TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት " ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርምራ ጊዜውን የፈቀደው የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረቡትን መከራከሪያ እና የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው። የምርመራ ጊዜው ከግንቦት 19 ቀን…
#ችሎት

ዛሬ መርማሪ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የጠረጠሩበትን የክስ ጉዳይ ለማጣራት "ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠን " ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅረበዋል።

ግንቦት 19 በዋለው የመጀሪያው ቀን ችሎት፣ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን " ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በዩቱብ ኢንተርቪዎችን በመስጠት ቀስቅሷል" በሚል እንደሚጠረጥረው መግለፁ ይታወሳል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ፖሊስ ደንበኛቸውን የጠረጠረበት መንገድ ተጨባጭነት እንደሌለው፣ ደንበኛቸው ላለፉት አራት ዓመታት በዩትዩብ ምንም ዓይነት ኢንተርቪው ሰጥቶ እንደማያውቅ ለችሎቱ በማስረዳታቸው ፖሊስ የቀደመ የክስ ሀሳቡን ለመተው ተገዷል።

መርማሪ ፖሊስ ዛሬ በዋለው ችሎት "ዩቱብን ወደ ፍትሕ መፅሔት ቀይረው "ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ ፅሁፎችን በፍትህ መፅሔት ይጠቀማል" ብሏል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቃ አቶ ሔኖክ አክሊሉ "ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩትዩብ በመጠቀም ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ ይስራል ለዚህም የሰነድና የሰው ማስረጃ አለኝ ብሎ ይሄን ሁሉ ቀን የወሰደ ቢሆንም ፖሊስ፦ ሰነድም፣ ማስርጃም፣ ማቅረብ አልቻለም ይልቁን ወንጀል ፍለጋ ዛሬ ዩቱዩብን ትቶ በፍትሕ መፅሔት በመጠቀም የሚል አዲስ ክስ ይዞ ቀርቧል።

ፍርድ ቤቱ፣ ፖሊስ ከዩትዩብ ወደ መፅሔት የዞረበትን ሁኔታ ተመልክቶ አዲስ ክስ እንዳይቀበለውና ተመስገንን በዋስ እንዲያሰናብተው ጉዳዩንም በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዲመለከተው እንጠይቃልን" በማለት ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ ይሄንና በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ስለ ተፈፀመው ድብደባና የሰብዓዊ አያያዝ ጉድለት በተመለከተ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ግንቦት 30/2014 ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል::

Via Tariku Desalegn

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት ዛሬ መርማሪ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የጠረጠሩበትን የክስ ጉዳይ ለማጣራት "ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠን " ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅረበዋል። ግንቦት 19 በዋለው የመጀሪያው ቀን ችሎት፣ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን " ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በዩቱብ ኢንተርቪዎችን በመስጠት ቀስቅሷል" በሚል እንደሚጠረጥረው መግለፁ ይታወሳል። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ፖሊስ ደንበኛቸውን…
#Update #ችሎት

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ የ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተፈቀደላቸው።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት ፈቅዷል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ነው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፍርድ ቤት በዋስ ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ከእስር አልተለቀቁም። ዛሬ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት፣ 3ቱ ጋዜጠኖች በ10 ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑ ይታወሳል። ነገር ግን መርማሪ ፖሊስ ይግባኝ ለማለት ለ8 ሰዓት ቀጥሮ ነበር ሆኖም ችሎቱን የሚመሩት…
#ችሎት

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ መዓዛ መሐመድ እና ሰለሞን ሹምዬ ላይ የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ሐሙስ ሰኔ 2/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ችሎት፤ ለ3ቱ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደው ዋስትና ውድቅ እንዲደረግ እና 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ሐሙስ ሰኔ 2/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል። የመርማሪ ቡድኑ ምርመራዬን ስላልጨረስኩ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እና ከሌሎች ተቋማት የምንሰበስባቸው መረጃዎች ስላሉ የ14 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው…
#Update #ችሎት #ብርጋዴር_ጄነረል_ተፈራ_ማሞ

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል።

በዚህም ፤ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ምርመራ ካለቀ ደንበኛችን የተከሰሱበት ጉዳይ ዋስትና የሚያስከለክል ባለመሆኑ እና ተጠርጣሪው ደንበኛችን ታዋቂ ሠው በመሆናቸው ሊጠፉ ስለማይችሉ የደንበኛችን የዋስትና መብት ይከበርላቸው ሲሉ ተከራክረዋል።

ፍርድ ቤቱም ሲሰጥ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ምርመራው ያለቀ በመሆኑ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ ዘግቷል።

በመቀጠል የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ዐቃቤ ህግ አስተያየት እንዲሰጥበት አድርጓል።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሰሱበት ጉዳይ የሽብር ወንጀል ስለሆነ በተጨማሪም ከሚዲያ ጋር በተያያዙ ሌሎች ተጨማሪ ክሶች ሊቀርቡ ስለሚችሉ ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ተከራክሯል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የተጠርጣሪ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ለሰኔ 3/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነገ ፍ/ ቤት እንዲቀርብ ታዘዘ። ጋዜጠኛ ተመስገን ፍርድ ቤት ነገ እንዲቀርብ ዛሬ መጥሪያ ደርሶታል። ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ እንደተናገሩት " ለነገ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ ዛሬ እንደደረሰው አረጋግጫለሁ " በለዋል። " በዚህ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ቻሎት ነገ ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ጋዜጠኛ…
#Update #ችሎት

በትላንትናው እለት 06/10/2014 ዓ.ም በደረሰው መጥሪያ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ቻሎት ዛሬ ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አቃቤ ህግ ቀርቦ ተጨማሪ 15 የክስ መመሥረቻ ቀን ጠይቆ ተፈቅዶለታል ስለሆነም ለሰኔ 22/2014ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ተቀጥሯል።

በተመሳሳይ ጋዜጠኛ መዓዛ እንዲሁም ጋዜጠኛ ሰለሞን ላይ የተጠየቀው 14 ቀን ቀጠሮ ውድቅ አድርጎ 5ቀን ተቀጥረዋል።

(Gabriela)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

ዛሬ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ)
አመራር የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከታሰሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ክሱን ያቀረበውም የፌዴራል ፖሊስ መሆኑን የፓርቲው መረጃ ያመለክታል።

ፖሊስ አቶ ስንታየሁ ፤ ሕዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ ሲያሰራጩ እንደነበርም ጠቅሷል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው ባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ እየተዘጋጁ እንደነበር እና ጉባኤውን ለማደናቀፍ የደረገ ድርጊት ነው ፤ ውንጀላውም የፖለቲካ ተሳትፎ ተከትሎ የመጣ ፖለቲካዊ ጥቃት እንደሆነ ገልፀው ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ስንታየሁ ባሉበት መዝገብ ስር የቀድሞው የአማራ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን(አሥራት) ባልደረባ ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬ ፣ ዋሴ በመረሳው እና ደምስ አያሌው የተባሉ ወጣቶች ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባቸው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። እነሱም ሕዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ ሲያሰራጩ እንደነበርም ተጠቅሷል።

ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ 12 የምርመራ ቀናት በመፍቀድ ለሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

4ቱም ተከሳሾች ከየነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ ወደ ባሕር ዳር ሰባታሚት ወህኒ ቤት መወሰዳቸውን ባለደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia