TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR (1).pdf
#ይነበብ🚨

" በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል።

በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ '  ሰፍሯል።

ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ?

- በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት #የዳኝነት_አካላት ለተወሰነ ጊዜ፦

በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ #ክትትል_ለማድረግ

የኮምፒዉተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችንና ሰርቨሮችን ለመለየት፣

መገናኛዎችን #በክትትል ሥር ለማዋል ወይም #ለመጥለፍ

ድርጊቶችን፣ ባህሪዎችንና ንግግሮችን በድምፅ እና በምስል #ለመቅረፅ እና #ፎቶግራፍ_ለማንሳት

የደብዳቤ ልዉዉጦችን #ለመጥለፍ እና #ለመያዝ

በሽፋን ሥር ስለሚደረግ ምርመራና በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍ ለመጠቀም፣

የሚያስችል ትዕዛዝ #ለወንጀል_መርማሪ_አካላት መስጠት ይችላሉ።

- የመርማሪ አካል የተደነገጉትን የማስረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚችለዉ ፍርድ ቤት አስተማማኝ ምክንያት መኖሩን በማረጋገጥ #ሲፈቅድ_ብቻ ነዉ።

- መርማሪው አካል #አስቸኳይ_ሁኔታ_ካጋጠመው በአካባቢው ያለውንና የሚመለከተውን የዓቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስረጃዎችን ሊሰበስብ ይችላል፡፡

- መርማሪ አካል #ያለፍርድ_ቤት_ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስረጃ ለመሰብሰብ በጀመረ በ፵፰ ሰዓት ውስጥ ምክንያቶቹንና በዓቃቤ ሕግ የተሰጠውን ጊዜያዊ ፈቃድ ጨምሮ ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል። ፍርድ ቤቱ የጥያቄውን አግባብነት መርምሮ ለመቀበል ወይም ደግሞ ውድቅ ለማድረግ ይችላል፡፡

- ፍርድ ቤት የምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበስብ ለመርማሪ አካል ፈቃድ ሲሰጥ፡-
ሀ. ማስረጃ ስለሚሰበሰብበት ዘዴ እና ስለሚከናወንበት አግባብ፤
ለ. የሚከናወንበት ጊዜ በተመለከተ ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡

- የማስረጃ ማሰባሰቢያው ዘዴ ጠለፋ ወይም ክትትል እንደሆነ #ጠለፋዉ ወይም #ክትትሉ የሚደረግበትን የስልክ ፣ የፋክስ ፣ የሬዲዮ ፣ የኢንተርኔት ፣ የኤሌክትሮኒክስ ፣ የፓስታና የመሳሰሉትን የግንኙነት መስመሮች አድራሻ ወይም መለያ መጥቀስ አለበት፡፡

- ማንኛውም የመገናኛ አገልግሎት አቅራቢ በመርማሪ አካል ጠለፋውን ለማካሄድ ሲጠየቅ ጠለፋው በፍ/ቤት ወይም በአቃቤ ሕግ የበላይ ሃላፊ የተፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ አለበት፡፡

- በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሕግ አስከባሪ አካላት በጠለፋ የተገኘ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ #በጠለፋ_በተገኘበት_መልክ_በቀጥታ ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም፡፡

ሙሉ ረቂቅ አዋጁን በዚህ ያንብቡ 👇 https://t.iss.one/tikvahethiopia/88222

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia