TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#updateየቡራዩ ከተማ ፖሊስ⬆️

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ በተለያዩ ቀበሌዎች የጸጥታ አካላት ደንብ ልብስ፣ የጦር መሳሪያ፣ ገንዘብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

በግለሰቦች መኖሪያ ቤትና በተሸከርካሪዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ የአዲስ አበባ ፖሊስና የአገር መከላከያ ሰራዊት ደንብ ልብስ፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 5 ሽጉጥ፣ የተለያዩ ህገወጥ ማህተሞች፣ 45 ሺህ ብርና ሌሎች ድምጽ አልባ መሳሪያዎች ተይዘዋል።

እንዲሁም #ግጭቱን ለማስተባበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ቪትስ መኪናዎች ከነአሽከርካሪያቸው ጋር መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ጠቁሟል።

የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደረጀ ባይሳ እንደተናገሩት፤ በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰውን ጥቃት የተጠረጠሩ ሰዎች ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

“ከዚህ #ወንጀል በስተጀርባ ያሉ የተለያዩ ዕቃዎችም ተይዘዋል።ሽጉጦች፣ ክላሾች፣ በዚህ በወንጀል ድርጊቱ በሰው ግድያ ላይ በተለይ የተጠረጠሩ ሰዎች ተይዘዋል። እነዚህ ሰዎች #እንዲጨፋጨፉ፣ ለወንጀል ድርጊት እና #ለሞት መንስዔ የሆኑ ናቸው ተብሎ ህብረተሰቡ በሰጠን ጥቆማ፣ በሁለት ቪትስ መኪና እየተንቀሳቀሱ የተያዙ ሰዎች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ውጤቱ ለህዝብ ይፋ ይሆናል።

በዚህ ሂደት የተለያዩ ዩኒፎርሞች፣ የተለያዩ ዕቃዎች፣ የቢሮ ማህተሞች ተይዘዋል። ከዚህ ከግድያ ጋር ላይያያዝ ይችላል። የተለያዩ የሚሊተሪ፣ የፖሊስ ልብስ ተይዘዋል። ፖሊስ አስመስሎ፣ ፖሊስ እንደዚህ አደረገ በማለት ይህን በመልበስ የክልሉን ፖሊስ ስም በማጥፋት የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ይሆናሉ ብለን የያዝነው አለ በምርመራ፣ በቁጥጥር ስር ውሎ-#እያጣራን ነው። የአገር መከላከያ ደንብ ልብስ እራሱ ሬንጀር ለብሶ ከቤቱ የተገኘ ስላለ እሱንም የአገር መከላከያ ሰራዊት ስም ለማበላሸት እነሱ ናቸው እንደዚህ የሚያደርጉ የሚል ግምት ስላለ እሱንም አሁን በቁጥጥር ስር አውለን ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ 8 ሽጉጥ፣ 3 ክላሽ ተይዞ በዚህ ይዞ ሲንቀሳቀሱ ያየነው አሁን በቁጥጥር ስር አውለን እያጣራን ነው።

ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ላይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ በጥቃቱ የደረሰውን ጉዳት የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ፖሊስ የከፋ ጉዳት እንዳይከሰት ከወጣቶች፣ ከአድማ በታኝ ፖሊስና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ችግሩን ለመቆጣጠር የተለያዩ ስራዎች ሰርቷል።

እስከ ትናንት ድረስ በወንጀሉ ተጠርጥረው የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

በደረሰው ጥቃት የተፈናቀሉ ወገኖች ቢኖሩም ድርጊቱ #የኦሮሞ ተግባር #ሳይሆን የተጀመረው አገራዊ ለውጥ እንዳይቀጥል የሚፈልጉ ሃይሎች ተግባር እንደሆነ በመግለጽ ሳይፈናቀሉ የቀሩ ሰዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመመለስ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት ያለው ኮሚቴ ተቋቋሞ እየተሰራ እንደሆነ የጠቆሙት ምክትል ኮማንደር ደረጀ ህብረተሰቡ የተፈናቀሉትን ዜጎች ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል።

የፖሊስ አዛዡ ከዚህ በኋላ በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሚሆን ጠቁመዋል።

©OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች #ለሞት እና #ለአካል_ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " - ራኬብ መሰለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ፤ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ ተጎጂዎችን፣ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል የጸጥታ አካላትን፣ የቆሎጂ መጠለያ ሠራተኞችን እና የሆስፒታል ባለሞያዎችን አነጋግሯል።

በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት " ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ " የሚኖሩ ቢያንስ 6 ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስለዚህም ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት በመሥራት በአካባቢው ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ለሆኑ ጉዳዮች ሰላማዊ መፍትሔ በመስጠት የነዋሪዎችን እና የተፈናቃዮችን ደኅንነት በዘላቂነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ፣ ለደረሰው ጉዳት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ባደረጉ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን ጠቅሰው “በተለይም ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አክለውም " በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት) መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣንም ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገው ሌላው የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል ! " - ነዋሪዎች (ከሰሞኑን በሚዛን አማን በነበረ ህዝባዊ ውይይት ላይ የተነሳ) #ቲክቫህኢትዮጵያ @tikvahethiopia
" የሀብታም ልጅ #በገንዘቡ የባለስልጣን ልጅ #በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገዉ ሌላዉን የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል " - ነዋሪዎች

ሰሞኑን በሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

ይኸው ውይይት በደቡብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደና በቤኒሻንጉል ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የተመራ ነበር።

በህዝብ ወይይቱ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል።

ከነዚህ መካከል ፦

እንደካሮት ቁልቁል የሚሄደዉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ለምን ባለቤት አጣ ? ተመዘበረበት የተባለዉን ገንዘብ ጉዳይ የያዘዉ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወዴት አደረሰው ?

ያለብን የመንገድ ችግር አሁንም እናቶች በህክምና እጦት #ለሞት እየዳረገ ነው። መፍትሄ ለምን አይሰጥም ? የሚሉት ይገኙበታል።

ሌላው የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣን ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገዉ ሌላዉን የድሀ ልጅ ከስራ ዉጭ አድርጎታል ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ አሰምተዋል።

ተሳታፊዎቹ መንግስት ቁርጠኛ አመራር በመስጠት ስርአቱን ሊያስተካክለዉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በእለቱ መድረኩን የመሩት የደቡብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ፤ ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመንግሥት በኩል ቀይ መስመር በማለት ያስቀመጠዉ ጉዳይ ነው " ሲሉ  ገልጸው ችግሩን በመቅረፉ ሂደት ህዝቡ ከመንግስት ጎን ሊቆምና ሊታገል ይገባል ብለዋል።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia