጉዟችንን የተለየ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎችን እናስተላልፋለን፡፡

▪️አዳዲስ አመራሮች ቦታውን የሚይዙበት መድረክ ይሆናል፡፡

▪️ለእኛና አገራችን የሚጠቅም ውሳኔ እንደሚተላልፍ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

▪️በክልላችን አዲስ የለውጥ ምዕራፉን ደግፋችሁ ለውሳኔዎቹ ንቁ ተሳታፊ እንደምትሆኑ ተስፋ አደርጋሁ፡፡

▪️የትግራይ ህዝብ በርካታ ችግሮችን አልፈህ እዚህ እንደደረስከው ሁሉ አሁንም ከህወሓት ጎን እንድትቆም እንጠይቃን፡፡

▪️አገራችን አሁንም #አደጋ ላይ ስላለች የምታደርጉትን ትግል አጠናክራችሁ ቀጥሉ፡፡

▪️ባለፉት አመታት ሁሉም የአገሪቱ ህዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆን በርካታ ስራዎችን ሰርተናል፡አሁን ላይ በአንፃሩ ያለው ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ ፈር ሊይዝ ይገባል፡፡

▪️በአዲስ አበባና አካባቢዋ ለደረሰው የዜጎች ሞትና ጉዳት የተሰማንን ሀዘን እንገልፃለን፡፡

▪️በዚህ ጉባኤ በትግራይ የተጀመረውን ለውጥ የሚያጠናክሩ ውሳኔዎችን ህውሃት የሚያስተላልፍ ይሆናል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በምዕራብ ኦሮሚያ በቄለም ወለጋ አካባቢ #ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን መንግስት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር #አይሻ_መሀመድ አስታወቁ፡፡ ሁኔታው ህዝብንና ህገ መንግስትን #አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ መንግስት #እንደማይታገሰው ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቦንጋ⬆️

"ፀግሽ እንደምታየው በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ህዝቡ እየመጣ ተቃውሞውን እያስተጋባ ነው። የከተማው ህዝብም ንፍሮ ቀቅሎ ለሰልፈኞች በማቅረብ ድጋፍ እያደረገ ነው። ደስ የሚለው ግን ከስራና ከሰው መጉላላት ውጪ እስካሁን በንብረትም ሆነ በሰው ላይ የደረሰ #አደጋ የለም። ጥያቄያቸው፦
1, የቡና መገኛነታችን ይከበር
2, ክልል የመሆን ጥያቄያችን ይመለስ
3, የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ችላ ብሎናል
4, ዞኑን ወክለው በክልል እና በተወካዮች ም/ቤት ያሉት አመራሮች የህዝቡን ጥያቄ እያስተጋቡ አይደለምና....ሌሎችም ናቸው። መነሻው ግን አንደኛው ነው። esa ከቦንጋ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በትናትናው ምሽት በኦስሎ ቀላል #አደጋ ገጥሞት እንደነበረ አስታወቀ፡፡ B787-900 በተሰኘው አውሮፕላኑ ላይ አደጋው የደረሰው ከመነሳቱ በፊት ክንፉ ላይ የነበረውን ግግር በረዶ እየተራገፈ በነበረበት ወቅት ከአንድ ቋሚ ጋር በመጋጨቱ ነው መሆኑን ገልጿል፡፡ በዚህም በአውሮፕላኑ የቀኝ ክንፍ ላይ  ነው ቀላል ጉዳት ስለማጋጠሙ የገለጸው፡፡ አደጋው ቀላል መሆኑን ያስታወቀው አየር መንገዱ ሁሉም ተጓዦች ወደ ሆቴል ማምራታቸውን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡ አየርመንገዱ በተፈጠረው ነገር ተጓዦችን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፥ ጉዞዋቸውንም ማመቻቸቱን ገልጿል፡፡

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ዛሬ ከጥዋቱ 1 ሰዓት አካባቢ አምባሳደር ሀራምቤ ሆቴል አካባቢ #ቶዮታ_ፒካፕ መኪና መስመሩን ለቆ በመውጣት በአካባቢው በነበሩ መንገደኞች ላይ #አደጋ አደረሰ፡፡ በአደጋው አንድ ሰው #ሲሞት በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው #ዘውዲቱ_ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ንብረትነቱ የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ የሆነ ሌላ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ባጋጠመው የሞተር ብልሽት ምክንያት በረራውን #አቋረጠ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው #አደጋ ምክንያት ከበረራ #የታገደው ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በወቅቱ ተሳፋሪ ያልጫነ ሲሆን አብራሪዎቹ ካሊፎርኒያ ወደሚገኘው የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ ወስዶ ለማቆም ጉዞ በጀመሩ በአስር ደቂቃ ውስጥ በአውሮፕላኑ አንደኛ ሞተር ላይ በተፈጠረ ብልሽት ሞተሩ ከልክ በላይ #በመሞቁ ምክንያት ወደ ካሊፎርኒያ ያደርጉት የነበረው በረራ ተቋርጦ ኦርላንዶ ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገደዋል ሲል cnbc ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።

'የቦይንግ ካምፓኒ በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ በማሰብ በሚመስል መልኩ ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰውን አደጋ ከማሰልጠኛ ሲሙሌተርና አውሮፕላኑን ያበር ከነበረው ፓይለት ጋር በተያያዘ ያጋጠመ አደጋ ለማስመሰል በኒውዮርክ ታይምስና በአንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሳሳተ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia