TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ቶሌራ አዳባ-ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ እና የኦሮምያ ገዥ ፓርቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ በመተማመን እና በመግባባት መንፈስ እንደሚሠሩ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ #ቶሌራ_አደባ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በትጥቅ ትግል መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንግሥት በሰላም አሳምኖ ለመመለስ ጥረት ማድረግ አለበት፤ ካለበለዚያ “መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ግዴታ ስላለበት በወሰነበት መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር ይችላል” ብለዋል።

በኦዴፓና በኦነግ መካከል ሰሞኑን የተደረሰው ስምምነት አዲስ አለመሆኑን የጠቆሙት አቶ ቶሌራ በግንባራቸውና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ሰኔ 1/2010 ዓ.ም. አሥመራ ላይ የተደረሰውን ባለሦስት ነጥብ ስምምነት በፈጠነ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል።

የአሥመራው ስምምነት “ኦነግ #በሰላማዊ መንገድ ትግሉን በሃገር ቤት እንዲቀጥል ማድረግ ማስቻል፤ ካለው መንግሥትና በተለይም ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር የኦሮሞን ጉዳይ በተመለከተ መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር በጋራ የሚሠራበትን ሁኔታ በመደጋገፍ መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ትግላቸውን በመንግሥት ድጋፍ የሚቀጥሉበትን ሁኔታ በመመካከርና በመነጋገር ማመቻቸት” እንደሆነ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ሸዋ ዞን ዛሬ ጸጥታው ቢረጋጋም አንጸኪያና ሀገረ ማርያም ዋጨራ በተባሉ ቦታዎች የተኩስ ልውውጥ መሰማቱን DW ዘግቧል፡፡ ለችግሩ ተጠያቂው በታቀደ መልኩ የሚንቀሳቀሱት የተደራጁ የኦነግ ሃይሎች ናቸው፤ የማይታወቁ ሃይሎች የሚባለው ተራ መሽሞንሞን ነው በማለት ተናግረዋል የሰሜን ሸዋ ዞን ጸጥታ መምሪያ ሃላፊ ካሳሁን እምቢያለ ለሬዲዮው፡፡ በጥቃቱ የእምነት ተቋማት ተቃጥለዋል፡፡ ዛሬ አጣየ ጃኩብ በተባለ ቦታ እነዚሁ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ተጋጭተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና...

ኦነግ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር የፈጠሩት ታጣቂዎች የኦነግ አይደሉም ሲል አስተባብሏል፡፡ የግንባሩ ቃል አቀባይ #ቶሌራ_አደባ ለሸገር እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ ከሌላ ክልል የመጡ፣ ለተቃዋሚ ድርጅት የወገኑ ናቸው፡፡ ከየትኛው ክልል እንደመጡ እና ለየትኛው ፖለቲካ ድርጅት የወገኑ እንደሆኑ ግን ቃል አቀባዩ አላብራሩም፡፡

Via Sheger,DW,Wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በአሁኑ ወቅት #በኦነግ ትዕዛዝ የሚተዳደር ወታደራዊ ኃይል የለም›› – የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ #ቶሌራ_አደባ
.
.
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ‹‹በአሁኑ ወቅት በኦነግ ትዕዛዝ የሚተዳደር ወታደራዊ ኃይል የለም›› ሲል አረጋገጠ።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ ግንባሩ ቀደም ሲል ታጣቂ ኃይል የነበረው ቢሆንም ፣ወታደሮቹን ለአባገዳ እና ለኦሮሞ ህዝብ ካስረከበ ወዲህ ወታደሮች የሉትም።

መሠረታዊ የሆነና መታወቅ ያለበት ጉዳይ ኦነግ የመንግሥትን ጥሪ ተከትሎ ወደ አገር ቤት የገባው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሆኑ ነው ያሉት አቶ ቶሌራ፣ይህም በመሆኑ ‹‹ግንባሩ በአሁኑ ወቅት የትጥቅ ትግሉን አቁሟል።›› ብለዋል። ‹በኦነግ ትዕዛዝ ስር የሚተዳደር ወታደራዊ ኃይል አሁን እንደሌለም አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ቶሌራ ገለፃ፤ ኦነግ ወታደር አያደራጅም፤ ትግሉን የሚያካሄደው በሰላማዊ መንገድ በመታገል ነው። ዓላማውም ይኸው ነው። በአሁኑ ወቅትም የሚያደራጀው ሲቪልን ሲሆን፣ አባሎቹም ሲቪሎች ናቸው።

ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ኦነግን መወንጀል በመንግሥትም በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ተለምዷል። ኦነግ ባልሰራቸው ጥፋቶች ስሙን መጥቀስ በየጊዜው የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በአንዳንድ አካባቢዎች ከሚከሰቱ ችግሮች ጋር ኦነግን ማያያዝ በርከቷል።

 በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ቡድኖች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ ቶሌራ፣ ቡድኖቹ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ እንጂ በድርጅት መልክ የሚንቀሳቀሱ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ቡድኖቹ በዝርፊያ፣ በስርቆትና በመሰል ነገሮች የተሰማሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

የኦነግን መለያ ምልክት አሊያም ባንዲራ ይዘው መንገድ ላይ ተሽከርካሪ አስቁመው የሚዘርፉ እንዲሁም በኦነግ ስም በየመንደሩ እየተዘዋወሩ በሬ፣ ገንዘብ አምጣ የሚሉ ለዝርፊያ ብቻ ተሰባስበው የሚበተኑ ቡድኖች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። ይህን አይነቱን አካሄድ ግን የሚያጣራ አለመኖሩንም ገልጸው፤ ጉዳዩን አጣርቶ እውነተኛው ላይ መድረስ የሚችለው መንግሥት እንደሆነ አመልክተዋል።

አቶ ቶሌራ፣ በየትኛውም የሽግግር ወቅት ችግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ በተከሰቱ ችግሮች ላይ ሙሉ በሙሉ ኦነግን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም ማለት ነው።›› ሲሉም አስረድተዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia