TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሻሸመኔ አሰቃቂ ግድያ ሊመሰክር የነበረው ሰው ደብዛው ጠፍቷል‼️
.
.
ሻሸመኔ ላይ ሰው #ገድለው በመስቀል በአስከፊ ግድያ ወንጀል የተከሰሱ ወጣቶች ላይ ሊመሰክር የነበረው ሰው #ደብዛው_ጠፍቶብኛል ሲል የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

#በሻሸመኔ_ከተማ ነሐሴ ስድስት ቀን 2010 ዓ.ም አንድን ወጣት #ቦንብ ይዟል በሚል ገድለው የዘቅዝቁ ወጣቶች መኖራቸው ይታወሳል። በዚህ በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ከተከሰሱ ስድስት ሰዎች መካከል ሁለቱ የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው እና የተቀሩት አራት ተጠርጣሪዎቸ ደግሞ ምስክሩ ደብዛው በመጥፋቱ በነጻ መለቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል አቃቢ ህግ አቶ #አሽማው_ሰይፉ ገልጸዋል። ተከሳሾች የምስክሩን ደብዛ አጥፍተዋል የሚል ግምት እንዳለ የገለጹት አቶ አሽማው፤ ምስክሩ ባስመዘገበው ስልክ ቁጥርም ሆነ በአድራሻው ተፈልጎ እስከአሁን ሊገኝ አለመቻሉን ተናግረዋል።

በተለያዩ #ማህበራዊ_ሚዲያዎች ጨመሮ በግለሶችና በተቋማት የሚገኙ የምስል እና ድምጽ ማስረጃዎች እንደምስክርነት ለምን ጥቅም ላይ አልዋሉም የሚል ጥያቄ ከአዲስ ዘመን የቀረበላቸው አቶ አሽማው፤ የምስልና ድምጽ #ማስረጃዎቹ ከፖሊስና ከተለያዩ አካላት ለፍርድ ቤቱ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ይሁንና ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ #ቅንብረ የተደረገበት ስለመሆኑ እና ስላለመሆኑ ማረጋገጫ ባለማግኘቱ ማስረጃው ፍርድቤቱን ሊያሳምን አልቻለም።

እንደ አቶ አሽማው ከሆነ፤ አራቱ ተከሳሾች በነጻ ቢለቀቁም የሰው ምስክሩ በተገኘ ሰዓት ክሱ መጀመሩ አይቀርም። በፍርድ ሂደቱ ላይ የአራቱ ሰዎቸ በነጻ መለቀቅ በአቃቤ ህግ በኩል ተቀባይነት ባለማግኘቱ ይግባኝ ተጠይቄ ውሳኔ እየተጠበቀ ይገኛል ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን(የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia