TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሜቴክ ሃለፊዎች ላይ ክስ ተመሰረተ‼️

#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመሠረተ።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ላላስተማራቸውና ባልተቀረፀ የትምህርት ካሪኩለም ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት፣ የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

በአሜሪካ መንግሥት ከሚታወቀውና በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ዋነኛ ከሆነው ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ጋር ተቀራራቢ ስም ያለው ተቋም፣ ነገር ግን በማንም የማይታወቅ በማስተርስና በዶክትሬት ዲግሪዎች ለማስተማር መኮንን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በተባለ ተጠርጣሪና ባልተያዘ ግለሰብ መቋቋሙን ክሱ ያስረዳል፡፡

ግለሰቡ ራሱን የሐሰተኛ ተቋም ሥራ አስኪያጅ አድርጎ በማቅረብ፣ ከቀድሞ የሜቴክ ኃላፊዎች ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትለ፣ ሻለቃ ገብረ ሥላሴ ገብረ ጊዮርጊስ፣ ሻለቃ ፋሲልአበራ፣ መቶ አለቃ ቶማስ ደረሰ፣ ወሰን የለህ ኃይለ ሚካኤልና ሀድአት ወልደ ትንሳይ በተባሉ የሜቴክ የተለያዩ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በጥቅም በመመሳጠር፣ ሐሰተኛው ተቋም ከሜቴክ ጋር ከፍተኛ ትምህርት ለማስተማር የውል ስምምነት መፈራረሙንና ዋና ዳይሬክተሩ እንዲፀድቅ ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ግለሰቡ ድርጊቱ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዳይታወቅ የተለያዩ የውጭ አገር ዜጎችን በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ፣ ክፍያው በውጭ ምንዛሪ እንዲፈጸምላቸው ስምምነት ማድረጉን ክሱ አክሏል፡፡ ግለሰቦቹ ትምህርቱን ሳያስተምሩ ተመራቂዎች ዲግሪ በሕገወጥ መንገድ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ እንዲሰጥ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

#በሐሰት የተቋቋመው ኮሌጅ በታዳሽ ኃይል፣ በኦፕሬሽን ማኔጅመንትናበኢንዱስትሪያል ኢኮኖሚክስ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪዎች ለመስጠት አራት ውሎችን በመፈጸም፣ በአጠቃላይ 3,901,140 ዶላር ወይም 75,114,030 ብር ሐሰተኛ ተቋሙ አሜሪካ ውስጥ በከፈታቸው የሒሳብ ቁጥሮች ገቢ ማድረጋቸውንና በእጅ አዙር የጥቅሙ ተካፋይ በመሆናቸው፣ ሥልጣንን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ዓቃቤ ሕግ መሥርቶባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ሜጀር ጄኔራል #ክንፈ #ማርዳ_መለስ ለተባለች ግለሰብ በሁለት ዙር 56,205 ዶላር ወይም 1,250,886 ብር ክፍያ ከሜቴክ እንዲከፈል በማድረጋቸው፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በመንግሥት ላይ 76,364,916 ብር ጉዳት ማድረሳቸውን የቀረበባቸው ክስ ያሳያል፡፡   

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.

4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia