TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ልጆቹ በስህተት ነው የተለቀቁት፤ እየታወቀ አይደለም!" - አቶ አይዛክ ሀሰን (የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ክትትል ሂደት መሪ)

(በአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

ከሞያሌ ለይቶ ማቆያ የተለቀቀው ግለሰብ ከወር በፊት ነበር ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው። በቦረና ዞን የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ባልደረባ አቶ አብዱዋ ዋቆ ግለሰቡን ከሌሎች 40 ሰዎች ጋር ወደ ለይቶ ማቆያ ያስገቡት የሱማሌ ክልል የጤና ባለሞያዎች ናቸው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ያኔ ከገቡት 40 ሰዎች በበሽታው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች ናሙና ለምርመራ የተላከ ቢሆንም የሱማሌ ክልል የጤና ባለሞያዎች ውጤቱ ሳይመለስ ሰዎቹን ለሳምንታት አቆይተዋቸው አርብ ዕለት ወደ ሀዋሳ እንደመለሷቸው ተናግረዋል።

የቦረና ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሮባ ዴንጌ ሰዎቹ የተሳፈሩባቸው የህዝብ አውቶብሶች መለየታቸው፤ ያቤሎ ሲደርሱ ያረፉበት ሆቴል ፀረ ተባይ መድሃኒት መረጨቱን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አቶ ሮባ በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ወደ #ሀዋሳ ያመሩት 40 ሰዎች፣ በዞኑ የተገናኙት ሌሎች ሰዎች በሙሉ ተለይተዋል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ክትትል ሂደት መሪ አቶ አይዛክ ሀሰን "ልጆቹ #ተሳስተው ነው የተለቀቁት፤ እየታወቀ አይደለም ፤ ኳረንቲን 14 ቀን ቢሆንም ልጆቹ 18 ቀን ነበር የቆዩት ፤ ውጤቱ ስለዘገየ ነው። ልጆቹ የተለቀቁት እየታወቀ አይደለም፤ በስህተት ነው" ብለዋል።

አቶ አይዛክ አንድ ላይ ከነበሩት መካከል የ4 ሰዎች ናሙና ለምርመራ የተላከ መሆኑን ገልፀው አሁን ሁሉም በደቡብ ክልል በለይቶ ማቆያ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሞያሌ በነበሩበት ወቅት 2 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እነሱን ሲንከባከቡ የነበሩ አጠቃላይ 9 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንደገቡ መደረጉን አስረድተዋል።

@tikvahethiopiaBot